ሴታቆርቋዥ(Feminism)፣ ወሲብ እና የወንድ አልጫነት

የሴታቆርቋዡ እሳቤ (Feminism) በትዳር ሕይወታችን በተለይም በመኝታ ቤት የፈጠረው ተፈጽዕኖ በአደባባይና በእልፍኝ ከፈጠረው ተጽዕኖ በአያሌው ይልቃል። እንዲኽም ይገለጻል፦

፩ ሴቶች በትዳር ውስጥ እንኳን ቢኾኑ ከመቻቸት የመነጨ ቅጽበታዊ ሳይኾን በድርድር እና በንግግር የጸደቀ ተራክቦ እንዲፈጽሙ ያበረታታል።
፪ ያ ከአደባባይ ጀምሮ በእልፍኝ ተከትሎ የመጣው ያለመረታት፣ ያለመሸነፍ ጠባይ መኝታ ቤትም ተከትሏት ገብቶ ራሷን ሙሉበሙሉ ለባሏ እንዳትሰጥ ይገድባታል። በዚኽም ምክንያት ከተራክቦው ልታገኝ የሚገባት የእርካታ ጥግ ሳታገኝ ትቀራለች። አንቺው ታመጪው አንቺው ታሮጪው ነው ነገሩ።

አኹን ደግሞ የሴታቆርቋዡ እሳቤ(Feminism) ወንዶችን እንዴት አልጫ እንዳደረጋቸው (እንዳደረገን የዛሬን አያድርገውና) እንይ።

ሴታቆርቋዡ (Feminism) በአደባባይ፣ በእልፍኝ እና በመኝታቤት ውስጥ ያሰረጸውን የተሳሳተ እና አፍራሽ አመለካከት የዛሬው ወንድ ልጅ ሲቀበለው አልጫ(የወጣለት ፈሪ) ይኾናል። የሚገርማችሁ ይኼን አልጫነቱን ደግሞ መልሰው የሚጠየፉት ራሳቸው ሴቶቹ መኾናቸው የችግሩን መፍትሔ ያርቀዋል።

የወንድ ልጅ የአደባባዩ አልጫነት

ወንድ ልጅ ሴትን የሚተዋወቅበትና የሚያናግርበት መንገድ “ጾታዊ ትንኮሳ” በሚባልበት ዘመን ሴትን ደፍሮ መቅረብ፣ ጓደኝነትም መጠየቅ ወይም ደግሞ አለባበሷንና ስነ ስርዓቷን አድንቆ መተዋወቅ ይፈራል። ለምን ይፈራል? ይኽ ዐይነቱ አቀራረብ “ሌላ ትርጓሜ ቢያሰጥብኝስ ጨዋነቴን ነጥቆ ዱሩዬ ቢያስብለኝስ” ብሎ ያስባልና ነው።

የቢሮ ሠራተኛ ብትኾን ጥሩ ለብሳ፣ መነጽር አድርጋ ፊቷን ቅጭም ብታደርግ እርሱ ሊቀርብበት ላሰበው ጨዋታ ጊዜ የሌላት ለቁም ነገሩም ቢኾን እድል እንደማትሰጠው ያስባል። ከራስ ፀጉሯ እስከ እግር ጥፍሯ በነጠላ ተከናንባም ያያት መንፈሳዊም ብትኾን የእርሱ ፍላጎት እርሷ ውስጥ ያለ አይመስለውም እንዳውም ጥያቄው ከመንፈሳዊ ሕይወቷ የሚያደናቅፋት ይመስለዋል።

ስለዚህም ትኾነኛለች የሚላትን ከቤቱ ወጥቶ በአካል ከመፈለግ ከጓደኞቹም ጋር ኾኖ ከማፈላለግ ከመተዋወቅም ይልቅ በማሕበራዊ ድረገጹና “እናገናኛለን፣ እናጋባለን” ከሚሉት ዘንድ መሸመትን ይሻል።

የወንድ ልጅ የዘመኑ የእልፍኝ አልጫነት

እዚህ ደግሞ የቤቱ መሪ አስተዳዳሪ እርሱ ቢኾንም “ስናገር አልሰማም” አልያም “አላስፈላጊ መልስ ይሰጠኛል” ይልና የገጠመውን ተግዳሮት ፊትለፊት ከመጋፈጥ ይልቅ ቤቱን ትቶ ይወጣል። ምክንያት ስትሉት “ጭቅጭቅ ሰለቸኝ” ይላል፤ እውነታው ግን ፊትለፊት መነጋገር ይፈራል። ሚስቴን ተቆጥቼ “ማስቀየም አልፈልግም” ይበል እንጂ እውነቱ ግን “ጥላኝ ትሄዳለች ” ብሎ ይሰጋል፤ ከግጭትም ይርቃል።

እናት አባቱ ቤት ከእህቱ ጋር ያደርግ እንደነበረው እዚህ ደግሞ ሚስቱን አይኗን እያየ እቅጩን መነጋገር፣ በጠንካራ ቃላትም መመላለሱ ወደ አካላዊ ግጭት እንዳያመራ ይቆጠባል፤ ምክንያቱም እርሱ “የተማረ ዘመናዊ በጠረጴዛ ዙሪያም በሚደረግ ውይይትና ውሳኔ” የሚያምን ነውና፤ እውነቱ ግን ፈሪ የወንድም አልጫ ነው።

በዚህም ምክንያት ወይ ውጪ አምሽቶ ይገባል፣ በቤትውስጥ ቢኖርም ፍዝ(ካገኘበልቶ ካጣም ተደፍቶ) ይኾናል። እናም ዛሬ ዛሬ ወንዱ የተወውን ቤት የመምራት ልጆችን የመግራት ሥራ ከሌላው የቤት ሥራ ጋር ደርበው ሴቶቹ ይሠራሉ።

አንተ ግን ቤትህን በስርዓት ማስተዳደር ግዴታህ ነው። እንኳን ሚስትህ ቤትህ መጥተው ከገበታህ ማዕድን የሚቆርሱት ወዳጆህ እንኳ ስርዓትህን ባይደግፉህ፣ቢቃወሙህም ፍቺንም ቢደግሱልህ፣ ፈርተህ ጋጠወጥ ቤተሰብ መሥርተህ ለሃገር ሸክም የኾኑ ልጆች እንዳታፈራ።

የመኝታቤቱ አልጫነት

ሴታቆርቋዡ እሳቤ (Feminism) ሴቶችን ያላቀ(empower) መስሎ ያከሰረ መኾኑን በተለይ ትዳራቸውን ከድጡ ወደ ማጡ በላከበት የመኝታቤቱ ይስተዋላል በዚህም የወሲብ ሕይወት ወንዱ ከምንግዜውም የበለጠ አልጫ ኾኗል።
እንዴት? አንደኛ የዛሬ ጊዜ ባል አብዛኛውን ጊዜ ከሚስቱ ለመራከብ ይለማመጣል። ሲፈራ ሲቸር፣ ሲወጣ ሲገባ፣ ሲኮሳተር ሲልመጠመጥ ብዙ ደጅ ይጠናል ሊያውም መልሱ “አሞኛል፣ ደክሞኛል፣ ደብሮኛል፣ሥራ አለብኝ፣ አጠናለሁ… ” ሊኾን።

የሴታቆርቋዡን እሳቤን የያዘ ወንድ መኝታቤት ገብቶ ፈቃድ ይጠይቃል፣ፈቃዷን ሲያገኝ ፍላጎቷን ያማርጣል፣ ምርጫዋን ሲያገኝ እንደነገሩ ይንደፋደፋል፣ ከዚያም ለአፈጻጸሙ ማረጋገጫን ይሻል። ይኼ ዘመናዊነት ሳይኾን ዘመንኛ አልጫነት ነው፤ የሚሠሩትንምአለማወቅ ኃላፊነትንም አለመውሰድ ነው።

ወሲብ ቅጽበታዊ ስሜታዊ ኾኖ በኹለቱ ተቃራኒ የጾታ ዋልታዎች መካከል በሚፈጠር ከፍተኛ ጾታዊ ስበት ሲፈጠር። ድርጊቱም በሰሜኑ ዋልታ(ወንዱ) መሪነትና ፍጥነት በደቡብ ዋልታዋ(ሴቷ) ተከታይነትና አራስ ነብርነት የሚደምቅ የተፈጥሮንም ጥያቄ የሚመልስ በኹለቱ ተቃራኒ ዋልታዎች ስህበት ትዳር የሚቆምበት ምህዋሩንም ተብቆ የሚሾርበት ግብግብ እንጂ….. ይቆየን

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *