ሴጋ (Masturbation) እና መዘዙ በአባወራው ቤት ላይ(የመጨረሻው ክፍል)

ሴጋን በመተውህ ስለምታገኘው ጥቅም

ባለፉት ሁለት ጽሑፎች ስለ ሴጋ አካላዊ፣ አእምሮኣዊና ስነልቦናዊ ጉዳቶች ስናይ ወሲባዊ ትዕይንት(Pornography) ደግሞ ቀንደኛ አቀጣጣዩ መኾኑን ታዝበናል። ዛሬ ደግሞ ሴጋን ስንተው ስለምናተርፈው እንጨዋወት።

ትርፍ ፩ አካላዊ ትርፍ ጉልበትህን ታተርፋለህ)

ሴጋን ስታቆም በፊት ልፍስፍስ የሚለው ሰውነት ወደ ተፈጥሮኣዊው አቅሙ ይመለሳል። የፊትህ መገርጣት፣ የሱሪህ መስፋት ይታገስሃል። ጠዋት ከአልጋህ ስትወርድ ድቅቅ የሚለው ወገብህ ዛል የሚለው ጡንቻህ ይቀራል። አካላዊ እንቅስቃሴ የምትሠራበት ጉልበትም ይኖርሃል። የቀን ውሎህም በኃይል ይታጀባል።

ወንድሜ የሚገርምህ ነገር ከዚያች ከጥቂት ደቂቃ ሴጋ በተቃራኒ ከሚስትህ ጋር የምትፈጽመው ወሲብ ከአንድ ሰዓት በላይ ቢፈጅም እንኳ በጋራ እርካታ እስከታጀበ ድረስ በቀን ውሎህ ንቁና ቆፍጣና ኾነህ ትውላለህ። ይኽ ደግሞ የወሲብን ተፈጥሮኣዊነት፣ አግባብነትና ፍቅር ገንቢነቱን የሴጋን ሰውሠራሽነት(artificial)ና አጥፊነት ትረዳበታለህ።

ትርፍ ፪ አእምሮኣዊ ንቃትና መነቃቃት

የንቃት መጠንህ መጨመር አንዱ ሴጋን በማቆም የምታተርፈው ነው። ጠዋት በጠዋት መንቃት፣ ንቃትህንም ለሥራ፣ ለተመስጦ፣ ለአካል ብቃት እንቅስቃሴ ወይም ለንባብ መጠቀም ትችላለህ።
አእምሮህ የሰውነትህ የዕዝ ማዕከል ነው። የፈለግከውን ለመሥራት የሰውነትህንም ሙሉ አቅም ለመጠቀም አእምሮህ ንቁ መኾን አለበት። የአእምሮን ተፈጥሮአዊ ንቃት ለመጠቀምና ለማጎልበት ሴጋን ማቆም መፍትሔ ነው።

ትርፍ ፫ ሴትን ለመጥበስ፣ ለመጀንጀን ለመዋሰብም(ከሚስትህ) ወኔ ተነሳሽነት ይኖርሃል

ዘወትር ሴጋ የምትመታ ከኾነ ሴትን (ለመተዋወቅ)ለመጥበስ፣ ለመግባባት(ለመጀንጀን) ወኔ ያጥርሃል ወይም አትፈልግም። ምክንያቱ ደግሞ ደፍረህ ሴትን እንድትተዋወቅ የሚያደርግህን ፍላጎቱንም የሚያሳድርብህን የወሲብ ስሜት በሴጋ ገድለኸዋልና።

ወንድሜ ማናችንም ከተቃራኒ ጾታ ጋር የምንመሠርተው የፍቅር ግንኙነት በወሲብ ፍላጎት ጠንሳሽነትና በእርሱም ዙሪያ ያጠነጥናል። አንተ ለሴት ልጅ ያለህ መውደድ፣ ከእርሷም ያለህ ፍላጎት ተፈጥሮኣዊና ጤናማ ነው። ማንም ፍጡር በራሱ ስልጣን ጎትቶ ያመጣው ሳይኾን ፈጣሪ በጥበቡ ያስቀመጠው እንጂ።

በተለይም አንተ አግብተህ እና በትዳር ተወስነህ መኖር የምትፈልገው ወንድሜ ወሲባዊ ፍላጎትህ በዐላማ የተሰጠህ ነውና አትሰቀቅበት፣ የሚያሳፍርም አይደለምና አትደብቀው፣ ለትልቅም ዐላማም ተሰጥቶሃልና በሥርዓት ያዘው፣ ጠብቀው፣ ተረዳው፣ እንደዘራኸውም ታጭድበታለህና በአግባቡ ተጠቀምበት።

ሴጋን ስትመታ በተፈጥሮኣዊው ወሲብ ሳይኾን በሰው ሠራሽ(Artificial) መንገድ ፍላጎትህን በድብቅ፣ ማስተንፈስህን እወቅ። ከዚህም የተነሳ በአደባባይ ውሎዎችህ ከምታገኛቸው ሴቶች መካከል ለፍቅር ለትዳር ጓደኝነት ራስህን ከማጨት ይልቅ ምርጥ ጓደኛ(best friend) ኾነህ ታርፈዋለህ። ከዚህ ይልቅም ሴቶችን ፍለጋ social media አልያም “እናጋባለን” የሚሉ አካላትን ትጎበኛለህ።

ሴጋን ስታቆም ግን ይኽ ኹሉ ታሪክ ይኾንና የማግባት ጥቅሙ፣ የሴት ልጅ ውበቷ፣ ላንተ የመሰጠቷ ምክንያትና እርሷን የመጠየቅ፣ የመግባባት የመተኛት ወኔውን ትታጠቃለህ።

ትርፍ ፭ ስንፈተ ወሲብን ትሰናበተዋለህ(ሌላ የጤና እክል ከሌለብህ)

ዛሬ ዛሬ ስንፈተ ወሲብን ለጊዜውም ቢኾን ለማስወገድ ትልቁም ትንሹም መድኃኒት ቤት ተሰልፎ ቫያግራ ሲገዛ ይታያል። ወንድሜ የዚኽ ዘመን አይደለም ያዛውንቱ የወጣቱ ችግር እየኾነ የመጣው ባሎችን አንገት ያስደፋ ሚስቶችንም በትዳራቸው ያስከፋ ክፉ በሽታ ስንፈተ ወሲብ ነው። ቫያግራ ደግሞ ግን በሐኪም የችግሩ መነሻ ታውቆ እስካልታዘዘ ድረስ ችግሩን የበለጠ ያከፋዋል እንጂ መፍትሔ አይኾንም።

መፍትሔው ግን መጀመሪያ የወሲብ ትዕይንቶችን ማየት ማቆም፣ ሴጋህን መተውና ቫያግራን አለመጠቀም ናቸው።

ጀግናው ወንድሜ!

ያንተ ታላቅ ወንድም አድርጌ ራሴን በራሴ ስልጣን ቀብቻለሁና ያለፍኩበትን፣ የበረታኹበትንና የወደቅኹበትን አካፍልሃለው። እኔን እንድትታዘብ ሳይኾን ከጥንካሬዬ እንድትወስድ እንድትጨምርበትም፣ ከስሕተቴ ተምረህ እንዳትደግመው፣ ካነበብኩትም እንድትጠቀም እንጂ። ይኹንና እርማትህንና አስተያየትህን አከብራለሁ።

ይኽ ስለምወድህና ስለምወድህ ብቻ ነው።

ዐለም ብዙ የሚጣፍጡ እውነት የሚመስሉም ነገር ግን ጎጂ ውሸቶች አሏት። የፈለግነውን እውነት እግዚአብሔር በገለጸልንና በተረዳነውም መጠን (በተለይም ከተፈጥሮአችን፣ ከትዳር፣ ከወሲብ ጋር በተያያዘ) እንካፈላለን።

ብንኖር ምስጋና ባንተ ሕይወት ውስጥ ስላለው ቦታ ….. ይቆየን

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *