ሴት-አውል (Player) እና ዱርዬ(Bad boy

)

ዛሬ ከአባወራው (በስብዕና) በብዙ ከሚርቀው ሴት-አውል ወንድ ጋር ነኝ። ሴት አውልነት በማሕበረሰባችን ውስጥ በኃይማኖትም ኾነ በባሕላችን ዘንድ መልካም ስም አይደለም።

ለሴት-አውል ወንድ ሴት-አውልነት ጠባዩ ነው። ለመግባባት ይበጀንም ዘንድ ሴት-አውልነትን እንግለጽ።
ሴት-አውልነት በቁጥር ከበዙ ሴቶች ጋር ጾታዊ(ወሲባዊ) ግንኙነትን ባማከለ ኹኔታ መወዳጀት ነው። ይኼም ሲኾን ሴቶቹ ፈልገው እና ፈቅደው በተራ አልያም በጋራ ከወንዱ ጋር የሚወዳጁበት ነው።

ሴት-አውል፦ የሴት-አውልነቱ ጠባይ የተጠናወተው፣ ለራሱ ወሲባዊ ፍላጎት ያደላ፣ ይኽንንም “አሳቢ”፣ “ተቆርቋሪ” መስሎ የሚያሳካ፣ ጉልበትን ማስገደድን የማይጠቀም ነው። በተለይም የሴቶችን ለፍቅር፣ ለእንክብካቤ፣ ለጨዋታ፣ ለቅብጠት ያላቸውን ቦታ አይቶ፣የሚያደርግላቸውንም ኾነ ጊዜ ማጣታቸውን አስታኮ ይኽንኑ በመስጠት በፈንታው ወሲብን የሚገበይ ነው።

ሴት-አውል ራስወዳድ ነውና የሴቷን ፍላጎት የሚፈጽመው የራሱን ፍላጎት ለማድረስ ነው። የሚፈልገውንም ሲያገኝ ወይም ሲበቃው ይተዋታል። ሲተዋትም ለሚሰማት ስሜትም ኾነ በዚያ ስሜት ስለሚበላሸው ሕይወቷ ደንታ የለውም። በዚህም ኃላፊነት የማይሰማው ትዳርን ቤተሰብን መመሥረት የማይችል(የማይፈልግ) ትውልድን የማነጽም ኾነ ሀገርን የመገንባት ርዕይ የሌለው ይልቅስ “ማነሽ ባለሳምንት” እያለ ወደ ተረኛዋ የሚሄድ የስሜቱ ባሪያ ነው።ሴቷም ትላንት “ይሄ ደግሞ ምን ሴት ሲጎትት ነው እንዴ የሚውለው” ስትል ቆይታ ውስጧ የናፈቀው ተራዋ ሲደርስ በደስታ ትሄዳለች(አግብታለች አላገባችም አይመልሳትም)።

ዛሬ ዛሬ በተለይ ኃላፊነት የሚሰማው፣ በትዳሩ የሚወሰን፣ ወሲብ ተፈጥሮኣዊ ዐላማውን ማስፈጸሚያ ጸጋው እንጂ በራሱ የሚኖርለት ዐላማው እንዳልኾነ ከተረዳ አባወራነት ይልቅ ሴት አውልነት እንደ ጀብድ መታየት ከጀመረ ሰነባብቷል።

ሴት-አውልነት በአብዛኛው ማሕበረሰባችን ውስጥ በይፋ የተወገዘ ምግባር ነው። የማሕበረሰባችን እሴቶች የኾኑት ባሕል እና ኃይማኖትም ይህንን ምግባር ይጠየፉታል።
በተለይም ደግሞ የዚህ ምግባር መጠቀሚያ የኾኑት ሴቶች ራሳቸው በይፋ(በግልም ኾነ በጋራ) በአፍኣ፣ በአደባባይ ያወግዙታል። ይኹን እንጂ ከውግዘታቸው በተቃራኒ ልባቸውን(ቀልባቸውን) በሕቡዕ (በድብቅ) “ደስ በሚያሰኝ” ስሜት ጠርንፎ የሚጎትት አንዳች ኃይል እዚህ ሴት-አውል ወንድ ውስጥ አለ። ፈልገውት ሳይኾን ሳይፈልጉ፣ በአስተዋይ አእምሮአቸው አስበውት እና ፈቅደው ሳይኾን በአንድ በድብቅ ኃይል ይማረካሉ። እርሱ ምን ይኾን?

አንተ ውድ ወንድሜ ሴት-አውልነትን ማውገዝ ቢገባህም ስላወገዝክ ብቻ ግን ማስቀረት አትችልም። ሴቶቻችን (ሚስቶቻችን፣ ልጆቻችን፣ እናቶቻችን፣ እህቶቻችን) በዚህ ባወገዝነው ልምምድ እንዳይጎዱ አንተ እና እኔ ግዴታችንን መወጣት አለብን።

ነገር በምሳሌ ጠጅ በብርሌ እንዲል ብሂለ-አበው ፦ ሌባን ለማስቀረት ሌብነትን ማውገዝ የመጀመሪያው እርምጃ ቢኾን እንጂ የመጨረሻው አይደለም። “እኽሳ?” ከራስወዳድነት የተላቀቀ ተካፍሎ የመብላት፣ ተረዳድቶ የመኖር ባሕላችንን ማዳበር ከዚህም ሲያልፍ ቤትንም በኃላፊነት መጠበቅን ይሻልና።

ለእኔ እና ላንተም እንዲሁ ነው። ሴት-አውልነትን በማውገዝ ብቻ ሴቶቻችንን መደዴ ወይም ሂያጅ ከመኾን መታደግ አንችልም። ምክንያቱም ደግሞ እነርሱም በአፋቸው በይፋ የሚያወግዙት ነገር ግን በሕቡዕ የሚወስዳቸው ነውና። “እኮ እርሱ ምንድነው?”

ለዚህም ነው በቅጽበትና በድግግሞሽ ለሚለዋወጠው ስሜቷ ጠባቂ፣ እረፍት(ወደብ)፣ ኃላፊ፣ ራስ(dominant)፣ ለሴትነቷ ልከኛ ግጣም ወንድ (ለጾታዊ ፍላጎቷም የልብ አድርስ አንጀት አርስ) ምናለፋህ አባወራ ኹን የተባልከው።

==== === ===== ===== ==== ==== ==== === === ==== ==== === === ===
በዚህ ትይዩ ደግሞ የፈለገውን በጥያቄ ሳይኾን በኃይል፣ በብልጠት ሳይኾን በጉልበት የሚወስደው ዱርየው-ወንድ(Bad boy) አለ። ይኼንንም ሴቶቻችን በይፋ ቢያወግዙትም አኹንም በሕቡዕ ወደ እርሱ የሚጎትታቸው አንድ ምሥጢር አለ። …. “እርሱስ ምንድን ነው?”

ለሳምንት ብንንኖር ዱርየውን-ወንድ (Bad boy) እናያለን…… ከዚያም….. ከዚያም… ሴት-አውሉ እና ዱርየው-ወንድ ቤተሰብ ለመመሥረት፣ ለትዳር የማይኾኑ፣ በዚህ ላይም በሕብረተሰቡ የማይደገፉ፣ ሴቶችም በአፋቸው የሚያወግዟቸው ኾነው ሳለ ውስጣቸው ግን ለምን ይማረክባቸዋል? እነርሱ ላይስ ለምን ይጥላቸዋል? ….ይቆየን

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *