ምስጋና

ደረጃ ዝርዝር የማይወጣለት አንድዬ በፈተና ውስጥ ትግስትን ሰጥቶ የሚያስተምረኝ “ክብርና ምስጋና ለዘልዓለም ለአንተ ይኹን” እለዋለሁ።

በቀጥታ
፩ኛ አባት
አኹን ላለሁበት ማንነት የስነሥርዓትን ሀሁ ያስተማረኝን አባቴ ከልብ አመሰግነዋለሁ።

ስነሥርዓትን ዐለም “አምባገነንነት፣ ጭቆና” በምትልበት በዚህ ዘመን ፈተናዎቹን ተቋቁሞ መክሮ፣ ገስጾና ቀጥቶ አሳድጎኛል። ትላንት ላይ መልካም ሰው ጥሩ ዜጋ እንድኾን ቀጥቶኛልና አመሰግነዋለሁ።

ዛሬ እኔም በተራዬ አባት ስኾን እንደ ዐለም “ስልጣኔ”(ስንፍና) ሳይኾን በርሱ ፈለግ ልጆቼን መክሬ፣ ገስጬና ቀጥቼ አሳድጋለሁ።

በተዘዋዋሪ
፪ኛ ሚስት

*አባወራነትን በተሳሳተ መንገድ ተረድቼ የወጣለት ምስኪን ኾኜ ባገባትም ወደ አባወራነት ከፍታ እንድወጣ በእምቢታ ውስጥ ወደ ልከኛው ማንነት የምትመልሰኝን

*እንደጠላት ሀሳብና ምክር ሳይኾን ከንክር ምስኪንነት እስክወጣ፣ ያስለመድኩትም ጠባይ ሲለወጥ የታገሰችኝን
.
እህታለም

ቃ..ላ..ቶ..ች ያ..ጥ..ሩ..ኛ..ል

፫ኛ እናንተን
አባወራን ስጀምረው አብራችሁኝ ለነበራችሁ በኋላም የተቀላቀላችሁ ኹሉ እወዳችኋለሁ።

ወንዶቻችንን ምሉዕ በኩልኼ(ብቁና ሙሉ ዜጋ) ማድረግ እንጂ ልቅ ኾኖ ሰነፍ፣ ስነሥርዓተ የለሽ፣ራስ ወዳድና ግድየለሽ ወንድ ማሳደግ ነገ ሙሰኛ፣ ዘረኛ፣ ግለኛ ትውልድን መፍጠር ነው።

ይኽም ሲኾን ታዲያ ወንድን ከቤተሰብ፣ ከማሕበረሰብ፣ ከኃይማኖትና ከሀገር መሪነት ማውጣት ትውልድን መግደል፣ ሀገርን ማጥፋት፣ የሰው ዘር፣ የፈጣሪንም ዐላማ መገዳደር ነው።

ይኽንንም የወንዶች ስብዕና ወደ ተፈጥሮኣዊውና ልከኛው ማንነት ለመታደግ አባወራ ገጽን በኹሉ የደገፋችሁትን ምስጋናዬ ወደር የለውም።

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *