ምስኪን-ወንድ !!

ምስኪን:- 1 ያጣ የነጣ፣ የተቸገረ ደሃ
2 አሳዛኝ(ሰው፡እንሰሳ….)
3 የዋህ ይለዋል የ2001 የኢትዮጲያ ቋንቋዎች ጥናትናምርምር ማዕከል አማርኛ መዝገበ ቃላት።
ለኛ ጽሁፍ ሁለተኛውና ሦስተኛው በተለይም ሦስተኛው ይሰማማናል። እኔ ደግሞ በዙሪያዬ ያሉት ስለ ምስኪን ምን ይላሉ ስል ይህን አግኝቻለሁ።
ምስኪን ሰዎችን በነገሮች ሁሉ የሚያምን ለጠየቁት እና ለተጠየቀው ሁሉ ለራሱ ሳይሳሳ የሚያደርግ፤የእርሱን ፍላጎትና ዐላማ ለሰዎች ሲል የሚያዘገይ ወይም የሚሰርዝ። በእያንዳንዱ እንቅስቃሴው(ድርጊቱ)፣ንግግሩ ሰዎችን ላለማስቀየም በተቻለውም ደስ ለማሰኘት የሚሞክር። ይህ በተለይ ለሚወዳት ለፍቅረኛው፣ለሚስቱ ሲሆን ስንት እጥፍ እንዲጨምር አይጠፋችሁም።

ምስኪን-ወንድ ከሴቶች ጋር የሚኖረው ግንኙነት በሕይወት ደረጃዎች፦

1.ትምህርት ቤት (ሁለተኛ ደረጃ)

በትመህርት ቤት እያላችሁ ሴቶች የሚወዱት ከማህላቸውም የማይጠፋ ደብተር፣ቦርሳ፣ቦታ የሚይዝ የምታውቁት ወንድ አለ?
ሁሉንም ሁላችንም ባናደርገውም የተወሰኑትን ግን ብዙዎቻችን አድርገናቸዋል ። ይህ ምስኪን-ወንድ ታዲያ ምናልባትም ከአራትና አምስት ከዛም በላይ ለሚሆኑ ሴቶች የቅርብ ጓደኛ ነው። ለእነዚህ ሴቶች የቤትሥራ ይሠራል፣ያስጠናል፣ሲቀሩ ደብተር ከማዋስ ጀምሮ እስከመገልበጥ ፈተና እስከ ማስኮረጅ የደረሰ እርዳታ ይሰጣል። ከቤት ወደ ትምህርት ቤት ሲመጡ ይቀበላል፤ከትምህርት ቤት ሲወጡ ይሸኛል ታክሲ ይጋፋል ያሳፍራል፤ ከማንኛውም ጥቃት ለመከላከል ይሞክራል ከወንዶች ለሚሰነዘሩ ጥቃቶች ግን ዲፕሎማሲን ለመጠቀም ከዛ ካለፈም ለመክሰስ ይሞክራል እንጂ ግብግብ አይገጥምም። ብዙዎቻችን በተለይ ሴቶችን ማናገር የማንችለው ይህን ምስኪን-ወንድ ብዙ ሴቶች በዙሪያው ስለተገኙ እድለኛ አድርገን እንቆጥረዋለን።

ግን እኛ እንደምናስበው እና በምናስበው መልኩ ነውን?

ይህ ምስኪን-ወንድ ከእነዚህ ከከበቡት ሴቶች ውስጥ ለአንዷ በተለይ የፍቅር አመለካከት ቢኖረው ለእርሷ ለመናገር ሲታሽ አመታት ያልፋሉ ምናልባትም ሳይነግራት ሁለተኛ ደረጃ ያልቅና ኮሌጅ ይገባሉ። የጠየቁትን ሲያደርግላቸው እና ሲሆንላቸው ከነበሩት ሴተች መሐከል፣ ስለጠባዩ ሲያደንቁት ስለአሳቢነቱ ዘወትር ሲያወሩለት ከነበሩት አንዷን ፈልጎ ፍላጎቱንም በግልጥ እና በቆራጥነት አይናገርም። ስነግራት እምቢ ብትለኝስ፣ቅር ብትሰኝብኝስ፣ዓላማዋን ጥናቷን ባስታትስ፣ለዚህ ነው የቀረብከኝ ብትለኝስ……..አያለ የበዙ ምክንያቶች እየደረደረ የውስጡን በውስጡ አፍኖ ይኖራል።

በሌላ ጎን ደግሞ ከእነዚሁ ሴቶች መሐከል አንዷ ለእርሱ የተለየ የፍቅር ስሜት ቢኖራትም እርሷ በፈለገችው መጠን አይረዳትም።ሴት ነችና አትነግረውም። እርሱም ለመውደዷ መልስ ብሎ የሚያስበው ከሌሎቹ ሴቶች ጓደኞቿ ያልተለየ ይሆንና ተቀጣጥሎ የነበረው ስሜቷ ይከስማል።

በዚህ መሐል ታዲያ ወንዳወንዱ ወንድ ፣የአባወራ ወኔ ያለው፣ የሚፈልገውን የሚያቅ እርሱንም የሚጠይቅ በፈለገው ነገር የማይደራደር ከፈለገው መጠን ያነሰም ሆነ የበዛም የማይቀበል። እርሱ ይመጣል ይጠራታል የጨብጣታል ምስኪኑ እንደሚጨብጣት አይደለም ሰውነቷ ውስጥ መልእክት ማሰራጨት በሚችል የወንድ ሰላምታ ነው። ፍላጎቱን ልመናና ልምምጥ በሌለበት መልኩ ይገልጻል ይህም በመጀመሪያው ቀን ከሞላ ጎደል ሰኬታማ ያደርገዋል። ወሬው ጊዜው ቁጥብ ስለሆነ ለሌላ ቀን እንደሚደውል ገለጾ ስልኳን ይቀበላል።በቃ አለቀ።ምስኪኑስ? መመለሻዋን በናፍቆት ይጠብቃል ስትመጣም ልጁ እንዴት አይነት ራስወዳድ ወንድ እንደሆነና እንደተናደደበትም ይፎልላል፤ምን አለሽ ይላታል፤ ስልኬን አለኝ ፤ሰጠሽው? እንደውም(ተመስገን)ይላል በሆዱ። በፍጹም አይጠረጥራትም ምክንያቱም ምስኪን ስለሆነ።

እስቲ በእናንተም ተሞክሮ አዳብሩት ከራሳችንም ሆነ ከሰዎች ስህተት እንማር።

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *