ሴት ልጅህን ስለሕይወት ስለማስተማር

ሳተናው!
እንደ ወላጅ፣ እንደ ሴት ልጅም አባት በዚህችም አታላይ ዓለም ሴት ልጅህን በምግባርና በስርዓት ማሳደግ ከባድ ጥረት ይጠይቃል።

በተጨማሪም ሴታቆርቋዦቹ(Feminists) በተስፋፉበት በዚህ ዘመን እርሷን ተፈጥሮኣዊ ጸጋዋን (የእናትነት ሚናዋን) በወቅቱ ተጠቅማ ሀገር ተረካቢ ትውልድ እንድታፈራ ማስተማር ፈታኝ ነው።

ሴት ልጅህ እግዚኣብሔር የሰጣትን ጸጋ ተጠቅማ፣ ሚናዋን ፈጽማ ኃላፊነቷን መወጣትን ኋላቀርነት አለመሰልጠን አድርጋ ዓለም ታሳያታለች። እንዲሁም ለባሏ ተገዝታ ልጆች ወልዳ እነርሱንም ተንከባክባ ለቁም ነገር ማድረሰ ዛሬ ዛሬ “ግርድና”  የሚል ጸያፍ ቃል ትሰጣለች።

ዓለም ሴት ልጅህን ትምሕርቷን እንድትማር ስትነግራት ትምሕርቷን እንድትማር ሥራዋን እንድትሠራ ነገር ግን ትዳርና ልጅ እንደሚደረሱበት እየነገረቻት ነው። በዚህም ዘመኗን ኹሉ ራሷን ከወንዶች ጋር ስታፎካክር ሴታሴትነቷንም እየተወች ወንዳወንድም እየኾነች ትሄዳለች።

ከዚህ በፊት እንዳጫወትኩህ ደግሞ ይኽች ዓለም ለሴቶች የተቆረቆረች ትመስላለች ብዬኃለሁ። ለምሳሌ ልንገርህ ፦
ዓለም
፨ ሴቶችን በልጅነት አታግቡ እንጂ በልጅነት/ከጋብቻ በፊት/ ወሲብ አትፈጽሙ አትላቸውም። እንዲያውም ተገደው አይደፈሩ እንጂ ሂያጅነታቸውን(ከብዙ ወንድ መተኛታቸውን) ታበረታታለች።

፨ ትዳርን አዘግዩ ትምሕርትና ሥራ ላይ አተኩሩ ስትል ልቅ የኾነ ወሲብን ግን በብዙ ፈርጁ አበረታታ ነው።

፨ ሴቶችን ትምሕርት እና ሥራ ላይ ጊዜያቸውን ማጥፋቱ ን ስኬት ባሏና ልጆቿ ጋር ሲኾን ግን ብክነት ወይም ኪሳራ አድርጋ ነው።

፨ ሴት ልጅን ሽር ጉድ ብላ አለቃዋን እንድትታዘዝ በስልጠና የተደገፈ መመሪያ ሰትሰጣት ባሏን መታዘዙን ግን”ባርነት”፣  “ግርድና” ብላ ታስጠይፋለች(የኋለኛው የፈጣሪ ትዕዛዝ መኾኑን አስተውል)።

፨ “ያለፍቃዳችሁ ባላችሁም አይተኛችሁ” እያለች ገላቸውን ግን እንደሸቀጥ በአደባባይ እንዲያሳዩት እንዲዘሙቱበት በዚህም ትዳራቸውን እንዲያፈርሱ ትገፋፋለች።

፨ ተፈጥሮኣዊው የሴትነት ወጉ በወንዶች የተጫነባቸው አድርጋ ትሰብካለች። ለምሳሌ፦ ጸጉሯን ማሳደግ መንከባከብ፣ ቀሚስ መልበስ፣ በወጣትነት ማግባት፣ ለባሏ መገዛት፣ መታዘዝ፣ ልጅን መውለድ፣ ተንከባክኮ፣ አሳድጎ ለቁምነገር ማብቃት፣ ለልጆች የመታዘዝ አርአያ መኾን ወንዱ “ለራሱ እንዲመቸው የፈጠረው ነው” ይባላልና።

ሳተናው!
ሴት ልጅህን ስለሴትነት ለመምከር/ለማስተማር መጀመሪያው ጊዜ ገና ሕጻን እያለች ነው። ወደፊት ለምትሰጣት ጠንካራ የሕይወት ምክሮች በሕጻንነቷ መሠረት ትጥላለህ።

እድሜዋ አሥራዎቹ ውስጥ ሲገባ ቀድሞ በጣልክላት መሠረት ላይ ተፈጥርኣዊ ሐቆችን እና በትዳር ውስጥ ፈጣሪ ስለጣት ሚና  ደረጃ በደረጃ ትገነባታለህ።

ልጅህን ስለሴትነት ስትነግራት፣ ስታደርገውና ስታበረታታት እናቷም አርኣያ ስትኾናት ተፈጥሮዋን ወዳና አክብራ ትይዘዋለች። ልብ አድርግ! ትደግ ትደግ ብለህ እድሜዋ አሥራዎቹ ውስጥ ከገባ አመለጠችህ።

ሴት ልጅህን በአነጋገሯ፣ በአለባበሷ፣ በአረማመዷ፣ በአቀማመጧ ኹሉ ትሕትናዋን፣ ሴትነቷን  የጠበቀ እንዲኾን አስተምራት ይኽንንም አበረታታ። አስተውል! የምታበረታታው ተፈጥሮዋን ሳይኾን በተፈጥሮ የተሰጣትን ጸጋ መጠበቋንና መንከባከቧን ይኹን (ይኼ ለሚስትህም ይሠራል)።

ተፈጥሮዋን ግን አድንቅ፣ አስደናቂው ፈጣሪ የፈጠራት ድንቅ ፍጥረቱ እንደኾነች በዚህም ፈጣሪዋን እንድታመሰግን አሰልጥናት። ይኽን ስታደርግ ላልደከመችለት ተፈጥሮዋ ምስጋናን ውዳሴን ከመበቀል ትጠብቃታለህ።

ይኹን እንጂ የተሰጣትን ጸጋ ወዳው፣ ጠብቃው፣ ተንከባክባው ያለነውር ስትጠቀምበት ያን ግዜ  አሞግሳት።

አባወራው ንሳ ልጅህን፦

፩ኛ አንተን ማክበር አስተምራት። ይኼንንም አንተ መከበር እንደምትፈልግና እንደሚገባህም ግድ ስትል እና እናቷ ደግሞ አርአያ ስትኾናት ትረዳለች።

፪ኛ መታዘዝንም እንዲሁ አሰልጥናት

፫ኛ የእናቷን ፈለግ ተከትላ ቤት አያያዝ፣ ምግብ አበሳሰልና ታናናሾቿን መንከባከብ ሙያ ታድርግም ዘንድ።

፬ኛ ለወንድ ልጅ ያልተሰጠው ድንቅ ተፈጥሮኣዊ ጸጋ እንዳላት፣ እንድትጠብቀውና እንድትንከባከበው እርሱንም ተጠቅማ ፈጣሪ የሰጣትን ሚና እንድትወጣ አስተምራት።

፭ኛ ትምሕርትና ሥራ ብላ በልምላሜዋ ጭላጭ ትዳር እንዳትመሠርት ይልቁንም በጉብዝናዋ ወራት ይኼን ትልቅ አደራ እንድትሸከም ምከራት።

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *