ሴትን ያመነ ጉም የዘገነ(….ካለፈው የቀጠለ)

ይህ የሴቷን ቃል ተመልክቶ በጉም የተመሰለን ተረት የጉምን ባሕርይ እያስታወስን ወደ ሴቷ እንወስደዋለን።

የጉም ባሕርይ አየራዊ ነው ወይም ጉም በባሕሪው አየር ነው፤ ከሙቀት የተነሳ ተኖ አየር ላይ የቀዘቀዘ ውሃ ከፈሳሽነት ወደ አየርነት የተለወጠ። ምንም እንኳ ሕልውናውን በዓይናችን ብንመሰክርም በእጃችን ግን ጨብጠን ማረጋገጥ አንችልም።
ጉም አልጨበጥ ብሎን ብንበሳጭ ችግሩ ያለው ከጉሙ ሳይኾን የጉምን ተፈጥሮአዊ ባሕርይ ካልተረዳነው ከእኛ ነው።

አንተ ከሚስትህም ሆነ ከሴት ጓደኛህ ጋር በሚኖርህ ግንኙነት ይኼንን ተረት ባትተርተው እንኳ ምንጊዜም በዚህ ትርጓሜ አስበው። ይህንን ካላወቅህ፣ ካልተቀበልክ በሕይወትህም ካልተለማመድከው እመነኝ መቼም ሚስትህን አትረዳትም። ይህን ተፈጥሮአዊ ባሕሪዋን ባለመረዳትህ ታዲያ በመሓላችሁ ለሚፈጠሩ አለመግባባቶች ሁልጊዜ ተጠያቂ ታደርጋታለህ።

የእርሷ ቃል እንደ ጉሙ ነው። ጉም ሕልውናው በአየር እንደሆነ ንፋስም ተሸክሞ እንዲያመላልሰው፤ የእርሷም ቃል ሕልውና ስሜቷ ነው። ቃሏን ስሜቷ ያመጣዋል፣ እርሱንም ይገልጸዋል። “እንዲህ” አለችኝ ብለህ ልታደርግ ስትነሳ ወይም ካደረግህ በኋላ ሌላ ስሜት ይመጣል የቀደመ ቃሏን በሌላ ይሽራል።

ይኼ ለውጥ ግን የእርሷ ችግር ነው እንዳትለኝ በፍጹም አይደለም እርሷ አስባበትም የሚኾን አይደለምና። ይልቁንስ አንተ ሚስቴን ደስ አሰኛለሁ ለምትለው አባወራ ልታውቀው የተገባ የሴቷ ዋነኛ ባሕርይ ነው። ባሕርይ የአንድ አካል መገለጫ ሲኾን ግኝቱ ደግሞ የአካሉ ተፈጥሮ እንጂ ቤተሰብ፣ አካባቢ ትምህርት ቤት…… አይደለም።

ግኝቱ ተፈጥሮ ነው ካልን አስገኚው ፈጣሪ ነው ብንል የአገላለጽ እንጂ የትርጉም ለውጥ የለውም። ፈጣሪ ደግሞ ፈጥሮ ሲጨርስ ሁሉ መልካም እንደሆነ አይቷልና አንተ ባትረዳውም ስለ መልካምነቱ ግን አትጠራጠር።

ልብበል!! ይህ የሴቶች ባሕርይ ዘር፣ ቀለም፣ ሀገር፣ የትምህርት ደረጃ፣ ዕድሜ ሳይለይ በሁሉም ሴቶች ውስጥ በመጠን ቢለያይም ያለ ነው።

የሚከተሉትን የባልና የሚስት ወጎች እስቲ እንይ
(ትላንት ማታ) አባወራ፦ ውዴ ነገ እረፍትም አይደል፣ ምርጥ ቴያትር እጋብዝሻለሁ።
ሚስት፦ እሺ የኔ ጌታ ደስይለኛል።
(ጠዋት) አባወራ፦ መግቢያ ትኬት እንዳያልቅብን ቶሎ በይና እንውጣ።
ሚስት፦ የት?
አባወራ፦ ቴያትር አላልኩሽም?
ሚስት፦ ባክህ ከቤት አልወጣም።
አባወራ ወገቧን ጎተት፣ ከንፈሯን ግምጥ፣..”እንውጣ ንግስቴ፤ንጉስሽን ብዙ አታስጠብቂው”።
ሚስት፦ ህ..ም..ም…(የስሜት ወጀቧ ተቀየረ) እሺ ልብሴን ቀይሬ አሁን እመጣለሁ የኔ ጌታ።

ምስኪን-ባል እና የሚስቱ ወግ
(ትላንት) ምስኪን-ባል፦ ውዴ ነገ እረፍትም አይደል? ቴያትር ብናይ ምን ይመስልሻል?(X)
ሚስት፦ ፊልም አይሻልም?
ምስኪን-ባል፦ እሺ(X)
(ጠዋት) ምስኪን-ባል፦ እባክሽን መግቢያ ትኬት እንዳያልቅብን ቶሎ በይና እንውጣ?(X)
ሚስት፦ የ…ት?
ምስኪን-ባል፦ ቴያትር ስልሽ ፊልም አላልሽም?(X)
ሚስት፦ ኧረ የትም አልሄድ።
ምስኪን ባል፦ ኧረ ባክሽ! ይሻላል? ይቅር ከደበረሽ።//ወይም ተናዶ ምንድነው አንቺ ደግሞ ቴያትር ስልሽ ፊልም አልሽ ዛሬ ደግሞ አልሄድም ትያለሽ? በቃ ተይው እንደውም።(X)
X፦እነኚህ የምስኪኑ የተሳሳቱ ንግግሮች ናቸው።
========
ልብ አድርጉ!! አባወራው ፍርጥም ያለ ድርጊት ቀረሽ ቃል ይናገራል ከዛም ተናግሮ አይቀርም ያደርገዋል። በምርጫ ብዛት ለምትቸገረው ሚስቱ ሌላ ምርጫ አይጨምርም። ሲቀጥል ሚስቱ እምቢታዋ በወቅቱ ከተሰማት የስሜት መዋዠቅ እንጂ ግብዣውን ጠልታ እንዳልኾነ ያውቃል። ስለዚህ ቃሏን ለመቀየር ስሜቷን መቀየር ነበረበትና አደረገው እንጂ አልተበሳጨም።
ምስኪኑ ግን ይህን የሚስቱን ተፈጥሮ አይረዳም፤ አንድም ተምሬአለሁ፣ በውይይት አምናለሁ ሲል ቃሏን ያምናል እና ባትፈልግ ነው ይላል፤ አንድም ደግሞ ኃሳቧን መለዋወጧ ምክንያት የለሽ እምቢታ ያደርገዋል። ….. ይቆየን

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *