ሴት አቆርቋዥ ወንዶች (Feminist men)

ሳተናው!
ዛሬ ደግሞ ስለሴት አቆርቋዥ ወንዶች(Feminist men) ላጫውትህ። ይኼንንም የምነግርህ አንተ ራስህ እንዲህ እንዳትኾን እና ከእንደ እንዚኽ ዓይነት ወንዶች ራስህንም ኾነ ቤትህን እንድትጠብቅ ነው።

ምስኪን ወንዶች አሁን ባለንበት በ21ኛው ክፍለ ዘመን ሴታቆርቋዥ ወንዶች(Feminist men) የመኾን እድላቸው ሰፊ ነው። ለሴቶች መብት ተቆርቋሪ ስለሴቶች ነፃነት ተሟጋች ነን ይላሉ። ነገር ግን ይኽን የሚያደርጉት በምትኩ “በሴቶች እንወደዳለን”፣ “በሴቶች እንከበራለን” ከዚህም የተነሳ “ለትዳርም ኾነ ለወሲብ ይፈቅዱናል” ብለው አስበው ነው።

ይኽ ደግሞ ቁልጭ ያለ የስጋ ገበያ ነው። ከዚኽ በፊት ስለምስኪኑ ወንድ የጻፍኩልህን እርሱ በልቡ የሚይዘውን ድብቅ አጀንዳ “ሰዎች(ሴቶች) ይኼን ባደርግላቸው ይኼን ያደርጉልኛል” የሚለውን ያስታውስሃል።

ምስኪን ለሴቶች መብት መቆርቆርን፣ ስለእነርሱ ሁልጊዜ መልካም ማውራትን ኋላ ላይ መወደድን፣ ጭብጨባን፣ ክብርን ሲቀጥልም ወሲብን(ከሚስቱም ኾነ ከሌላ) ያስገኝልኛል ብሎ ያስባል። ይኽን የመሰለውን ገበያ ታዲያ ተፈጥሮኣዊውንና ራስን ኾኖ እናም አክሎ ከሚገኘው መሳሳብ ውጪ የኾነ ዕድሜውም አጭር ፈቃድ ነው።

ምስኪን ወንዶችም ኾኑ ሴታቆርቋዦቹ ወንዶች ያልተረዱት ነገር ቢኖር በሴትና በወንድ መካከል ያለው መከጃጀል እንደሌሎቹ የስጋ ገበያ ዓይነቶች አለመኾኑን ነው።

ሳተናው! አ…ስ..ተ…ው…ል!
እርሷ የምታገባህም ኾነ ካገባችህም በኋላ እንኳ የምትተኛህ ከውለታዎችህም ኾነ ከስጦታዎችህ ብዛት የተነሳ አይደለም።

ይልቁንስ በተፈጥሮኣዊው እውነት ላይ የተመሠረተ እውቀትህ፣ በእርሱም በኾነ በራስ መተማመንህ፣ እንዲሁም ራስህንም ኾነ ዙሪያህን የመግዛትና የመቆጣጠር ብቃትህ ይማርካታል (ባጭሩ ወንዳወንድነትህ)።

ይኽን ተፈጥሮኣዊ የወንዳወንድነት ባሕርይ ግን በተለይ በአስተዳደጋቸው ወቅት ሳይጎለብት ይቀርና በተቃራኒው ለማንነታቸው ጭብጨባና ይኹንታ ፈላጊ ሲኾኑ ወንዳወንድነት ደግሞ ዱርዬነት ይመስላቸዋል።

ይኹን እንጂ ምስኪኖችም ኾኑ ሴታቆርቋዥ ወንዶች(Feminist Men) ይኼን ተፈጥሮኣዊ የኾነ የስበት ምስጢር ወደ ጎን ይተዋሉ። ከሴቶቹ(ከሚስቶቻቸው) ጋር በኃሳብ ስለተስማሙ፣ አብረዋቸው ስለዋሉ፣ ለጥያቄዎቻቸው መልስ ስለሰጡ፣ ስለፍላጎቶቻቸው ከአንደበታቸው የሚገኘውን ስለተቀበሉ ፣ ጭብጨባና ውዳሴም ስላበዙላቸው በሴቶቹ ዘንድ መወደድን፣ መከበርን፣ አንሶላ መጋፈፉንም እናተርፋለን ብለው ያስባሉ፤ ሲያምራቸው ይቀራል እንጂ አያገኙትም።

እስቲ ከሰዎች ስሕተት እንኳ እንማር! ምን ያክል ሴቶች ምክንያቱን በውል በማያውቁት፣ ምንጩንም ባልተረዱት ስሜት ምስኪንና የልጆቻቸው አባት የኾኑ ባሎቻቸውን ትተው በራስ መተማመናቸው(አንዳንዴም ትዕቢታቸው)ጥግ የደረሰ ዱርዬዎች ጋር እንዲሄዱ አስተውል።

ከላይ የገለጽኩትን ተፈጥሮኣዊ ስበት የማይቀበሉት፣ ለመስማት የማይፈልጉት፣ የሚጠየፉትም ቀድሜ የጠቀስኳቸው ሁለቱ ወንዶች ናቸው። እነርሱም ብዙ ከኾኑላቸው ሴቶች ብዙ ጠብቀው ጥቂት ወይንም ምንም ክብር ሲያጡ አልፎ ተርፎም ወደ”ዱርዬዎቹ” ሲሄዱ ሴቶቹን “ክብርን የማይወዱ፣ ከሚወዳቸው ይልቅ ለሚንቃቸው  የሚሸነፉ” ብለው ያሟቸዋል።

ሳተናው ወንድሜ!
ይኽ እኔ የምነግርህ በሕይወት ከተማርኩት በኢ-መደበኛ ጥናትም ካበለጸግኩት እውቀቴ ከፍዬ ነው። ይኽ የምነግርህ ነገር መራር እንደኾነ አውቃለሁ። ነገር ግን ምን ስትሰማው ቢመርህም ካላዋቂነትህ የተነሳ በሕይወትህ ስትፈተንና ስትወድቅም ኑሮህ እንደሚመርብህ ግን በጭራሽ እንደማይኾን እኔ ሕያው ምስክር ነኝ።
===========================================
ምስኪንና ሴታቆርቋዥ ወንዶች(Feminist Men) ለሴቶች ሲሟገቱ ከራሳቸው ከሴቶቹ ይበልጣሉ። “ለምን?” አትለኝም ?

፩ኛ ሚስት ብትኖራቸው “ታጨበጭብልኛለች”፣ “ያለገደብም ትተኛኛለች”፣ “ታሞግሰኛለች”፣ “ትወደኛለች” …ሲሉ
፪ኛ እናት ብትኖራቸው “ጎሽ ልጄ፣ ጠበቃዬ ትለኛለች”፣ “ትመርቀኛለችም”ሲሉ… ያስባሉምና
፫ኛ “ብዙኃኑ ለደካሞች የቆመ፣ ለሰው አዛኝ” ይለናል ሲሉ
እነዚኽና እነዚኽን የመሰሉትም የብዙኃኑን ልብ ያሸንፍልናል፣ ጆሮኣቸውን ይሰጠናል፣ ዐይናቸውን ይመልስልናል ብለው።

እንደዚህ ዓይነት ወንዶችን በማሕበራዊ ሚዲያው ላይም ኾነ በመገናኛ ብዙኃኑ ላይ ዛሬ ዛሬ በብዛት እናገኛቸዋለን። ልዩ ምልክታቸውም የሚታይ፣ የሚዳሰስና የሚጨበጥን ሥራ ከመሥራት ይልቅ ስለ ሥራው አጣፍጠው የሚያወሩ ፤ ኾነው ከመገኘት ማስመሰል የሚወዱ፤ መስጠት ያስደስተናል ብለው በሰፈሩበት ልክ የሚጠብቁ ሲያጡም የሚበሳጩ መኾናቸው ነው።

ሳተናው! ተጠንቀቅ!
ሴታቆርቋዥ ወንዶች (Feminist men) ዱርዬና አባወራ ወንዶችን እንደማየትና መስማት ደማቸውን የሚያፈላው ምንም ነገር የለም። ከማንም ጋር መኖር ቢችሉ እንኳ፣ ማንንም ቢታገሱ ዱርዬና አባወራን ግን በጭራሽ፤ ቢችሉ ያጠፏቸዋል ባይችሉ አጥፍተዋቸው ይጠፋሉ።

“ዱርዬስ እሺ ዱርዬ ነው አባወራውን ግን ለምን?”.. …… ይቆየን

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *