ሁሉ አይጠቅምምና፤ ያገኘኸውን ሁሉ አትብላ!ሳተናው!
አንተ በዓላማ ለዓላማ የምትኖር ሰው ነህና ከርዕይህ ሳትደርስ ሳታሳካውም እንዳትቀር አመጋገብህን አስተካክል። ምንም እንኳ ሁሉን መብላት ብትችልና ቢቀርብልህም ሁሉም ግን አይጠቅምህምና አትብላ።

ይልቁንስ ከተመገብካቸው በኋላ ባንተ ላይ ስለሚያደርሱት ተጽዕኖ አስበህ መርጠህና ለይተህ ተመገብ እንጂ።

ሳተናው!
በዚህ ጦማር ውስጥ ምግብ ስልህ፦ ምግብ ስጋዊ፣ ምግብ መንፈሳዊ እና ምግብ አእምሮኣዊውን ማለቴ መኾኑን አስተውል።

ለእነዚህ ሦስቱ አንተነትህ የሚኾን ምግብ ዓለም ከቀድሞው ጊዜ ይልቅ በዓይነትና በብዛት ታቀርባለች። ምንም እንኳ የአቅርቦታቸው ነገር አንዱ ካንዱ ቢለያይም ምግቦቹ ግን አያቶቻችን ከኖሩበት ዘመን ይልቅ ሰዎች ተጠበውባቸው ይዘጋጃሉ።

ይህን አዘገጃጀታቸውን፣ አቀራረባቸውን እና ተደራሽነታቸውን ስታይ ሁሉንም መቅመስ(መብላት) ሊያምርህ ይችላል።

ነገር ግን አምሮ የተሰራ፣ ተከሽኖ የቀረበ፣ ጣፍጦህም የምትበላው ሁሉ አይጠቅምህም፤ አይጠቅምህም ብቻም ሳይኾን ሊጎዳህም ይችላል።(ምግብ ስልህ ስጋዊ፣ መንፈሳዊ እና አእምሮኣዊ ምግብ መኾኑን አትርሳ)

ሳተናው!
አስረጅ ስለ ስጋዊ ምግብ፦
ለሰውነታችን ምግብ ቢያስፈልግንም ጤንነቱ የተረጋገጠ፣ ከጥቅሙ አልፎ የጎንዮሽ ጉዳት ቢኖረው እንኳ ጉዳቱ ኢምንት የኾነውን መርጠን እንመገባለን።

ለምሳሌ እንደ ኬክ፣ አይስክሬም፣ ቺፕስ እና የመሳሰሉትን ዓይነት ጣፋጭ ምግቦችን ብንወስድ እንደ ዋና ምግብ በብዛትና በተደጋጋሚ ብንወስዳቸው ከጥቅማቸው ይልቅ ጉዳታቸው ያመዝናል።

ይኹን እንጂ እንደዚህ ዓይነቶቹ ምግቦች ለአብዛኞቻችን ጣፍጠውን እንደምንበላቸው ስሜታችንን ብንከተል ኖሮ ሁሌ በበላናቸውና በተጎዳንም ነበር።

ምግብ አእምሮኣዊ፦
በመደበኛ ትምሕርት ቤትም ኾነ በመገናኛ ብዙኃን የምንቀስማቸውን እውቀቶች በማስተዋል መቀበል ያስፈለሰጋል።

በተለይም ዛሬ ዛሬ ዓለም በበይነ መረብ ወደ አንድ መንደርነት በተለወጠችበት ወቅት እና ከእውነትኛ መረጃ ይልቅ የፈጠራ ወሬ በከፍተኛ ፍጥነት በሚጓዝበት ኹኔታ አንተ የምትመገበውን መረጃ በደንብ ልታጤነው ግድ ይልሃል።

ሳተናው!
ማንም ስሜቱ ከቁጥጥሩ ዎጪ የኾነን ሰው (ስሜታዊን)፤ ሌሎች ስሜቱን የሚቀሰቅሱ ነገሮችን እያደረጉ ይቆጣጠሩታል።

በየቀኑም የእርሱ ስሜት ላይ ልጓም አበጅተው ሳር አጀንዳውን እያሳዩ ይጋልቡታል። ራሱን መጉዳት ብቻ አይደለም ሌሎችንም ይጎዱበታል።

ይኽንንም ለማድረግ አስቀድመው ትውልዱ ራሱን እንዳይገዛ፣ ስሜቱን እንዳይቆጣጠር እና ለራሱ ጥፋት/ስንፍና ኃላፊነትን ከመውሰድ ይልቅ ሰበበኛ እንዲኾን ያደርጉታል።

ራሱን የማይገዛ ስሜታዊና ለሥራውም ኃላፊነት የማይወስድ ትውልድ ደግሞ ለማፍራት ቀላሉ መንገድ ደግሞ ትዳርን በተለያዩ የዳቦ ስሞች አስፈርሶ ልጆችን ያለ አባት ማሳደግ ነው።

…. ይቆየን

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *