ምስኪን ካልኾንኩ ምን ልኹን?

ሳተናው!
ምስኪን በአንድ ባልጠበቀውና አስደንጋጭ በኾነ አጋጣሚ በምስኪንነቱ መጎዳቱን እስኪረዳ ድረስ አብዝቶ እና አምልቶ ምስኪንነቱን ይቀጥልበታል።

አልያም ደግሞ ተፈጥሮኣዊ እውነትን ፈልጎ እስኪያገኝ ምስኪንነቱ የሰውን ልብ የሚከፍትለት ክብርና መወደድንም የሚጨምርለት ይመስለዋል። ከእነዚኽ ከሁለት አጋጣሚዎች ባንዱ ታዲያ ከመራሩና ከጠጣሩ ነገር ግን ከተፈጥሮኣዊው እውነታ ጋር ይፋጠጣል።

ይኽ ፍጥጫም በአብዛኛው ከሚከተሉት ከሦስቱ(አንዳንዴም ከአራት) ማንነቶች አንዱን እንዲይዝ ያደርገዋል።

፩ኛ ምስኪን መታለሉ ሲገባው አንድም ደግሞ ተፈጥሮኣዊውን እውነታ ሲያውቅ ፍርሃት ይወርሰዋል፣ ጉልበቱ ይርዳል፣ ወኔው ይርቀዋል። ያየውን ማመን የሰማውን መቀበል ይከብደዋል።

“ለምን?” ብሎ ደጋግሞ ይጠይቃል። ይኹን እንጂ እውነታውን ለመረዳት የኾነውንም ለመቀበል አቅም ይቸግረዋል። ቅስሙ ይሰበራል፣ ሐሞቱ ይፈሳል ራሱንም ቀና የሚያደርግበት ወኔ ያጣል።

አንድም የጀመረኝ ይጨርሰኝ ከዚኽ ወዲያ ዋጋ የለኝም ሲል አንድም ደግሞ ለፍቅሬ ወሰን ድንበር የለውም ሲል በምስኪንነቱ ይቀጥላል።

ይኹን እንጂ አጋጣሚዎቹ ኹሉ ከበፊቱ እየከፉ የእርሱም ብስጭት እየበዛ ይኼዳል ። ሚስቱም ብትኾን ለእርሱ ያላት አክብሮት በፍጥነት እያሽቆለቆለ ይወርዳል። ይኽ ምስኪን ታዲያ በዚኽ ተስፋ መቁረጡ በሽታ መሸመቱ አይቀሬ ነው።

፪ ያለበት ማሕበረሰብ፣ ፖለቲካው፣ ጓደኞቹ፣ ሴቶቹ “መጠቀሚያ አድርገውኛል” ፣ “በየዋህነቴም ተጠቅመው እኔን ግን ጎድተውኛል” ሲል ዓመጸኛና ጋጠወጥ በመኾን ዱርዬ ይባላል።

ዱርዬ ከዚኽ በኋላ ማንንም አያምንም፣ ለማንምም የሚኾን የዋህነት አይገኝበትም። የራሱን ጥቅም ማስቀደሙ በራሱ ስሕተት ባይኾንም ይኼን ጥቅሙን ለማስጠበቅ ግን የሌሎችን መጨፍለቁ ግን ዱርዬ ያሰኘዋል።

ከፍተኛ የኾነ ወኔ፣ ተነሳሽነትና ድፍረት ተላብሶ የሚፈልገውን ነገር በግልጽ ይናገራል፣ ያገኛል፣ ይወስዳልም። በሴቶች ዙሪያም ቢኾን ጋጠወጥነቱ ምቾት ቢነሳቸውም እንኳ ወኔው፣ ተነሳሽነቱና ድፍረቱ ይማርካቸዋል።

ከምስኪኑም አንጻር ዕድሎችን፣ ስኬቶችን እና ሴቶችን የማየት፣ የማግኘት አጋጣሚውንም የመፍጠር አቅሙ ሰፊ ነው። ይኽ ዱርዬ ለማሕበረሰቡ ባሕል ኃይማኖት እና አሰሰተዳደራዊ ስርዓት ያለመገዛቱ ነገር ጋጠወጥ ቢያሰኘውም እርሱ ግን ትላንት “ግብረገብ” ኾኖ የመጎዳቱን ነገር እያሰበ ዱርዬነቱን አምኖ ይቀበላል።

፫ ትናንት ከሄደበት የስሕተት መንገድ ተመልሶ ተፈጥሮኣዊውን እውነት ተቀብሎ ራሱን በዐዲስ ማንነት የሚያንጸውን፤ ለዚኽም የትኛውንም ዋጋ በመክፈል የሚጓዘውን “አባወራ” ብየዋለሁ(ለእኛ ዐውደ ንባብ)።

አባወራ እውነትን ሐቅን መርምሮ ስሕተቱን ከልኩ ለይቶ ልከኛውንም ይዞ ይኼዳል። በትላንት የስሕተት መንገዱ ማንም ይምራው ማን የመረጠውን የወሰነው ራሱ፣ የኼደም እግሩ ነውና ለሥራው ራሱን ተወቃሽ ያደርጋል። ለውጤቱም ኃላፊነት ይወስዳል።

አባወራውን ከዱርዬው የሚለየው ዋነኛው፣ መሠረታዊውና ወሳኙ ነጥብም ይኼው ለሠራው ሥራ ኃላፊነት መውሰዱ ነው። እርሱ ለሠራው ሥራ እኔ “ሠራሁት” ሲል ትክክል ባይኾን እንኳ ይቅርታ ጠይቆ ይታረማል።

ወቅታዊ ትዝብት

አብዛኛው ወንድ አኹን ላይ ስንታዘበው (በተለይም ከሴቶች)ጋር ባለው ግንኙነት ምስኪን ነው። ከመራሩ እውነት ጋር ሲፋጠጥ ደግሞ የወጣለት ምስኪን አልያም ሕግ በላላበት ኹኔታ ዱርዬ ካልኾነም ሌላ ሴታውል የተባለ ማንነት ይዞ ብቅ ይላል።

በዚኽ ዘመን ስሜታቸውን ገዝተው፣ ሚናቸውን ተረድተው፣ ኃላፊነታቸውን አውቀው፣ ርዕይን ሰንቀው፣ በተፈጠሩበት ልክ ለተፈጠሩበት ዓላማ የሚኖሩ ጥቂቶች ናቸው።

እነርሱ የፓለቲካ ልኬት፣ ተፈጥሮን ለናቀ የጋራ ስምምነት፣ ከሰዎች በተለይም ከሴቶች ለሚገኝ ወዳጅነት ሲሉ ፍጥረታቸውን አይጨቁኑም፣ አይክዱም፣ አይቀይሩምም።

እነዚኽ ወንዶች ናቸው እንግዲህ በእኛ ዐውደ ንባብ “አባወራ” የሚባሉት።…….

ወቅታዊ ትዝብት

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *