ምስኪን-ወንድ ውሸታም ነው

ላለፉት ጥቂት ሳምንታት አባወራውን ወንድ ይገልጹታል ብዬ ባነሳኋቸው ርዕሶች ስር ስጽፍ ቆይቻለሁ። አሁን ደግሞ በንጽጽር ለማየት እንድንችልንና ራሳችንንም ከምስኪንነት ለማላቀቅ የምስኪን-ወንድን መሠረታዊ ችግሮች(ጠባዮች) እያነሳን እንወያያለን እናንተም ርዕሱን ይዛችሁ እንድትወያዩበት እጋብዛችኋለሁ።
ምስኪን-ወንድ የሚለው ስም በጣም አሳሳች ወይንም ተስማማሚ ያልሆነ ስም ነው። ምክንያቱም ምስኪን-ወንዶች ምንም ይሁኑ ምን ምስኪን ናቸውና(ምስኪን ተወዳጅ ነው በሚል እሳቤ)። እገሌ ምስኪን ነው ስንል በተለይ በአሁኑ ወቅት በሕብረተሰባችን ውስጥ ምን ያክል ተቀባይነት እንዳለው አይጠፋንም።
እነዚህ ወንዶች ምስኪን በመሆናቸው የሚወደዱ እና ጤናማ ሕይወት በተለይም ትዳር ይኖረናል ብለው ያስባሉ። እውነቱ ግን የተገላቢጦሽ ነው፦ሕይወታቸው የሚመርባቸው በተለይም ደግሞ ትዳራቸው ለዳኝነትም ሆነ ለሽምግልና በሚያስቸግር ፈተና የተሞላ እና የተትረፈረፈ ነው። በውጭ በሰው ሲታዪ እንደእነሱ ምርጥ የትዳር ጓደኛ የለም፤ ሚስቶቻቸውም ምስኪን-ባል ስላገኙ እድለኛ እንደሆኑ ተቆጥረው ከወዳጆቻቸው አድናቆት ይጎርፍላቸዋል።ይሁንና ልባቸው ወልቆ አልያም ውስጣቸው በግኖ ትዳራቸውን ለማፍረስ ማሕበረሰቡ በምስኪንነት ያጸደቀውን ባል ለመፍታት ሲያመነቱ የትዕግስታቸው ጽዋ ሲሞላም ሲፈቱ ይስተዋላሉ።
በተለይም ምስኪን-ወንዶች መንፈሳዊ የሆኑ ወይም የመንፈሳዊነት መገለጫው ምስኪንነት መስሏቸው ባለማወቅ ከተፈጥሮአዊው የወንድነት (እስከዛሬ ስናያቸው ከነበሩትና ከመሳሰሉት) ጠባያቸው አፈንግጠው ሲወጡ ችግሩ ያይላል መፍትሔውም ይፈትናል።

ለዛሬ ብዙዎቻችን የማናስተውለውን የምስኪን-ወንድን ኢ-ተአማኒነት (ውሸታምነት ስለው አትደንግጡ የራሱን ፍላጎት በተመለከተ ስሆነ) እናያለን። እስቲ ይሄን ምስኪን ልብ ገዝተን በእርጋታ እና በአስተውሎት ተፈጥሮአችንን ናፍቀን ስሜታችንን ለቀን እንየው።
ምስኪን-ወንድ በማሕበረሰቡ ውስጥ ከሚሰጠው ቦታ አንጻር ሰዎችን ለማስደሰት የማይቆፍረው ጉድጓድ የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም። ልብ በሉ እንግዲህ ይህ ሰው ሰዎችን ማስደሰት እንደ ግብ ሲያስቀምጥ የሚጓዘው ርቀት ረጅምና አድካሚ ነው። ሰዎችን ማስደሰቱ ባልከፋ እንዳውም ይበል የሚያሰኝ ይሆናል።ነገር ግን የእርሱን ስሜት፣ፍላጎት እና መሻት የት አድርጎት ነው? ብለን ስንጠይቅ መልሱ ያፍናቸዋል እንደሌሉት ይዋሻል ቢኖሩትም ከሌሎች ሰዎች ፍላጎቶች አንጻር ኢምንት እንደሆኑ ያወራል። ከዚህም የተነሳ እርሱ በሁኔታዎች ላይ ያለውን ስሜት እና ፍላጎት በግልጽ ቋንቋ ከመናገር ይልቅ ሰዎች ሊሰሙ የሚወዱትን ይናገራል። ይህ ታዲያ ፦ አይሆንም፣ አልችልም፣ አልወድም፣ አይመቸኝም እና የመሳሰሉትን የእምቢታ ቃላቶች ከእርሱ የቋንቋ መዝገበ ቃላት ያወጣቸዋል አልያም ያርቃቸዋል።
ሌሎችን አስደስታለሁ ብሎ ያፈናቸው ፍላጎቶቹ ታዲያ መቼም ሳይሟሉ ሁልጊዜም ጥያቄ ሆነው ይቀጥላሉ። ይህም ታዲያ ዘወትር ሰውን ለማስደሰት የሚጥር የሚለፋ ነገር ግን ለእርሱ የውስጥ ጥያቄዎች መልስ ያጣን ሰው ያስገኛል። በተለይም የትዳር አጋሩ እርሱን ለማስደሰትም ሆነ ከእርሱ ጋረ ስምም ለመሆን ትቸገራለች። በእርግጥ ብዙ መሻቶቿን እርሷ እንደምትፈልገው ቢመልስም በአብሮነታቸው ውስጥ ግን የእርሱ እንደጎደለ በዚህም የተነሳ ግልጽ ባልሆነ ቅሬታ ውስጥ ይወድቃል። “በሽታውን ያልተናገረ መድኃኒት የለውም” ይባላልና ይህ ሰው ከሚስቱ ለፍላጎቶቹ የሚመጥን መልስ አያገኝም ምክንያቱም ግልጽ አይደለምና ወይም ስሜቶቹን እና ፍላጎቶቹን በተመለከተ ይዋሻልና።
ግን ለምን ምስኪን-ወንድ በፍላጎቶቹ ዙሪያ ይዋሻል?
ስንል 1ኛ ከዚህ በፊት ያነሳነው በሁሉ ልወደድ ባይነቱ ነው።
2ኛ ግጭትን በመርሕ ደረጃ መሸሹ ነው። ይህን ብናይ ደግሞ ምስኪን-ወንድ ከመጀመሪያው ዓላማው የተነሳ ግጭትን ይሸሻል። በዚህም ምክንያት ሚስቱን አልችልም፣አልፈልግም፣አይሆንም እና የመሳሰሉትን ብላት ቅር ትሰኛለች ፣እንጋጫለን፣ እንጨቃጨቃለን ብሎም ሰላማችን ይደፈርሳል ብሎ ስሜቶቹን እና ፍላጎቶቹን ይሸሽጋል።….ይቆየን

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *