ሴቶችን አይወዷቸውም

ሳተናው!

ሴታቆርቋዥ ወንዶች(Feminist men) ሴቶችን አይወዷቸውም። እነርሱ ከሴቶች ጋር ተፈጥሮኣዊ መንገድን የተከተለ ስሕበትን(መሳሳብን፣ መዋደድን) ከመከተል ይልቅ ሰጥቶ መቀበል መርሓቸው ነው።

ሴቶች እንዲወዷቸው፣ ሚስቶቻቸውም እንዲተኟቸው የሴቶችን ተፈጥሮኣዊ ፍላጎት ከመፈጸም ይልቅ በአፋቸው “ያስደስተናል” ያሉትን መከተል እርሱንም ሰጥተው በፈንታው ፍቅርን ወሲብን መሸመት ይሻሉ።

በመሠረቱ ከሴቶች እነማን ናቸው ከሚተኙት ወንድ ክፍያን በዓይነትም ኾነ በገንዘብ የሚጠይቁት? ወንዶችስ ከሴቶች መወደድን አልያም አንሶላ መጋፈፍን ሲያስቡ በዓይነትም ኾነ በገንዘብ ከፍለው የሚፈጽሙት ከኾነ “እንቆረቆርላቸዋለን” ለሚሏቸው ሴቶች ያላቸው ክብር የቱ ጋር ነው።

አስረጅ ፦ ከዚኽ ቀደም በወንድና በሴት መካከል ያለውን ተፈጥሮኣዊ መሳሳብ በሁለት ማግኔቶች ካለው መሳሳብ ጋር አመሳስለን ያየነውን እንከልሰው።

ማግኔት በባሕሪው ብረቶችንና ሌላ ማግኔትን ይስባል። ከብረቶቹ ጋር ያለውን ስሕበት ትተን ከመሰሉ ከማግኔት ጋር ያለውን እንይ። አንድ ማግኔት ሁለት ዋልታ ሲኖረው የሰሜን ዋልታ እና የደቡብ ዋልታ ተብለው ይጠራሉ።

ሁለት ማግኔቶች በተቃራኒ ዋልታዎቻቸው ሲሳሳቡ በተመሳሳይ ዋልታዎቻቸው ደግሞ ይገፋፋሉ። በሁለት ማግኔቶች መካከል ያለው የስሕበት ጥንካሬ ዋልታዎቹ በራሳቸው በያዙት ጥንካሬ ላይ ይወሰናል።

ከፍተኛ የኾነ የማግኔት ስሕበትን ለማግኘት የሁለቱን የማግኔት ተቃራኒ ዋልታዎች ማግኔታዊ ጠባይ መጨመር ነው(ለምሳሌ በኤሌክትሪክና ከሌላ ማግኔት ጋር በማፋተግ)።

ወደኛ ዐውደ ንባብ ስናመጣው

በወንድና በሴት መካከል ባለው ተፈጥሮኣዊው የጾታ ልዩነት የተነሳ መሳሳብ አለ። ይኽን መሳሳብ የሚያመጣው ወንዱ በወንድነቱ የሚያሳየው ተፈጥሮኣዊው ባሕርይ ለሴቷ ይስባታል። ሴቷም በሴትነቷ በተፈጥሮኣዊ ባሕርይዋ የምትገልጸው ለወንዱ ይስበዋል።

ሁለቱ ወንድና ሴት (ባልና ሚስት) በመካከላቸው ያለውን የፍቅር ስሕበት ለመጨመርና ለማጠንከር ሌላ ምንም ዓይነት ለተፈጥሮኣቸው ባዕድ የኾነ ነገር አያስፈልጋቸውም። ተፈጥሮኣቸውን ራሳቸውን መኾን ብቻ ይበቃቸዋል።

አባወራዎቹ ራሳቸውን ይገዛሉ፣ ይመራሉ ይጠብቃሉም። ስነስርዓትና ስነምግባርን ይዘው ዓላማን ሰቅለው የሚጓዙ ናቸው። ለአቋማቸው ጽኑ ናቸው፤ ለፈለገው ነገር ግትር ከኾነው ዱርዬ በተቃራኒ።

ይኽን ነው እንግዲህ አባወራው ገብቶትና ፈጽሞት የሚገኘው ነገር ግን ምስኪኑ እና ሴታቆርቋዡ ወንድ (Feminist men) ደግሞ የማይቀበሉት፣ የማይኖሩት እና የማይኾንላቸውም።

እነርሱ ተፈጥሮኣዊ በኾነው የሰውነት ጥያቄያቸው መሠረት ሴትን ቢሹም የሚስቡበትን መንገድ ግን ስተውታል። በገንዘብ በስጦታና በውለታ ብዛት የሴትን ልብ መግዛት፤ በተናገረችው፣ በወሰነችው እና ባደረገችው ነገር ሁሉ በመስማማት ከሴቶች(ከሚስታቸው) ወሲብን ማግኘት የሚያስችል ይመስላቸዋል።

ነገር ግን ሴቶቹ ከምስኪንና ከሴታቆርቋዥ ወንዶች (Feminist men) በብዙ እንደመስማማታቸው ሳይኾን ቀርቶ ያ በአደባባይ የሚያሙትን፣ የሚኮንኑትን ዱርዬ ወንድ መርጠው (አባወራዎቹ ጥቂቶችና እንደልብም የማይገኙ ከመኾናቸው አንጻር) ጥለዋቸው ይሄዳሉ።

ይኽም እነዚኽን ሁለቱን ወንዶች ያበሳጫቸዋል። ምክንያቱም ግልጽ ነው፤ በኃሳብ የሚስማሟቸው እነርሱ፣ ውሳኔያቸውን የሚቀበሏቸው እነርሱ፣ አደባባይ ላይ ወጥተው “የሚሟገቱላቸው” እነርሱ ነገር ግን ልባቸውንም ኾነ ገላቸውን የሚሰጡት ለሌላ መኾኑ ነው።

እንደ ምስኪኖቹና ሴታቆርቋዦቹ ወንዶች(Feminist men) ሀሳብ ለሴቶቹ(ለሚስቶቻቸው) በኃሳብ መስማማትን፣ ያሉትን መቀበልን፣ ፍላጎታቸውን ማሟላትን ከፍለው በፈንታው መወደድን፣ መከበርንና ወሲብን መሸመት ይፈልጋሉ።

ተፈጥሮኣዊ ፈቃድንና መሻትን ተከትለው ሳይኾን እንደ ስጋ ገበያ አንዱን ከፍለው ሌላ መሸመት ይፈልጋሉ። ይኽም ለሴቶች ክብርና ፍቅር የሌላቸው ላልተሟላው እና የተፈጥሮን ሕግ ተከትለው ሊያሟሉት ላልቻሉት ድብቅ ፍላጎታቸው ደግሞ ሰጥቶ መቀበልን ከፍሎ መግዛትን የሚያስቡ ናቸው።
…….

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *