ምስኪን ይለፋል “ዱርዬ” ያለፋል

ማስታወሻነቱ፦ ለሚስቱ ታማኝ ለኾነው ነገር ግን የዓለምን የእኩልነት ጩኸት ሰምቶና አምኖ ትዳሩን ለመሥራት ደፋ ቀና ሲል ሚስቱን ለሚያጣው፣ትዳሩ ለሚፈርስበት፣ ልጆቹም ለሚበተኑበት ምስኪን።

እንደሌላው ጊዜ ጦማሬ ኹሉ ይኽ ጽሑፍም አንተን ደስ የሚያሰኝ ውሸት የለውም። አኹን ያለውን የዓለምን እንደውም የአብዛኛውን ትዳር እውነታ ፍንትው አድርጎ የሚያሳይህ መራራ እውነት እንጂ። ያለፈውን ሳምንት “ሴት ልጅ በልቧ ጀግናን ታከብራለች” ጦማሬን ብታስቀድም ደግሞ ለዛሬው በመንደርደሪያነት ያግዝሃል።

ሳተናው!

አንተ የቤትህ(የሚስትህ) ራስ በምንጣፍህም ላይ ንጉስ ነህ። በጭራሽ እልሃለሁ ያስወድደኛል ብለህ ወደ ምስኪንነት ተራና ተርታ ማንነት አትውረድ። ከቤትህ ራስነት ከምንጣፍህም ንጉስነት ከሚያወርድህ ከየትኛውም የዓለም ጽንሰ ኃሳብም ራቅ እርሱ ትዳርህን የሚያሳጣህ ወደ ባርነት/ሞት የሚወስድህ  የስንፍናና የጥፋት መንገድ ነው።

ባለፈው ሳምንት የጻፍኩልህን አስተውል የሴትን ልብ ጀግና እንዲማርከው ። አንተ ደግሞ እግዚኣብሄር በሰጠህ (አካላዊ፣ አእምሮአዊና መንፈሳዊ) ጸጋ ተጠቅመህ ከቃሉም ትዕዛዝ ተነስተህ ይኽን ተፈጥሮኣዊውን ጀግንነትህን ልትጠብቅ፣ ልታሳድግና ልታጸና ይገባሃል።

በአጉል ስልጣኔ ተወስደህ ከኃላፊነትህ ብትሸሽ፣ ጸጋህንም በአግባቡ ባትጠቀም፤ ከዚህም የተነሳ ደካማዋ ሚስትህ  የዱርዬ ሲሳይ ብትኾን፤ ግዴታህን ያልተወጣህ አደራ በልም፣ ቃሉን የማታከብር የማትታዘዝም ብትባል እንጂ “ስልጡን” አያሰኝህም።

ፈጣሪህ አንተን በመሪነት፣ በራስነት ሲያስቀምጥህ ያንተንም ኾነ የእርሷን የስነልቦና ውቅር፣ የአእመሮ ይዘት፣ የአካልም ብቃት ስለሚያውቅ ነው። ወዳጄ እርሱ ባወቀ የሠራውን ስርዓት ፍቅር ገብቶኛል ስልጣኔም ተገልጦልኛል ብለህ አታፍርስ።

ቁምነገሩ ምን መሰለህ፦
ይኽቺ አመንዝራ ዓለም ለፈቃዷ ማስፈጸሚያ ይረዳት ዘንድ ክቡር የኾነው ትዳር እንዲቃለል፣ በእርሱ መፍረስም ትውልድ መረን እንዲወጣና ሀገርም እንዲፈርስ የምትጠቀምበት ሰውንም ወደ ኃጢያት ባርነት ወደ ሞትም አዘቅት የምትወስድበት ስኬታማ የኾነ ስትራቴጂዋ ነው።

ይኽንንም ባንተና በሚስትህ መካከል “እኩልነት” በሚል የፉክክር መንፈስ፣ ተፈጥሮኣዊ ሚናችሁን እንዳትይዙ የልዩነትን መርዝ በመርጨት ፈጣሪ ካቀደላችሁ ሕይወት ታርቃችኋለች።

ጭብጡ፦ ዓለም ምን ብትጮህ አንተ ግን ሚስትህንና ልጆችህን ዓላማ ሰቅለህ፣ ወደ እርሱ የሚጓዙበትንም የቀና መንገድ መርጠህ መምራቱን አትተው። ከዚህ ሚናህ ብትዘናጋ ግን ሴት ልጅ ስሜቷን የሚገዛ፣ ደመነፍሷን የሚመራና ፈቃዷን አውቆ ለሚፈጽም ልቧ ይሸነፋልና ሰውነቷም ይማረካልና ብዙ መዘዝ ያስከተለ ማጣፊያውም ያጠረ ክፉ ቀን ላይ ትወድቃለህ።

ዐለም እንደምትዋሽህ ትዳርህን የገነባህ፣ ቤትህን የሠራህ ሚስትህንም ያስደሰትክ መስሎህ በእኩልነት ዝባዝንኬ ተተብትበህ ከሚናህ ርቀህ ደፋ ቀና ብትል ሚስትህ የሚያስፈልጋትን ቁሳዊ ነገር ብታሟላላት እንጂ ስሜቷን መግዛት፣ ገላዋንም መማረክ አትችልም።

ምክንያቱ ደግሞ አንተ ተፈጥሮአዊ ቦታህን ዓላማዊ ሚናህን ዘንግተህ መምራት ሲገባህ መመራት፣ መወሰን ሲኖርብህ መማከር፣ ድርጊት ሲጠበቅብህ ማስፈቀድ የምታበዛ ምስኪን ኾነሃልና ነው።

በዚህን ጊዜ ነው እርሷን መምራት፣ በምርጫዎቹ መወሰን፣ የፈለገውንም ማድረግ ለሚቻለው ወንድ የምትሸነፈው፣ ገላዋም የሚማረከው። ይኽ ወንድ ደግሞ ይሉኝታ የሌለው፣ ስነስርዓትንም የማያውቅ ለማሕበራዊም ኾነ ኃይማኖታዊ እሴቶች  ቦታ የሌለው(ዱርዬ) ነው።

ሳያማክር የመወሰን፣ የፈለገውን በግድም ቢኾን የማድረግ፣ ለማዘዝ የማይሰቀቅ ነውና አንተ ያዳፈንከውን መመራት የሚፈልገውን ሴትነቷን አቀጣጥሎ ስሜቷን ገዝቶ፣ ልቧን አሸንፎ ገላዋን ማርኮ ታደርገዋለች ብለህ በጭራሽ የማታስበውን ያደርጋታል/ያስደርጋታል። 

አንተ በመኝታ ቤታችሁ፣ ያውም በጭለማ ውስጥ፣ ለዚያውም በብርድ ልብስ ተሸፍናችሁ የማታደርጉትን ከዚህ ሰው ጋር በአጉል ቦታ፣ በ”አጉል” መንገድ ታደርገዋለች። ለዚህ ደግሞ ዋነኛው ተጠያቂ አንተው ነህ ሲጀመር መምራት አለመቻልህ አልያም መታዘዝን የተማረች አለመምረጥህ። 

ራስህን ካላረምክ በዚህም ከቀጠልክ አንተ ትለፋለህ፣ ሴታውሉ ይላፋታል ዱርዬው ያለፋታል…..  በመጨረሻም…..ይቆየን
ሴታውሉን የጨመርኩበት ተጨማሪ ኃተታ email address ለላካችሁልኝ ብቻ አደርሳለሁ።

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *