ምላስን ለሴት ጉልበትን ለወንድ

 

ሴቶቻችን ከእኛ ከወንዶች ይልቅስሜታዊ ማሕበራዊ መኾናቸውንና እነዚህንም ለማሳለጥ ይረዳቸው ዘንድ አንደበታቸውን እንደሚጠቀሙበት ገልጫለሁ።

የተለያዩ ዘመንኛ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት ሴቶች በቀን ውስጥ የሚናገሩት ቃላት በአማካይ ከወንዶች በ13,000 ይበልጣል። ወንዶች ወደ 7,000 የሚጠጉ ቃላቶችን ሲናገሩ ሴቶች ደግሞ ከ20,000 በላይ መናገራቸው ነው። ሙሉ መረጃውን ቀጥሎ ያለውን link ተጭናችሁ ማንበብ ትችላላችሁ።

https://www.dailymail.co.uk/sciencetech/article-2281891/Women-really-talk-men-13-000-words-day-precise.html

ይኼ እንግዲህ ከልጆቻቸው፣ ከሌሎች ከቤተሰብ አባላት ጋር ለሚፈጥሩት የትዳርን፣ የቤተሰብን የማሕበረሰብን የፍቅር ሰንሰለት ያጠነክሩበት የተሰጣቸው ጸጋ(ስጦታ) ነው።

አስረጅ
ሁለት ሴቶች ከሥራ ገበታቸው የአንድ ሳምንት እረፍት ወስደው፣ ተዝናንተው፣ ተጫውተው ወደ ቤታቸው ቢመለሱ ቤታቸው ከገቡ በኋላ ደግሞ ስልክ ተደዋውለው ለረጅም ሰዓት አብረው ያዩትን ስለጉዞአቸው፣ ስለገጠማቸው…. ማውራታቸው አይቀርም።

ጀግናው ወንድሜ!
ዛሬ ምንድነው የምታወራው ትለኝ ይኾናል?
እኔ ግን እልሃለሁ ተፈጥሮህን መርምር እወቅ ባንተም ኾነ በሚስትህ መካከል ያለውን ተፈጥሮአዊ እውነት ከእውቀት ማሕደርህ ስትከት ትዳርህ ጤናማ ይኾናል። እንጂማ ተፈጥሮን ክደህ ጸጋውንም ንቀህ በባዶ እውቀት ፍቅር ያሸንፋል እያልክ ብትዘፍን ኋላ ማላዘንህ አይቀርም።

ቀጠልኩ
ታዲያ ይኼን ኹሉ የቃላት ኮታ ሴቶች እንዴት ይጨርሱታል ብትለኝ?
አየህ በቀደመው ዘመን ቤተሰብ አባላቱ ብዙ ነበሩ። ልጆች አምስትና ከዚያ በላይ ሲኾኑ የባልና የሚስት ዘመዶችም ይኖራሉ።

በተጨማሪም ማሕበራዊ ሕይወቱ በራሱ የቤተሰብን ያክል የተቀራረበ ነበር። ታዲያ በዚህ በርካታ አባላት ባሉት ቤተሰብና ማሕበራዊ ሕይወት የተከበበች ሚስት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የሚሰማትን እያነሳችና እየጣለች ኮታዋም ተገባዶ ይመሻል። ምናልባትም ለአባወራው የሚተርፈው ለእግዜር ሰላምታና ጥቂት “ቁምነገረኛ” መረጃዎች መስጫ ብቻ ይኾናል።

አኹን እኔና አንተ ባለንበት ዘመን ግን ይኼን የወሬ ኮታ የሚያስጨርሳት የቤተሰብ አባልም ኾነ ማሕበራዊ ሕይወት የለም። ስለዚህ ቀን ሲሰሟት የነበሩት የተለያዩ ስሜቶችን አምቃ ማታ አንተ ስትገባ መተንፈስ ትፈልጋለች።

አስተውል! እነዚህ ወሬዎች በእኔ እና ባንተ ጆሮ ሲሰሙ ጭቅጭቅ፣ ንዝንዝ የሚባሉት ናቸው። ለእርሷ ግን ከቀን ውሎ ውጥረቷ የሚያሳርፏት፣ ካንተም ጋር ያላትን መግባባቱን የሚያጠነክሩላት ከድብርትም የሚገላግሏት ናቸው።

እኔ እና አንተ እነዚህን መስማት ለምን አንፈልግም? ምክንያቱም የእኔና ያንተ ጸጋ ደግሞ ለሰማነውን ችግር ፣ ጉድለት፣ ክፍተት ኹሉ መሙላት፣ መቆም ነው፣አለብን ብለንም እናምናለን። ይኼን ኹሉ ማድረግ ግን አይቻለንምና ጭቅጭቅ ንዝንዝ እንለዋለን።

የሚገርምህ ነገር ግን እርሷ የምትፈልገው መተንፈስን ካንተ የምትጠብቀው ደግሞ መስማትን ብቻ መኾኑ ነው።

አንድ ነገር ልብ በል እረሷ ስሜታዊ(emotional) ነችና የኹኔታ፣ የክስተት ትንሽ ትልቅ ሳይለይ ይሰማታል፣ እነርሱንም ማንሳትና መወያየት ትፈልጋለች። ይኽ ተፈጥሮዋ ነው።

አንተ እና እኔ ደግሞ ይበልጡን የአመክንዮ(logic) ሰዎች ነን ያየነው፣ የተከሰተው ነገር ኹሉ አይወራም፤ ይኼም ተፈጥሮአችን ነው። ነገር ግን የእኔን እና ያንተን ወሬ “ቁምነገር” የሴቶቹ ግን “የማይረባ ተራ ወሬ” እንለዋለን።

የብዙ ጭቅጭቆች ምክንያት
፩ኛ የእርሷ የወሬ ኮታ ላይ አለመድረስና
፪ኛ የእኔ እና ያንተ የሴቶችን ወሬ “እንቶፈንቶ” ማድረግ አና ቦታ አለመስጠት…

ታዲያ የሴቷ ምላስ ጉዳዩን ከጊዜ፣ ከቦታና ከኹኔታዎች ጋር አዛምዶ ማውራት እና ባልጠበቅከው መልኩ አዋዶ ማቅረብ ይቻለዋልና ግጭት ይፈጠራል። አንተ ደግሞ ግጭቱን መመከትም ኾነ መልስ መስጠት የሚችል ምላስ አልተሰጠህምና ጉልበትህን ትጠቀማለህ።

ተጠንቀቅ!
በዚህ ዘመን ጉልበትህን እስክትጠቀም ድረስ ያለው ግጭታችሁ(በእርሷ የምላስ የበላይነት የሚመራ መኾኑ እሙን ነው) “ጤናማ” ሲባል ልክ አንተ ጉልበትህን መጠቀም ስትጀምር ግን “ጥቃት” ይባላል።
ሴቷ ጸጋዋን አላግባብ ተጠቅማ ስጋህን ቦርቡሮ አጥንትህ ድረስ በሚሰማህ ንግግሯ ጤናማ ይባላል። አንተ በምላስህ አትመልስላት በእርሱ አልተካንህ(ስጦታህ አይደለም) የተሰጠህን ጸጋ ጉልበት ስትጠቀም ግን አጠቃሃት ይባላል።

ከዚያማ በፖሊስ ተቀፍድደህ፣ ራስህን ከቃላት ጥቃት በመከላከልህ በልጆችህ ፊት ተዋርደህ፣ ለዘመናት የደከምክበት ትዳር፣ ቤት፣ ተገፍትረህ ትወጣለህ። ይኼንን ስትፈራ ደግሞ እረሷ ያለአግባብ በምትጠቀምበት ምላሷ እየተደበደብክ እንደናቀችህ እየናቀችህ ትኖራለህ።

ይኽ ኹሉ ከመኾኑ በፊት፤ የተፈጥሮ ጸጋችንንም ባለማወቅ ከምንረግም(ሴትን በምላሷ ወንድን በጉልበቱ) ልዩነታችንን ለአንድነታችን ማዋል ተገቢ ነው።….. ይቆየን

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *