ሴቶችና የወንድ አልጫ

ሳተናው!
በዚኽ ዘመን ዐለም እንደምትነግርህ ሴቶችም በአፋቸው እንደሚመሰክሩት እንዳይምሰልህ ሴት ልጅ አልጫ ወንድን አትሻም። ይኼ ተፈጥሮኣዊ እውነት አንተ ብትቀበለውም እውቀት ይኹንህ።

ሴት ልጅ በደመነፍሷ(instinct) እርሷን፣ ልጆቿን ቤተሰቧን መጠበቅ እና መታደግ የሚችል ወንድን ትሻለች። ይኼንን በአፏ አትነግርህም፤ ነገር ግን የአቅሟን ደካማነት፣ ለወንዱ የተሰጠውንም ጉልበት ታውቃለችና ይኼንን ግዳጅ ለሚወጣ ወንድ ፈቃዷ ያዘነብላል።

ይኹን እንጂ ዛሬ ላይ ከሴቷተፈጥሮኣዊ ፈቃድ ውጪ ዐለም በውሸት ስብከት ታታልላትና ይኼንን ፈቃዷን ትሰውርባታለች። በደመነፍሷ ከሚሰማት ከተፈጥሮኣዊ ዝንባሌዋ ከሚመነጨው ፍላጎት ይልቅ “ፍቅር ሁሉን ያሸነፋል” በሚል ብኺል ተፈጥሮዋን ክዳ አልጫ ታገባለች ወይም ይኼንን ሚና “እኔ መወጣት እችላለሁ” ትልና ከሴታሴትነት ይልቅ ወንዳወንድነት ጠባይ ታሳያለች።

“ቤቴን እመራለሁ፣ የቤቱ የመጨረሻው ውሳኔ የእኔ ነው፣ ለወንድ(ለባል) ኃሳብም ኾነ ውሳኔ አልሸነፍም፣ መታዘዝም ግርድና ነው” የሚሉ አቋሞችን ትይዝና የፍቅር(የትዳር) ሕይወቷን በኃዘንና በጭቅጭቅ ትገፋለች።

ዠተዘራሽ እውቀት በመሙላት አልጫ ወንድ እንዲያገቡና በማያሳርፋቸው ትዳር ውስጥ እንዲባዝኑ በዚኽም ትዳር እንዲፈርስ ትውልድም መረን እንዲወጣ ታደርጋለች።

አንድም ደግሞ በዚኽች አሳሳች ዐለም አስተምሕሮ ተጠልፈው የወደቁት ሴቶች ምስኪንን በተለይም ደግሞ አልጫ ወንድን ለትዳር የሚፈልጉበት ጊዜ አለ(መቼ ለምን ሌላ ጊዜ አወጋችኋለሁ)።

አልጫ ወንድን አልጫነቱን አውቀው ያገቡት ሴቶች ታዲያ ሁልጊዜም በመዳፋቸው ሥር ሲያኖሩት ከዚኽ ቦታው ወጥቶ ራሱን ወደማከል ሲመጣ ግን ትዳሩ በፍቺ ይጠናቀቃል።

“ፈሪ ለእናቱ” እንዲባል አልጫ ወንድም በአቋሙ ከመጽናት፣ ዓላማውን ዳር ለማድረስ የሚመጣን ፈተና ተጋፍጦ ከሰዎች ጋር ከመጋጨት የራቀ ነው።

ሴቶች እህቶቼን በጭራሽ አልጫ ወንድን ከትዳር አጋር ምርጫችሁ ውስጥ አታካቱ ስል፤ ወንዶቹን እንዲጀግኑ በማበርታት ነው። እንዲኹም ደግሞ ልጆቻቸውን ድፍረት፣ ጥንካሬና ጽናትን(ሥነ-ልቦናዊም ኾነ አካላዊ) እንዲኖራቸው አድርገው እንዲያሳድጉም የራሴን ተሞክሮ በማካፈል ጭምር ነው።

ሴቶቻችን፣ ትዳራችን፣ ልጆቻችን፣ ማሕበረሰባችን፣ ሀገራችንም፦ ርዕይ ሰንቀው፣ ዓላማን ሰቅለው፣ ሚናን ለይተው፣ ስሜታቸውን ገዝተው የሚጓዙ ስለ እነርሱም ሲሉ ዋጋ የሚከፍሉ ጽኑ ጀግና ወንዶች ያስፈልጓቸዋል።

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *