ላታገባት ከባሏ ሆድ አታስብሳት

ሳተናው!

ሴታቆርቋዥ ወንዶች (Feminist Men) ከማንም እና ከምንም በላይ ዱርዬ እና አባወራ ወንዶችን ይጠላሉ(ይበልጡን አባወራውን)። “ለምን” ብላችሁ ስትጠይቁ እነርሱ በሴቶች(በሚስቶቻቸውም ቢኾን) ለመወደድ፣ ለመፈቀር፣ ለመዋሰብ ብለው የማይገቡት ጉድጓድ የማይወጡት ዳገት የለም።

ይኹንና እነርሱ አንድም ሳይሳካላቸው ዱርየው ወንድ በላይ በላዩ ሲቀያይር፤ ያ ቆፍጠን ያለው አባወራ ደግሞ ያለ ብዙ ድካም ትዳር መሥርቶ ሲወልድና ሲከብርም ያበሳጫቸዋል።

ይኽ የኋለኞቹ ጠባይ የፊተኞቹን ሲያሳጣቸው በተለይም ደግሞ የአባወራው የትዳር የቤተሰብ ስኬት ዐይናቸውን ደም ያስለብሰዋል።

ከሴቶች ጋር ባላቸው ግንኙነት ሴታቆርቋዥ ወንዶች ብዙ እንደመድከማቸውና ለሴቶች ብዙ እንደመኾናቸው ስኬታማ አይኾኑም። ዱርዬውና አባወራው ግን ምንም መነጠፍና መጎዝጎዝ ሳያስፈልጋቸው ራሳቸውን ኾነው።፣ ገዝተውና ተማምነው በመገኘት ብቻ ሚስት ለማግባትና ቤተሰብ ለመመሥረት አያይቸገሩም ።

ዱርዬውስ ዱርዬ ነው ለእርሱ ያላቸውን ጥላቻ ማሕበረሰቡም ያግዛቸዋል። ነገር ግን ለምን አባወራው ይጠላል?

አባወራው ፦ እነርሱም ኾኑ ምስኪኖቹ እንደሚያደርጉት ሰውን(በተለይም ሴቶችን) ምሩኝ፣ አኑሩኝ፣ እዩኝ፣ አሙቁልኝ፣ አጨብጭቡልኝም አይልም።  ሴቶች እንዲወዱኝ ብሎ የሚሠራው ሳይኖር ራሱን በመኾኑ፣ ባመነበት በመኖሩ፣ በፈለገውም ላይ ግልጽነቱ፣ በራስመተማመንና ድፍረቱ ያስከብረዋል(ልብ አድርግ! ያስወድደዋል አላልኩህም ያስከብረዋል)።

የዛሬ ድኅነቱን አይቶ የሚያዝን አልያም የዛሬ ኃብቱን አይቶ የሚመጻደቅ ሳይኾን ርዕይን ይዞ ዓላማን ሰቅሎ የሚኖር በእርሱም የማይደራደር ነው።
======================================
እንዴት እንለያቸው

ሴታቆርቋዥ ወንዶች(Feminist Men) “መንፈሳዊ” እንጂ ኃይማኖተኛ አይደሉም። ይኼም እንዴት ነው ቢሉ በተከታዮቻቸው ዘንድ የሚተገበር የጋራ መመሪያ ያላቸው ኃይማኖቶች(በእኛ አገር ክርስትናና እስልምና) ስለ አባወራው የትዳሩ፣ የቤቱ መሪነት በማያሻሙ ቃላት ያትታሉና ነው። ይኽ ደግሞ እነዚኽ ወንዶች ከሚያራግቡት ኃሳብ ጋር አይሄድምና “መንፈሳዊ ነኝ” እንጂ “ኃይማኖተኛ ነኝ” ማለትን አይፈልጉም።

በወጡበት መንበር በተቀመጡበት ወንበር ኹሉ ስለ ራሳቸው ተፈጥሮ ከማውራት፣ ራሳቸውንም በራሳቸው ከመግለጽ ይልቅ ስለሴቶች፣ ቡድን ቢመሠርቱ በሴቶች፣ የንግግራቸው መግቢያ፣ መጨበጪያ መደምደሚያም ሴቶች፣ ምንም ይኹን ምን የሚስማሙበት ኃሳብ የሴቶች… ….
ሳተናው! ይኽ በወንድ ልብስ የተሸለመ እርሱ ማን ነው? ሴታቆርቋዥ ወንድ (Feminist men)።
=========

ፊደል መቁጠራቸውንም ከስልጣኔ ቆጥረው (በዓለማዊ እውቀት ትልቅ ማዕረግ ላይ የደረሱ ነገር ግን መረን ጠባይ ያላቸውን አስብ)፣ “ኹሉንም ያማከለ፣ ያቀፈ፣ ያካተተ ” መንፈሳዊነት ይዘናልም ብለው፣ በጭብጨባም ብዛት የገነነ ስማቸውን ተገን አድርገው ትዳሩን በስርዓት የሚመራውን አባወራ አምባገነን ሲሉ ይከሳሉ።

እነርሱ ደርሰው ለ”ሴቶች” ተቆርቋሪ ናቸውና በሰው ሕይወት (ትዳር) ሳይጠሩ ዘው ብለው ይገባሉ። ይኼም እንዴት ይታወቅባቸዋል መሰላችሁ ሴታቆርቋዥ ወንዶች (Feminist Men) እኛ “አባወራ” የምንለውን ወንድ ይጥሉት እንጂ ፊት ለፊት መጋፈጥ ይፈሩታል።

ዘው ብለው ለሚገቡበት ትዳር ውስጥም ችግሮችን ሰሚ፣ መፍትሔዎችን ጠቋሚ ኾነው የሚያማክሩት ሴቷን (ሚስቲቱን) ብቻ ነው። አገባባቸውም በቀጥታ ሴቲቱን(ሚስቲቱን በማናገር አልያም በመገናኛ ብዙኃንና በሌሎችም መንገዶች አስተማሪ በመምሰል ነው። አፋቸውም ቅቤ ነውና ብዙውን ጊዜ የሴቶቹን ጆሮ ለማግኘት አይቸገሩም በኾዳቸው ግን ጩቤ አለና ያንን እነርሱ የሚቀኑበትን ትዳር ይገዘግዙታል።

በእንደነዚህ ዓይነት ወንዶች ብዙ ሴቶች ተታለዋል፣ ሳያገቡም ቀርተዋል ከማንም፣ የማንም ሳይኾኑ የኹሉምም ኾነው ቆመው ቀርተዋል። አለበለዚያም አግብተው ሲያበቁ “ነፃነታችንን ተነፍገናል”፣ “ለካ ስንት የሚያስቡልን ወንዶች ቀርተውብናል” በማለት እምቢኝ ሲሉ “ጀግኒት” ተብለው እየተወደሱ ትዳራቸውን አፍርሰዋል፣ ልጆችም ተበትነዋል፣ መረንም ኾነዋል።

ሳተናው!

ሴታቆርቋዥ ወንዶች (Feminist men)  ለሴቶች መብት “እንቆማለን” የሚሉ አስመሳዮች ናቸው። ቤታቸውን ፣ ትዳራቸውን ራሳቸውንም እንኳ መምራት ሳይችሉ ከሰው ጎጆ ገብተው የአባወራውን ሚስት ስትታዘዘው እና ስትራዳው ቢያዩ “ተጨቆንሽ፣ ተገፋሽ፣ ተበደለሽ፣ ተረታሽ” እያሉ የሚበሳጩበትን አባወራ ትዳር ያፈርሳሉ።

እነዚህ ወንዶች በሴቶች ዘንድ ዝናን ያተርፉ ዘንድ ሕልምን ያልማሉ፦

ሕልማቸው፡ “የሴቶች መብት(እኩልነት) ማስጠበቅ” ነው

ተልዕኮዋቸው፡ አንዲት ከባሏ ትዕዛዝም ኾነ መመሪያ የማትቀበል (ትኅትና የሌላት)
                  ትዳሯን “በጋራ” አልያም እርሷ የምትመራ
                  ራሷን የቻለች፣ “ባል”ሳታገባ መውለድና ማሳደግ የምትችል
                  ለልጆቿ እርሷ ብቻ በቂ የኾነች ……. ሴትን ማፍራት ነው

ድብቁና ዋነኛው ዓላማቸው ግን፡ ከሴቶች አድናቆትን፣ ጭብጨባን፣ ወዳጅነትን፣ ጓደኝነትን፣ ወሲብን ማትረፍ ነው።

እነርሱ ክቡር ስለኾነው ትዳር፣ በእርሱም ውስጥ ስላለው ኪዳን፣ ፍሬዎቹ ስለኾኑት ልጆች(ትውልድ)፣ ስለ ሀገር ገንቢነቱም በአፋቸው ቢያቆለጳጵሱት እንጂ ጉዳያቸውም አይደለም። እነርሱ ስለተፈጥሮኣዊ እውነት፣ ስለአምላካዊ ትዕዛዝ ስለሰው ልጅም ሕልውና ግድ አይሰጣቸውም።

ከዚኽም የተነሳ ለሰው ዘር በተለይም ለሴቶች መብት ቆመናል ይበሉ እንጂ የሰው ልጅ ለዘመናት የኖረበትን ቀዳሚውንና መሠረታዊውን ተቋም(ትዳር) ያፈርሳሉ። የሚገርመው ታዲያ አካሄዳቸውም (የሚጠቀሙበት ዘዴም) ኾነ የመጨረሻ ግባቸው በግብር ከሚመስላቸው ከአባታቸው ጋር አንድና አንድ ነው።

ሳተናው! ብልህ ከሰው ስሕተት ይማራል…..

…. … አልጨረስኩም …. ይቆየን

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *