ምስኪኑን መታደግ

👉 ሀገራችንን ለመታደግ በግዑዛን ፍጥረት ላይ ሳይኾን በሰው ላይ መሥራት አለብን፤ ስለኾነም ትውልዳችንን መታደግ ግድ ይለናል።

👉 ትውልዳችንን ለመታደግ ደግሞ የእርሱን አስገኝ ማሕበረሰብ/ሕብረተሰብ መታደግ ግድ እንዲል።

👉ማሕበረሰባችንን/ሕብረተሰባችንን ለመታደግ እርሱን የሠሩትን እያንዳንዱን ቤተሰብ መታደግ ግድ ይላል።

👉 ቤተሰብን ለመታደግ ደግሞ እርሱን የሚቀድም ትዳር መታደግ ግድ እንዲል።

👉ትዳር የተሰኘውን የቀደመውን፣ ጥንታዊውን እና መሠረታዊውን ተቋም ለመታደግ ደግሞ እርሱ የታነጸበትን መሠረት በእውነት ዐለት ላይ ማነጽ፣ ማጽናት እና መጠበቅም ግድ ይለናል።

ይኽ የትዳር መሠረት የቤተሰብም ምሰሶ ደግሞ ወንድ ነው።

በአባወራ ልዩ ዝግጅት ማስተባበር(Abawera events organizer) አዘጋጅነት በአባወራዎች መድረክ የሚከተሉት ይዳሰሳሉ፦

👍 ወንድ ልጅ ተፈጥሮኣዊ ሚናውን እንዲያውቅ

👍 ለዓላማ(በርዕይ) እንዲኖር

👍 ይኼን ተፈጥሮአዊ ሚናውን እንዲወጣ

👍 የተፈጠረለትን ዓላማም እንዲያሳካ

👍 በተሰጠው(በጸጋው)ተጠቅሞ እንዲጠቅምበት እንዲያጎለብተውም

👍 ራሱን፣ ትዳሩን፣ ልጆቹን፣ ማሕበረሰቡን፣ ትውልዱንና ሀገሩን እንዲጠቅም እንዲታደግም ልምድ እየተለዋወጥን፣ እየተመካከርንና እየተወያየን ቁምነገር እንገበያለን።

አኹን በተዘጋጀው የመጀመሪያው መድረካችን እኛ ወንዶች ካለማወቅ፣ በስልጣኔም ይኹን በየዋህነት ራሳችንን እና ትዳራችንን እየጎዳብን ስላለው ምስኪንነትን ከአባወራው ጋር በንጽጽር እናይበታለን።

በቀጣይነትም ተመሳሳይ መድረኮችን እያዘጋጀን ቁምነገሮችን እንገበይበታለን።


የመድረኩ እድሜ እና አለባበስን የተመለከተ ፕሮቶኮል፦

👉 እድሜያቸው ከ21 ዓመት በላይ የኾኑ ወንዶች ብቻ መሳተፍ ይችላሉ

👉 አለባበስ ሸሚዝ ጨርቅ ሱሪ በቆዳ ጫማ

👉 ምስልም ኾነ ድምጽ መቅረጽ አይፈቀድም

ማሳሰቢያ፦ ጂንስ፣ ስኒከር፣ ነጠላ ጫማ፣ ቱታ አይፈቀድም

መግቢያ ብር 200 በ19465322 አቢሲኒያ ባንክ አስገብተው ደረሰኙን ይዘው ይምጡ ወይም በቦታው ከፍለው መግባት ይችላሉ።

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *