ሴትን ያመነ ጉም የዘገነ

ማሳሰቢያ፦ ሴትን ያመነ ጉም የዘገነ ማለት ሴት ልጅ ውሸታም ነች ማለት አይደለም።

የሚስቶቻቸውን ተፈጥሮ አውቀውና ስሜቶቻቸውን ተረድተው ወደር-የለሽ ደስታን(እርካታን) ለሚያጎናጽፉ ዕጩ አባወራዎች ብቻ የቀረበ፤ለስሜታዊ እና ሆደ-ባሻ ወንዶች በፍጹም የተከለከለ ነው።

መግቢያ እና መግባቢያ የሚሆነውን ኃሳብ ሰኞ ዕለት ስለለጠፍኩ ዛሬ ወደ ቁም ነገሩ ልግባ።
መጀመሪያ ግን እነዚህን መሪ ቃላት ድገም፦
፨የተፈጥሮአችን አስገኝ ፈጣሪ(እግዚአብሄር) ነው።
፨ እርሱ ፈጣሪያችን እውነት እንደኾነ ተፈጥሮአችንም እንዲሁ ነው።
፨የተፈጥሮአችን ባሕርያት በፈጣሪያችን በዓላማ የተቸሩን(የተሰጡን) ናቸው።
፨እነርሱን አውቆ፣ተረድቶ እና ከእነርሱም ጋር ስምም ኾኖ መኖር በተፈጥሮ እውነት ላይ መመሥረት ነው።
፨በዚህ እውነት ላይ መመሥረት ደግሞ ማየል(ኃይለኛ፣ ብርቱ) መኾን፣ ከተሳሳተው የዓለም ማንነት ነፃ(አርነት) መውጣት እና የሕሊና እረፍት የኑሮ ሰላም ያድላል (ያስገኛል)።

እኛ ሰዎች በኑሮአችን ውስጥ በምናደርጋቸው የእለት ተእለት ግንኙነቶች በስሜት ሕዋሶቻችን የተቀበልነውን በእምሮአችን አመዛዝነን ፍላጎታችንን፣ ውሳኔዎቻችንን እናም አቋማችንን በቃላት እንገልጻቸዋለን። ይህ ምንም እንኳ በደፈናው ገዢ እውነት ቢኾንም ተግባራዊነቱ ላይ ስንመጣ ግን በሁለቱ ጾታዎች ይለያያል።

የምንናገረውን ቃል አስቀድሞ ማሰብ፣የሚያሳድረውንም ተጽዕኖ መገምገም ከዛም ግልጽ ባለ ቋንቋ እቅጩን (እውነቱን) መናገር፣ የተናገሩትን ቃልም መጠበቅ እና መኖር የወንድነት መገለጫ ናቸው(በአባወራነት መገለጫ መዳሰሳቸው አይዘነጋም)።

ይህን ስንል ግን ሴቶች እርግጠኛ የሆኑበትን ነገር በቃላት አይናገሩትም ማለት አይደለም። ከእኔ እና ካንተ በተለየ መልኩ በነገሮች ክስተት በድርጊቶችም ሂደት የሚናገሩት ቃል የተሰማቸውን(የስሜታቸውን ገላጭ) ነው እንጂ። ቀድመው የተናገሩትንም ቃል ባይጠብቁ ውሸታም አያሰኛቸውም።

ለሴት ልጅ ተፈጥሮ ስሜት ከቃላት እና ከሚታየው እውነት ቅድሚያ አለው። እርሷ በቃላት የምታስቀምጣቸው በወቅቱ በውስጧ ያለፉትን የስሜት ሞገዶች እንጂ በደንብ የታሰበባቸው፣ የተገመገሙ፣ አቋም የሚኾኑ ዘላቂ እውነቶች አይደሉም።
ለወንድ ልጅ በተለይም ለእንዳንተ አይነቱ ዕጩ አባወራ ግን እንዲህ አይደለም። አባወራ የሚናገረውን ያደርጋል፣ የሚያደርገውንም ይናገራል። ከአንደበቱ የሚወጣው ቃል የሚያስከብረው እና የሚያስወድደው ነውና(በተለይ በሴቷ)፤ ቃሉን ይጠብቀዋል ይኖረዋልም። ስለዚህም በሴቷ ፊት የምትናገረው ስሜታዊ ያልኾነ አስበህበትና አቅደህበት መሆን አለበት።ምክንያቱ ደግሞ ለእርሷ ቃልህ አቋምህ ነው ተፈጻሚነቱን ትጠብቀዋለች። ይህን እና ይህን አደርጋለሁ ብትላት እና ባታደርገው ትረሳዋለች አትበል። የት፣ መቼ፣ እንዴት፣ ምን እያደረጋችሁ እና ሌሎችም ስትነግራት የነበሩትን ዝርዝር ሁኔታዎች ምን ጊዜው ቢርቅ ትነግርሃለች። አንተ ግን እንዲህ አስታውሰህ “ይህን ብለሽኝ አልነበር?” ማለት አትችልም። ሲጀመር እንደ እርሷ ዝርዝር ነገሮችን አታስታውስም። ሲቀጥል ብታስታውስ እንኳ “ቃልሽን አልጠበቅሽም” ብለህ መጠየቅ የተፈጥሮአችሁን ለየቅልነት ያላገናዘበ አላዋቂነት ይሆንብሃል።

ሚስትህ ወይም እጮኛህ አሁን ተሰምቷት አደርገዋለሁ ወይም እንደዚህ ነው ያለችህ ነገር ከደቂቃዎች በኋላ ሊለወጥ ይችላል። እርሷ ስሜታዊ በሆነችባቸው ወቅቶች በሙሉ እንዲህ ነው፣ አደርገዋለሁ የምትለው ነገር በወቅቱ የተሰማትን ነው(ልብ አድርግ! ሴት ልጅ አብዛኛውን ጊዜ የአእምሮዋን አመክንዮ ሳይሆን የስሜቷን ታዳምጣለች)። ይኼም ማለት በደቂቃዎች ሽርፍራፊ ስሜቷ ቢለዋወጥ ቃሏም ኾነ ውሳኔዋ ይለዋወጣል። ይህንን የሚረዳት ወንድ ነው ሴት ልጅ በግር በፈረስ የምትፈልገው።

ተጠንቀቅ ግን ውሸታም አትባልም በፍጹም።
በጉም(በደመና) መነጻጸሯስ ይቀጥላል……..ይቆየን።

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *