ምስኪን ስለሁለት ነገር፣ በሁለት ነገር ሁለት ጊዜ ይበሳጫል!

ሳተናው!

ምስኪን ብዙውን ጊዜ ብስጩ ነው። ነገር ግን የእርሱን ብስጩነትም ኾነ መበሳጨት ማንም አያቅበትም፤ አያቅለትምም። ሰውን ሁሉ ለማስደሰት፣ ከነዐመላቸው በመቀበል ይኽንኑ ዐመላቸውንም አጽድቆላቸውና አብሮኣቸው ለመኖር በሚያደርገው ጥረት ይበሳጫል።

👉 ምስኪን ስለሁለት ነገር ይበሳጫል

😠      ፍላጎቱ አይፈጸምምና
😠😠 አመድ አፋሽ ነውና

😠 ስለፍላጎቱ አለመፈጸም ይበሳጫል

ምስኪን ሰውን ለማስደሰት ካለው ቁርጥ ፍላጎት የተነሳ የራሱን ፍላጎት ይተዋል። ይኹን እንጂ ፍላጎቱን ሲተው ሳይጠይቁት ፍላጎታቸውን ያሟላላቸው ሰዎች “ሳልጠይቃቸው የምፈልገውን ያሟሉልኛል” ሲል ይጠብቃል። ነገር ግን እነዚያ ሰዎች የጠበቀውን ሳይሰጡት ይቀራሉና ይበሳጫል።

ምስኪንን ይኽ የተደበቀ አጀንዳው ሰዎችን ግራ ሲያጋባ እርሱንም ከሚፈልገውና ከሚወደው ነገር ሲያርቀው ይታያል።

አንድም ደግሞ ሰዎችን አስደስታለሁ ሲል የእርሱን ፍላጎት(የሚፈልገውን) ለሌሎች አሳልፎ ይሰጣልና ይበሳጫል። ከዚያ በኋላም ሰዎች እርሱን ፍላጎት የለሽ(ወሲብንም ጨምሮ) አልያም አንድ ነገር አጣም አገኘም ምንም የማይመስለው አድርገው ይቆጥሩትና ዘወትር ይነፍጉታል(የማያስፈልገውና የማይፈልገውም ይመስላቸዋልና)።

😠😠 ስለአመድ አፋሽነቱ (በተለይም  በሴቶች(በሚስቱ)) ይበሳጫል

ምስኪን በሰው ዘንድ አገኛለሁ እንደሚለው መወደድ፣ መከበርና መመስገን አያገኝምና ይበሳጫል። ሰዎች ኹሉ ወደ ራሳቸው ፍላጎትና የተሻለ ደረጃ የሚንጠላጠሉበት መወጣጫቸው እንጂ የስኬታቸው ወይም የትርፋቸው አጋር አያደርጉትምና።
ምስኪን ምንጊዜም አመድ አፋሽ ነው (ለሁልጊዜ የቀረበ ምንጊዜም ነው)።

👉 ምስኪን በሁለት ነገር ይበሳጫል

😠      በራሱ ይበሳጫል
😠😠 በሌሎች ይበሳጫል

😠 በራሱ ይበሳጫል
ምስኪን ምስኪንነቱ የፍቅር  እና የመንፈሳዊነት ጥግ ስለሚመስለው የሰዎችን ትኩረት፣ ፍቅር፣ አክብሮት ባጣበት፣ በጎደለበትና በሚፈልግበትም ቦታ ኹሉ አብዝቶና አምልቶ ይፈጽመዋል።

ይኹንና አጥብቆ ቢፈልገውም ከምስኪንነቱ የተነሳ ባለማግኘቱና ከስህተቱም ባለመማሩ ዘወትር በራሱ ይበሳጫል።

😠😠 በሌሎች ይበሳጫል
ምስኪን በተለይ ሳይጠይቁት በጎ በሠራላቸው፣ ሳይጠሩት በተገኘላቸው፣ ሳይለምኑት በሰጣቸው ሰዎች ይበሳጫል። “ለምን?” ቢሉ ምክንያቱም እርሱ በተደበቀ ፍላጎቱ “ሳልጠየቅ ለሰዎች እንደዋልኩት ሳልጠይቅ ይውሉልኛል” ብሎ፤ ሲቀርበት ግን በእርሳቸው ይበሳጫል።

👉ምስኪን ሁለት ጊዜ ይበሳጫል

😠     ከሰው ጠብቆ በቀረበት ጊዜያቶች ኹሉ ይበሳጫል
😠😠 እውነታውን ያወቀለት – እንደተካደ መጠቀሚያ እንደተደረገ በአጋጣሚ ያወቀለት
                                        – የዐለምን (የሴቶችን ጠባይ) ከሶስተኛ ወገን በሰማና በተረዳ ዕለት

😠 ምስኪን በድብቅ አጀንዳው (መልካም ባደርግ ያደርጉልኛል)ውለታ ጠብቆ በቀረበት ወቅት ኹሉ ይበሳጫል። ሲሰጥ ኖሮ ኖሮ ቸግሮት ያጣለት ከሰውም ጠብቆ ዘወር ብሎ የሚያይ ጠያቂ ባጣለት ይበሳጫል።

😠😠      እውነታውን ያወቀለት ይበሳጫል፦

😠😠😡 እንደተካደ መጠቀሚያም እንደተደረገ አጋጣሚ ያወቀለት
😠😠😡የዐለምን ደላይነት የሴትንም ስሜታዊነትና ሌሎችም ጠባዮቿን በተረዳ ጊዜ በስሕተት ያቃጠለውን ጊዜ ባሸሰበበት ወቅት ይበሳጫል።

ምስኪን ስለሁለተት ነገር፣ በሁለት ነገር፣ ሁለት ጊዜ ከተበሳጨ በኋላ ደግሞ እውነቱን ባወቀ ማግስት ከሚከተሉት ከሦስቱ አቋሞች አንዱን ይይዛል፦

😢 አዝኖና ተክዞ “እንደፈለገ ያድርገኝ” ብሎ በምስኪንነቱ ይቀጥላል… ተስፋ ይቆርጣል… ራሱንም ኾነ ሰውን ይጎዳል።

😈 በምስኪንነቴ ተጠቅመውብኛል ሲል በብስጭት በቤተሰቡ፣ በማሕበረሰቡ እና በሴቶችም ላይ የበቀል እርምጃ በመውሰድ ዱርዬ ይኾናል።

😎 ካገኘው እውቀት የተነሳ በራስመተማመኑን በማሳደግ ከዚኽ በፊት ራሱ ከሠራው ስሕተት ሌሎችም ከሠሩት በመማር አባወራ ይኾናል።

አባወራ?….. ይቆየን

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *