ሚስቴ ልጆቼ አይሰሙኝም ስለማለት

አባቶቻችን ነገር በምሳሌ ጠጅ በብርሌ እንዲሉ እንመስለው እስቲ የአንድ ሃገር መራሔ መንግስት(ንጉስ፣ ፕሬዝዳንት፣ ጠቅላይ ሚንስቴር) ሲሾም ሀገር እንዲያስተዳድር ሰላም እንዲያሰፍን ነው። ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ ሰላም ይደፈርስና የተወሰኑ ክፍሎች ቢያምጹ፣ ንብረት ቢወድም፣ የሰው ነፍስም ቢጠፋ ይህ መራሔ መንግስት ምን ያደርጋል?

ለጠፋው ንብረትም ኾነ ነፍስ በይፋ ይቅርታ ይጠይቃል፣ አጥፊዎቹንም በሕግ ፊት ለማቅረብ ቃል ይገባል…..። ወይስ “ኧረ እባካችሁ አትረብሹ፣ በፈጠራችሁ ተለመኑኝ እምቢ ካላችሁ እኔ አገሪቷን ጥዬ መሄዴ ነው” ይላልን? ሌላ ሀገር ሄዶስ አገር ሲረጋጋ ይመጣልን? በጭራሽ። ይሄን ቢያደርግ ምን ያክል ለቦታው የማይመጥን ሰው መኾኑን ያሳብቃል።

ወንድሜ ላንተም እንዲሁ ነው። በተረዳኸው እውቀት በተቀበልከውም እምነት መሠረትነት ላይ ታንጸህ የሚስትንም ኾነ የልጆችን እምቢታ ተቋቁመህ የልዕልና ድንበርክን አስከብር። አንተ ቤትህን በስርዓትና በአግባብ ልትመራ ዝግጁ ነህ? ወይስ አልታዘዝ አሉኝ ብለህ ቤተመንግስት ቤትህን ሚስቴም አትሰማኝም ብለህ ዙፋን አልጋህን ትተህ ትሰደዳለህ?

ይህ ካንተ ይራቅ! አንተ እኮ ንግስት ሚስት ያለችህ ንጉስ የንጉስ ልጅ ነህ። የሀገር ግዛት ትዳርህን፣ ቤተመንግስት እልፍኝህን፣ ዙፋን መኝታህን ልታስከብር የተገባህ። እንጂማ ከውስጥም ኾነ ከውጭ ጓ ባለ ቁጥር (አለመግባባት ቢፈጠር) ቤትህን ጥለህ አንዴ ደጀሰላም፣ አንዴም ግሮሰሪ፣ አንዴ ወዳጆችህ ጋር እንዴት ታድራለህ?

ወዳጄ አንተ ልዑል ባለ ማዕረግ ኾነህ ሳለ እንደምስኪን ደጀሰላም አትደር፤ ቤትህንም ትተህ ከብርጭቆ ጋር አታንጋ፤ ምንም እንኳ ጊዜያዊ አለመግባባት ቢፈጠር በአንድ ሚስት ልትወሰን ሲገባህ ከኃጢያት መንደር ከስጋ ገበያም አታንዣብብ።

ሚስትህ ምንም እንኳ ስሜቷ በተለዋወጠ ቁጥር ንግግሯ ቢያስቀይምህም በፍጹም ግን ቤትህን ጥለህ አትውጣ። ይሄ በአንደኛ ደረጃ የፈሪ፣ በራሱ የማይተማመን፣ ጽናትም የጎደለው ሰው ምልክት ነው። ቤትህን ጥለህ መውጣትህ ላንተ “ነገሩን ያበርዳል” ብለህ ታስብ ከኾነ ተሳስተሃል ጭራሽ ትንቅሃለች እልሃለሁ።

ወንድሜ ከደረትህ ነፋ ከአንገትህ ቀና በል። በአባወራነትህ የያዝከውን ድንበር አስከብር። በስርዓትና በግብረገብ በራስ መተማመንም የታነጸውን የልዕልናህ ቅጥሩን ከግንባርህ ላይ ካለው ጽኑ እምነትና ቆራጥነት ጋር አገናዝቦ የማትደፈር መኾንህን ሲያቅ ሌላው ይሽሽ እንጂ አንተማ ለምን ወንድሜ?

አንተ እኮ በዓላማ ለዓላማ ወደዚህች ምድር መጥተሃል። ዘነጋኸውን?….
1 በዚህች ዐለም ስትኖር ዐላማ አለህ(purpose)
2 የቀደመው ዐላማህ በሕይወትህ ውስጥ ሚና ያሲዝሃል(role)
3 ቀዳሚው ሚናህ ደግሞ ልዕልና ነው(dominance)
4 ይህ ልዕልናህ ደግሞ ድንበር አለው(boundary)
5 ዐላማህ፣ ሚናህ፣ ልዕልናህ እና ድንበሩ ደግሞ ሁሌም የማይዛነፉ ስዩማን ናቸው(በቦታቸው)(consistent)
6 ከላይ ያሉትን አምስቱን ለመተግበር ደግሞ ጽናት ያስፈልግሃልና ትጉ ኹን(persistent)

ከቀላሉ ጀምር ከዚ በፊት የጠየኩህን ጥያቄዎች መለስ በልና እስቲ እያቸው። የልዕልና ድንበርህ በቤትህ ተንዷል ወይስ…?

የኔ ጀግና በወንድማዊ ፍቅር እወድሃሁና ጀግን!

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *