ሰው ሠራሽ ቅርፊት

እውነት የተጫነብን ቅርፊት አለን?
በዚህ ዘመን ባለንበት ነባራዊ ኹኔታ በአብዛኛው ወንድ ልጅ ከተፈጥሮው ውጪ ማሕበረሰቡ ወይም የማሕበረሰቡ የተወሰኑ አካላት በሠሩለት ቅርፊት(ቅርጽ) ውስጥ ይኖራል። ከዚህ ውጪ ከኾነ ረባሽ፣ በጥባጭ፣ ዱሩዬ….. የተሰኙ ስሞች ይሰጡታል።

ይኽ ቅርፊት ተፈጥሮኣዊ እውነትን ያልተከተለ የሰው ልጅ (በተለይም ወንዱን)በተፈጠረበት ብቃትና ልዕልና እንዳይጠቀምም ኾነ እንዳይጠቅም ያደረገ ነው።ሰዎች በግልም ኾነ በማሕበር ከራስወዳድነታቸው የተነሳ እውነት በሚመስል ውሸት ቀምመው የሚሠሩት በእርሱም ውስጥ እንድንኖር የምንገደድበትም ቅርጽ ነው።

ይኽ እኛን የማያውቀንና የማይወክለን ቅርፊት ታዲያ ከውልደት ጀምሮ እስከሞት እኛ(ወንዶች) እንኖርበት ዘንድ ግድ የምንባልበት ተፈጥሮኣዊ ባሕርያችንን መረዳትም የተሳነው ነው።

በተለይም አኹን አኹን የአባትና የልጆች ግንኙነት በሳሳበት ዘመን አብዛኛው የመዋለ ሕጻናትና የመጀመሪያ ትምሕርት ቤት(በቅርቡ የኹለተኛ ደረጃ ትምሕርት ቤትና የመሰናዶዎቹም) አስተማሪዎች ሴቶች በኾኑበት ዘመን ያይላል። ይኽ ታዲያ ወንዶቹን ተማሪዎች እንደሴቶቹ አርፈው እንዲቀመጡ፣ እንዳይፎካከሩ፣ እንዳይላፉ፣ እንዳይደባደቡ ይኽም ድርጊታቸው “ረብሻ” ተብሎ እነርሱ ደግሞ “ረባሽ” እንዲባሉ ያደርጋል። “ረብሸው” ቢገኙ ደግሞ ቅጣቱ ቁንጥጫ ወይም ግርፋት ሳይኾ መገለል ነው(መገለል ከፍተኛ የስነልቦና ጉዳት ያመጣል)።

እስቲ ለዛሬ በሕብረተሰባችን ወይም በሕብረተሰቡ የተወሰኑ አካላት ተቀርጾ(ተሠርቶ) እንድንኖርባቸው ከተገደድንባቸው ሰው ሠራሽ ቅርፊቶች የተወሰኑትን እንይ፦

ልጅነት
👉በልጅነታችን ከሴቶች ልጆች እኩል አርፈን ተቀምጠን በአሻንጉሊት እንድንጫወት ስንገደድ፤ መሯሯጣችን፣ መላፋታችን፣ መጣላታችን፣ መደባደባችን ረባሽነት እንደኾነ
👉አርፎ ቁጭ ብሎ TV የሚያየውን ጨዋ ብሎ በፍጥነት የሚሯሯጠውን ቀዥቃዣ ማለት
ምሳሌ፦ እኔ እኹድ እኹድ ልጆቼን(ወንድና ሴት) ይዤ ኳስ እንጫወታለንና ኹሌ እናቱ የምታዘንጠው የጎረቤታችን ልጅ የልጆቼ ጓደኛ አለ ና ኳስ እንጫወት ስንለው ኧረ እኔ እቆሽሻለሁ ይላል። በምትኩ ቁጭ ብሎ video game ሲጫወት ይውላል።
👉 መደባደብ በጭራሽ አይቻልም ብትመቱ እያለቀሳችሁ ትኼዱና ለመምሕራን መናገር እንጂ
👉 መቆጣት፣ መጣላት፣ መደባደብ የመጥፎ(የባለጌ) ልጅ ጠባይ እንደኾነ
👉የምትጫወቱበትን እቃ ማወላለቅ፣ መፈታታት ጥፋት እንደኾነ

ጉርምስና
👉ሕይወታች በቀለም ትምሕርት ብቻ እንደሚለወጥ
👉ጥሩ ነጥብ አምጥታችሁ ኮሌጅ ገብታችሁ፣ ሥራ ተቀጥራችሁ፣ አግብታችሁ፣ ወልዳችሁ ቤት/መኪና ገዝታችሁ …. መኖርን የኑሮ ጥግ ማድረግ
👉የውስጥ ፍላጎታችንን የተገነዘበ የጎንዮሽ ሙያ አለማዳበር
👉ሴትን ለጓደኝነት መጠየቅ ከትምሕርት፣ ከመንፈሳዊ ሕይወት ከዓላማ የሚያሰናክል እንደኾነ
👉በገባችሁበት ማሕበር፣ በመሠረታችሁት ቡድን፣ በተሰባሰባችኹበት ቦታ ኹሉ ችሎታን ሳይኾን የጾታ እኩልነትን በቁጥር ማስጠበቅ(እንደዛሬው ሹመት) ምፅ..

ትዳር
👉አግብታችሁ መኖር ስትጀምሩ መስከን እንዳለባችሁ፤ እንደጉርምስናችሁ ፍጥን ፍጥን ማለት እንደሌለባችሁ
👉ከወለዳችሁ በኋላ (በተለይ የሴቷ) የወሲብ ፍላጎት እንደሚቀንስ ይኼንንም ወንዶች እንዲረዱ
👉ወሲብ ቅጽበታዊ ሳይኾን በጠረጴዛ ዙሪያ በተለይም የሴቷን ፍላጎት ከግምት እንዲከት
👉ሴቶች በጠቅላላው ከወንዶች ያነሰ የወሲብ ፍላጎት እንዳላቸው
👉 በትርፍ ጊዜያችን የተለያዩ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ከመሥራት፣ ራስን የሚያሻሽሉ ተግባሮች ላይ ከመሳተፍ ጉንጭ አልፋ የኾኑ ጉዳዮችን ይዞ በማሕበራዊ ሚዲያም ኾነ በየሻይቤቱና ጠላቤቱ መቀመጥ
**** እስፖርት እንሥራ ስለው ሰውነቴ ላብ ላብ ይላል ብሎ ተበጣጥሮ ተሽሞንሙኖ ፊልም ሲያይ የሚውለው ጓደኛዬ ትዝ አለኝ
👉ከትዳር በኋላ መወፈር(ቦርጫም) መኾን “ሙሉ ሰው” የመኾን ምልክት እንደኾነ
👉”ሙሉ ሰው” ከኾንክም በኋላ ከኃይለኝነቱ፣ ከወሲብ ፍላጎቱ፣ ከተፎካካሪነቱ መገታት እንዲገባ ምክንያቱም እነዚህ የወንድነት ደካማ ጠባዮች እንደኾኑ
👉በቤት ምሥረታህላይአስፈለገህም አላስፈለገህም ሌሎች እንዳሟሉት የቤት ዕቃህን ማሟላት እንዲገባህ
***የሚያሳዝነው ነገር ከምትሰበስባቸው እቃዎች መካከል ላትጠቀምባቸው ገንዘብህን ይዘው መቀመጣቸው ሳያንስ አንተን(አእምሮህን) የማደነዝ አቅም ባላቸው TV(satellite dish) መለከፍህም እንጂ
👉በእነዚህ ትውልድን አደንዛዥ በኾኑ የቤት ውስጥ መሣሪያዎች ደግሞ ከተለያዩ ግድየለሽ ተቋማት የውሸት መዓት ሌትና ቀን ሲወርድብንና ስንጋተው…
👉ጾታዊ ግንኙነት በተለይም ትዳር 50/50 ነው የሚሉት ወፍ ዘራሽ ትምሕርት
👉ወንዶችና ሴቶች እኩል ናቸው የወንድና የሴት ብሎ ሥራ፣ ጨዋታ፣ ስፖርት፣የጸጉር አበጣጠር፣ ትምሕርት፣ አለባበስ፣ አካሄድ፣ አቀማመጥ… ወዘተርፈ የለም
ጨምሩበት እናንተም

የራሴ እና የቤተሰቤ እድገት ይመለከተኛል፣ የትውልድና የሀገሬም ነገር ያሳስበኛል የምትል ከኾነ እነዚህንና እነዚህን በመሳሰሉት ቅርፊቶች መታጠርህን ማስተዋል አለብህ። ከዚያም ቅርፊቱን ስትሰብር ያላየኸውን ማንነትህን፣ ያልተለማመድከውን አቅምህን የተፈጥሮ ጸጋህንም ጥግ ታገኛለህ።

ቅርፊት ሠበራ…… ይቆየን

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *