ሴቶች ውሸታም ባይሆኑም ቃላቸውን ግን አትመን

አንተ ይህን ገጽ ስትከታተል ለቆየኸው ወዳጄ ዛሬ ደግሞ የአባወራነት እውቀትህን የሚያጠነክርልህን ሌላ የተፈጥሮ እውነት ይዤልህ መጥቻለሁ።

ልብበል ተፈጥሮአችን ከእውነተኛው ፈጣሪ የተገኘ እውነት ነው። ተፈጥሮህን ማወቅህ የፈጠረህን የምታውቅበት ብሎም የራስህን የተፈጥሮ እውነት ከሠሪህ ከምንጩ የምትረዳበት እውቀት ነው። እውነት ደግሞ የኑሮህ አቅም፣ የነፃነትህ ምልክት እና ሕሊናህን የሚያሳርፍ ነው።

እኔ ጋር የዓለም አቀፍ ስምምነቶች፣የተባበሩት መንግስታት አንቀጾች፣የመንግስታት አዋጆች ተፈጥሮዬን እና የፈጣሪዬን ዓላማ የማይደግፉ ብለውም የሚያፈርሱ ከሆነ ቦታ የላቸውም።

አባቶቻችን ሲተርቱ “ሴትን ያመነ ጉምን የዘገነ” ይላሉ። ይህን ተረት በእርግጠኝነት የምነግርህ ዛሬ ላይ ብትተርተው ብዙ ሰዎች ይታዘቡሃል። ለምን ብትል ለሴት ልጅ “ክብርን የማይሰጥ” ብሎም “የሚያዋርድ” ሴት ልጅ በማሕበረሰቡ ውስጥ ያላትን ተአማኒነት “የሚንድ” አሉታዊ ተጽእኖ ያለው ሌላም ሌላም..ነው” ይሉሃል።

አንተ ግን ለፍርድ አትቸኩል። በተለይ አባቶችህ ያወረሱህ ቋንቋ፣ ኃይማኖት፣ጥበብ ዓለማዊ ሕይወትህን ከማቃናት በተጨማሪ ሰማያዊ ርስትን ገንዘብ የምታደርግበት ነው። ስለዚህም እንደዘመነኛው ወንድ ችኩል፣ ሆደ ባሻ፣ ስሜታዊ ሳትሆን የቆየልህን ቅርስ መርምር። ከውስጡም አንዳች እውነት፣ከዛም እውነት ማንነትህን ፣በማንነትህም እረፍትን ማግኘትህ ርግጥ ይሆናል። እኔ እና አንተ በአባወራነት ምርምር ከዚህ ተረት ምን እንማራለን?

ይህን ተረት የተረቱት የሴት ልጅ ተፈጥሮአዊ ባሕሪይ በዘመናት ሂደት እና ትዝብት ተረድተው ነው? ወይስ ተራቾቹ ያልተማሩ፣ለሴት ልጅ ጥላቻ ያላቸው ጠባቦች ስለሆኑ ነበር።…..

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *