ርዕይህን ጠብቅ

ሳተናው!

(ማሳሰቢያ፦ ርዕይ እና ሕልምን ለገለጻ ስል አንዱን ባንዱ እየተካሁ ልጠቀምበት እችላለሁና የንባቡን ዓውድ እያስተዋልክ ተከተለኝ)

ርዕይ ሲኖርህ የመኖር ተስፋ አለህ። የተፈጠርክበትን ምክንያት፣ የኑሮህን ትርጉም፣ የሕይወትህም ማጠንጠኛው እርሱ ነው። ከዚህም የተነሳ እያንዳንዷን ቀን ልትሠራባት፣ ልትለወጥባትና ልትለውጥባትም ትተጋለህ። ዘወትርም ርዕይህን እውን ስለምታደርግበት፣ እርሱንም የምትኖርበትነ መንገድ ታስሳለህ።

ነገር ግን በዚህ የጥረትህ ኺደት ውስጥ በርካታ እንቅፋቶች/ፈተናዎች ቢመጡም ርዕይህ ግን አንተ እስካልጣልከው ድረስ ማንም የማይቀማህ፣ ካንተም የማይለይ ሀብትህ ነው። አንተ ጤናማ አእምሮ እስካለህ ድረስ ርዕይህን ማወቅ፣ መጠበቅ እርሱንም መኖር ይጠበቅብሃል። አንዴ ርዕይህን ለይተህ ካወቅከው እርሱን ለማሳካት ራስህንም ኾነ ግብዓቶችህን በስነስርዓት አቅደህ በመኖር ብቻ ወደ እውን ታደርገዋለህ።

አለበለዚያ ግን በብዙ ደመወዝ ተቀጥረህም ብትሠራ ኑሮህን ታቀልበት፣ የዕለት አስቤዛም ብትገዛበት እንጂ ውስጥህን አያሳርፍልህም።

ሳተናው!

እንዲህ የተረዳኸውና የምትኖርለትን ርዕይ ስታውቀው ታዲያ ልትጠብቀው እና ልትንከባከበው ይገባል፦

፩ኛ በዙሪያህ ካሉ ሰዎች ጠብቀው
በዙሪያህ ያሉትን ሰዎች ሚስትህን ጨምሮ በውስጥህ ልዩ ቦታ ትሰጣቸዋለህና አስተያየታቸው አንተ ላይም ኾነ ርዕይህ ላይ ተጽዕኖ ማሳደሩ አይቀርም። ይኹንና አቅፈሃት የምትተኛት ሚስትህ እንኳ ብትኾን ሕልምህን ብትነገራት እንጂ እንደ ሲነማ አብራህ አታየውምና ይኹንታና ጭብጨባን ከእርሷ እስክታገኝ አትጠብቅ።
ይልቁንስ ላየው ርዕይ፣ ለታመነለት ዓላማ የሚኖር፣ የሚሄድበትንም የሚያወቀው እርሱ፤ ሚስቱ የቤት-ሥራው፣ የኑሮው ማዕከል፣ የሚኖርላት ዓላማው፣ ከእርሷ በቀር “የሕይወትን” ትርጉም ከማያውቀው ምስኪን በአያሌው ተመራጭ ነው።

ስለዚህም ስለ ርዕይህ አጉል ስልጣኔ ይዞህ ከሚስትህ ጋር “ይኹን አይኹን”፣ “ይቅር ይምጣ” እያልክ እሰጣገባ አትግባ፤ ምክንያቱም ፦
? ብታስተውህ አንተ “እሰማታለሁ” ብለህ ታስባለህ፤ አልያም “ይሰማኛል” ብላ “ዋጋ ትሰጠኛለች” ብለህ ተስፋ ታደርጋለህ። እውነታው ግን ራስህን ችለህ የማትቆም፣ በዓላማህ የማትጸና እና ልፍስፍስ መኾንህን ልቧ ማረጋገጡ ነው።(አፏ ግን መቼም ይኼንን አይነገርህም)

ማንም ሰውም ስለ ርዕይህ “ከንቱነት”፣ አልያም ሊሳካ “ስላለመቻሉ” እንዲነገርህ አትፍቀድለት።

አስተውል! ለዕለት ፍጆታህ የምትሠራው ሥራም ኾነ ለብቸኝነትህ ታግዝህም ዘንድ ያገባሃት ሚስትህ፣ እንዲሁም በኋላ ዘመንህ ያፈራሃቸው ልጆች፦ የኑሮህ ዓላማዎች፣ የሕይወትህ ርዕዮች አይደሉም፤ አይኾኑምም!

፪ኛ ርዕይህን ከዓለም ከምትሰማው ክፉ ጠብቀው

ሳተናው!
ዐለም የሰውን ልጅ ከተፈጠረለት ዓላማ፣ ከተሰጠው ርዕይ፣ ከተጠራበት ሕይወት ቢቻላት በብልጭልጭነቷ አታላ አለበለዚያም በኑሮ ፈተናዋ አስገድዳ ማስቀረት ባይኾን እንኳ ማዘግየት ልማዷ ነው።

ስለዚህም ስለምትሰማቸው ነገሮች ተጠንቀቅ። እነርሱ ፈሪ፣ ሰበበኛ፣ ሕልመኛ ብቻ፣ አድርገው ይሰልቡሃልና ነው። በተቻለህ መጠን ርዕይህን እውን የምታደርግባቸውን ጥበቦች ለመስማትና ለመተግበር እንጂ የዓለምን ልብ ሰቃይ እንቶፈንቶም የኾነ ወሬ ለመስማት ቲቪ ስር አትጣድ።

አለበለዚያ ግን ከርዕይህ ይለዩሃል፣ ወኔህን ይሰልቡታል የሥራ ወኔህን ብቻ ሳይኾን ሚስትህን ከፍላጎቷ የምታሳርፍበትን የወንድነት ወኔንም ጭምር እንጂ። ይኽ ደግሞ የዘመናችን ወንዶች ትልቁ በሽታ መኾኑ መርምረህ ድረስበት።

ሳተናው!

ትርጉም ያለው ኑሮ መኖር ትፈልጋለህን? ርዕይህን እወቅ፣ ጠብቅ ራስህንም ለሥነ-ስርዓት በማስገዛት እውን አድርገው።

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *