ምስኪን-ወንድ በኮሌጅ …..

 

ምስኪኑ-ወንድ የኮሌጅ ቆይታው ከበፊት ሕይወቱ የሚለየው የበለጠ በመጎርመሱ ይህም የተቃራኒ ጾታ ፍላጎቱን መጨመሩ ነው። ይህ ፍላጎቱ ጤናማ ቢሆንም እንኳ አውጥቶ፣ደፍሮ መናገሩ ለእርሱ ትልቅ ፈተና ነው። ለሴቶቹ የሚያደርገውም እንክብካቤ ትንሽ ነፍስ አውቄያለሁ ከሚል ይመስላል ብዙም ሴቶችን እግር በእግር በመከተል መንከባከብቡን ይቀንስ እንጂ ፈጽሞ አይተወውም። ነገር ግን በቅርብ ዕርቀት መውደዱንም ሳይገልጽ ርቆም ሳይርቅ በህቡዕ ይንቀሳቀሳል።

አስረጅ፦ እስቲ ሰኒ እና ኃይሚ ቴዲ ስለተባለው ምስኪን ጋደኛቸው ሲያወሩ እንስማቸው።

ኃይሚ ፡ ሰኒዬ ቴዲ እኮ በጣም አሪፍ ልጅነው
ሰኒ ፡ አዎ ግን ኃይሚ ቴዲ አሪፍ ልጅ ከሆነ ታዲያ ለምን ጓደኛሽ አታደርጊውም ማለቴ ቦይፍሬንድሽ ……
ኃይሚ ፡ እንዴ ምን ማለትሽ ነው ቴዲዬ እኮ ለእኔ ወንድሜ ማለት ነው በጭራሽ አላስበውም በዛ ላይ የእኔ ታይፕ አይደለም።

በሥራ ዓለምም ሲሠማራ የተመሠከረለት ምስኪን ነው።ሰዎች ደስ ይሰኙ ዘንድ በእርሱም እንዳያዝኑ የማይፈነቅለው ድንጋይ የለምና አንተን ያገባች ሴት ታድላ ይሉታል።

ትዳር
ትላንት ሰዎች እሱን ያገባች፣አንተን ያገባች ሲሉ ቆይተው ዛሬ ሲያገባ ደግሞ ታድለሽ፣ የሚንከባከብሽ፣ የሚያስብልሽ፣ የሚጨነቅልሽ አግኝተሽ ይሏታለ። በእነዚህና እነዚህን በመሠሉ የወሬ አጀቦች ተከልለው ወደ ትዳር ይገባሉ፤ ብዙ ሲባልም ሰምተዋልና ከትዳራቸው ብዙ ይጠብቃሉ።ይህም ባይሆን ግን ወንዶች በአብዛኛው በተለይ በአሁኑ ወቅት ከትዳር በፊት ባንሆን እንኳ ስናገባ ምስኪን የመሆናችን እድል ሰፊ ነው። ከፍተኛ የሆነ የምስኪንነት ልምምድም እዚሁ ትዳር ውስጥ እናገኛለን።

ነገር ግን በሚደንቅ ሁኔታ የምስኪን ወንድ ትዳር በፈተና ይናጣል። እንደትላንቱ ሳይሆን ዛሬ ሚስቱ ምኪንነቱ ያማታል ወንዳወንድ አለመሆኑ ምቾት ይነሳታል እንዳትፈታው አለም ስለምስኪንነቱ ያጨበጨበችለት ሰው ሁሉ እርሱን አግብተሽ ታድለሽ እያለ አስተያየት የሚሰጥበት ነው።ስለዚህም ጭቅጭቅ፣ንዝንዝ እና የምንዴት ንግግር ቤታቸው ውስጥ ጎጆ ይቀልሳሉ

ለውድ ምስኪን- ወንድሜ ! ተፈጥሮህን ዘንግተህ ወንድነትህን ትተህ አልተፈቀርኩም እያልክ የቤትህን አባወራነት ለተቀማኸው ምስኪን-ባል ፤ ቤትህ በፈተና ሲናጥ በሰይጣን እያሳበብክ አትቀመጥ።

ይልቅስ ለቤቱ መሪ፣ለሚስቱ ወንዳወንድ ባል፣ ለልጆቹ አባት ለመሆን ተነስ ታጠቅ ተፈጥሮህን መርምር ተረዳ ሰዎችናዓለም የጮኹለትን ማንነት ሳይሆን ፈጣሪ የሰጠህን እውነት ፈልግ። እዉነት ብቻ አርነት ታወጣሀለችና።

እንግዲህ ትዳራችን ውስጥ ያለውን ምስኪንነት እያየን አባወራ የሚያደርገንን ማንነት እየተላበስን ወደፈት እንዘረጋለን።

ልብ በሉ ዓላማችን ከምስኪኑ-ባል በብዙ የራቀ፣ተፈጥሮን የጠበቀ ሚስቶቻችንን ዝቀው የማይጨርሱትን የፍቅር እርካታ መስጠት እርሱም የእኛ ደስታ ነው አሜን……..ይቆየን

እናንተስ ምን ትላላችሁ ….?

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *