መዘዙ በትውልዳችን ላይ ምን ይዞ መጣ… ይመጣስ ይኾን?

በራድነት በወንዶች ላይ ሲታይ መልካም ይምሰል እንጂ ትዳርን መምራት፣ ቤትን ማስተዳደር፣ ማሕበረሰብን ሀገርን መምራት እና ሌሎችም ከወንዳወንድነት ሕብረተሰቡ ሊያገኝ የሚጠብቀውን ጥቅም ያሳጣል።

ራስህን ለማሸነፍ ምን ብትጥር ራስህንም ለማሻሻል ምን ብትደክም ትክክለኛ መሻሻል እና እድገት እንዳትደርስ ይዳርግሃል። ለዚህም አእምሮህን በማያስፈልጉህ መረጃዎች በመሙላት በማይመለከቱህም በማስጨነቅ እንደዲሁም ስለራስህ ተፈጥሮ የተዛባ መረጃ የሚሰጡህ የመገናኛ ብዙኃኑና ማሕበራዊ ድረገጹ ትልቁን ሚና ይጫወታሉ።

ከምትፈልገው ውጤት ትደረስ ያለምከውንም ታገኝ ዘንድ እነዚኽን እንቅፋቶች ከሥር ነቅለህ መጣል አለብህ።
ትልቁም የስኬትህ እንቅፋት ራስህ ነህ። ዘመኑ በተለያየ መንገድ በምግብ፣ በመረጃና በድርጊት የበረዘው ተፈጥሮ ግን በዓላማ የሰጠችህን ወንድነት ያስጠላህ/ያስጣለህ በራድ ወንድነት/ ስልብነት ተሸክመሃልና ነው።
በራድነት ከራሱ ከወንዱ ጉዳት ቀጥሎ ሚስቱን፣ ልጆቹን ቤተሰቡን የሚኖርበትን ሕብረተሰብ ሀገርን ይጎዳል።

በራድነት እነዚህን ይዞ መጣ፦

፩ኛ ደካማና የሥራ ተነሳሽነት ያለመኖር
፪ኛ ከኃላፊነት መሸሽን
፫ኛ የወሲብ ስንፍናን(ከስሜት መቀዝቀዝ ጀምሮ እስከ ስንፈተ ወሲብ)
፬ኛ ከአካላዊ ጥንካሬና ቅልጥፍና ይልቅ ስለመልክ፣ ስለአለባበስ መጨነቅን
፬ኛ ለራስ ዋጋ ማጣት/የራስን ዋጋ ከሰው መፈለግን(low self-esteem)
፭ኛ ዝቅተኛ በራስ መተማመንን
፮ኛ ራስወዳድነትን(ለራሳቸው ብቻ እንጂ ስለወገን፣ ሀገር፣ ግድ አለማለት)
፯ኛ ግልጽ ያለመኾን
፰ኛ አኩራፊነትን(ስሜታዊነት)
፱ኛ ምስኪንነትን
፲ኛ ጨዋ መሳይ ግን(passive aggression)፤ ሲገነፍሉ(ሲቆጡ) ራሳቸውን ጎድተው ለቤተሰብና ለማሕበረሰብ መትረፍ
፲፩ኛ ዐላማ ቢስነትን ….. ወዘተርፈ

ከተፈጥሮኣዊው ሚናህ የሚለይህን በራድነት ብሎም ምስኪንነት ለማስወገድ ይረዳህ ዘንድ አንዳንዶቹን ልጠቁምህ። ይኹንና በውጤቱ ራሱን ገዝቶ የሚመራ፣ ሌሎችንም የሚያስከትል፣የሚሄድበትንም የሚያውቅ ጠንካራ ወንድ እንጠብቃለንና የሚሠራበት/የሚያልፍበት መንገድ በፈተና የተሞላና ከባድ ነው።

ስንቅ አድርጌ የምሰጥህ ተፈጥሮኣዊ መረጃዎች ደግሞ በማር ያልተለወሱ ማጣፈጫም የሌላቸው መራር፤ ስትውጣቸው እስከዛሬ ከለመድከው የሚሻክሩ ደረቅ እውነቶች ናቸው። አንዳንዶቹም ልክ ነው ብለህ ሰምተህ ያንተ ካደረግጋቸው ጋር ሊጋጩብህ ይችላሉ።

ዱርዬነት፣ ሴታውልነት፣ በራድነት(ምስኪንነት) ከአባወራነት ጋር መንገዳቸው ለየቅል ነው። የቀደሙት መንገዳቸው በስሜት የሚነዳ፣ የራስ ምቾትን የሚጠብቅ፣ ትውልድንም ገደል የሚከት ነው።

የአባወራው መንገድ ግን ዐላማ ሰቅለህ የምትጓዝበት፣ ከጉዞህ ምቾት ይልቅ ፍጻሜህን አስበህ ዛሬን የምትደክምበት፣ ትውልድን ሀገርንም የምትታደግበት ነው።

በል ንሳማ ለአባወራነት ተሠራ ቀላል ልምምድ የለም ብዬሃለሁ። በእነዚህ ልጀምርልህ፦

፩ኛ በጠዋት መነሳት
፪ኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መሥራት

፩ኛ በጠዋት መነሳት
እንግዲህ አባወራ መኾን ፈልገህ የለ ፣ ስንፍናን፣ በራድነትን ገፈህ ልትጥል አይደል ……ይቆየን።

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *