ሴጋ(Masturbation) እና መዘዙ በአባወራው ቤት ክፍል(፪)

ጉዳት ፮ ለስንፈተ ወሲብ ይዳርግሃል

ውድ ወንድሜ! እኔ ይኼን ስጽፍልህ ትማርበት ዘንድ በእርሱም ፈጣሪ የሰጠህን ጸጋ በአግባባቡ ተጠቅመህ ትዳርህን ታተርፍበት ዘንድ ነው። እርግጠኛ ኾኜ የምነግርህ ከላይ ከዘረዘርኩልህ ጉዳቶች በላይ ሴጋ ለስንፈተ ወሲብ እንደሚዳርግህ ነው።

ብዙዎች እንደመዝናኛ ቆጥረው የተጠመዱበት የወሲብ ትዕይንት(pornography) ለዚህ ክፉና ጎጂ ልማድ ዳርጓቸዋል፤ ይኽም በፈንታው ይኾናል ብለው ያልጠረጠሩትን ችግር አስከትሎባቸዋል።

በተለይ አንተ በትዳር ውስጥ ያለኸው ወንድሜ ሚስትህን ለምን አገባሃትና ነው የእርሷን ፍላጎትና ፈቃድ የምትፈጽምበትን የወሲብ ኃይል አሟጠህ የምትጨርሰው?

ከላይ የጠቀስኳቸው የንዑሳን ችግሮች ጥርቅም የኋላ የኋላ ከሚስትህ ጋር ምንጣፍህ ላይ ስትወጣ ጉልበትህ እንዲከዳህና ስንፈተ ወሲብ ለተባለም ዐቢይ ችግር አሳልፎ ይሰጥሃል።

ወንድሜ! ምክንያቱ ምንም ይኹን ምን ወሲብን ከሚስትህና ከሚስትህ ጋር ብቻ ፈጽም። “ሚስቴ ብዙ ጊዜ ፈቃደኛ አይደለችም የት ልኺድ” ካልከኝም ከእርሷ ሌላ የትም አትኺድ። እርሷን ከመውቀስ በፊት ግን አንተ ግዴታህን ተወጣ።

ዳቦ ገዝተህ ከመምጣት የወር ወጪም ከመስጠት በበለጠ የሚስትህ ተፈጥሮኣዊ ጥያቄ መመለስ አለበት። ይኼንንም ለማድረግ ክፉና ጎጂ ልማድህን(ሴጋ) አስቀር። ገንዘብህ፣ ዘርህ፣ የትምሕርት ደረጃህ ሳይኾን በመጀመሪያ ደረጃ ወንድነትህ ማርኮ ወዳንተ እንዳመጣት አትዘንጋ።

ሰው እንዴት ከሴቶች መሐል ሚስቱን የጠራበትን፣ ከወንዶችስ መሐል በሚስቱ ያስወደደውን ወንድነት በራሱ እጅ አጥፍቶ በወደደችው ሚስቱ ራሱን ያስንቃል። ሚስትህ እንድትንቅህ፣ እንድትጠላህ፣ በአንተ ላይም እንድትሄድና እንድትፈታህ እስካልፈለግህ ድረስ ሴጋህን አቁም።

በትዳር ውስጥ ላለ ወንድ ልጅ እንደ ስንፈተ ወሲብ የሚያስጨንቅ፣ የሚያሳቅቅ በሚስትም የሚያስንቅ ምን አለ። ሚስትህ እኮ አንተ ምን የአደባባይ ጀግና የእልፍኙም ጌታ ብትኾን በምንጣፍህ ላይ ፈቃዷን ጀምረህ መጨረስ እስካቃተህ ድረስ በአደባባይም ኾነ በእልፍኝ በድፍረት ትንቅሃለች። አንተም ጉድህን ታውቀዋለህና እንዳይገለጥብህም ትሻለህና ሰዎች ንቀቷን አይተው እንዳይናገሯት ታስተባብልላታለህ።

በተለይ በዘመናችን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ወንዶች ለስንፈተ ወሲብ ለመጋለጣቸው የወሲብ ትዕይንት(pornography) እርሱን ተከትሎ የሚፈጸመውም ክፉውና ጎጂው ሴጋ ከፍተኛ አስተዋጽዖ አላቸው። ከዚህም የተነሳ የወሲብ ማነቃቂያ መድኃኒቶች ሕገወጥ ዝውውርና የተጠቃሚው መብዛት ጥሩ ማሳያ ነው።

በቅርብ ጊዜ የመድኃኒቶችን ሕገወጥ ዝውውር የሚቆጣጠረው መንግስታዊ ተቋም የኮትሮባንድ መድኃኒት እንደበዛና ዋነኛው ደግሞ የወሲብ ማነቃቂያ ተብሎ የሚሸጠው ቪያግራ እንደኾነ ተጠቅሷል።

በሌላ በኩል ደግሞ የሴታቆርቋዦቹ(Feminists) ወሲብን በድርድርና በስምምነት እንጂ ትዳር ስለተያዘ መኝታ ቤትም ስለተገባ የሚፈጸም እንዳልኾነ ሴቷንም እምቢ የማለት መብት እንዳላት ይከራከራሉ።

ይኽ ሲኾን ጤናማና ተፈጥሮኣዊ የወሲብ ፍላጎቱን ከሚስቱ ሌላ ባለመኼድ መተንፈስ የሚፈልገው ወንድ(በተለይም የዘመናችን ምስኪን ወንድ) ሴጋን እንደማስተንፈሻ ይጠቀምበታል።

አንተ ግን እንዲህ እንዲኾን በጭራሽ አትፍቀድ። ወሲብ ተፈጥሮኣዊ ስጦታ ስሜቱም ጤናማ እና አስደሳች ሲኾን አፈጻጸሙ ግን አግባብነት ባለው መንገድ የእኔ ካልከው ሰው ጋር እንደአመጣጡ ቅጽበታዊነት ሲኾን ነው። አልያ ግን በቀጠሮ፣ በድርድርና ድግግሞሹም በተራራቀ ቁጥር ፍላጎትህን ለማስተንፈስ ወደ ሴጋ መወሰድህ አይቀርም።

ወደ እዚህ ክፉና ጎጂ ልማድ ስትኼድ ደግሞ ለስንፈተ ወሲብ መጋለጥህ የማይቀር ነው። ይኽም ትዳርህን በእጅህ እንደማፍረስ ይቆጠራል። አንድ ሰው የሚኖርበትን ቤት መራጃ(ትልቅ የድንጋይ መዶሻ) አንስቶ ቢያፈርስ ታመመ አእምሮው ተለወጠ ቢባል እንጂ ጤነኛ እንዳያስብለው። አንተም ሚስትህ ወሲብ ብትከለክልህና ከፍላጎትህም የተነሳ ብትቸገር ሴጋ መሞታቱ ለጊዜው ውጥረትህን ቢያረግብልህ ችግሩን ግን ከድጡ ወደ ማጡ ይወስደዋል።

የወሲብ ትዕይንቶች(pornography) መተው ፈልገህ አለኾን ብሎሃል ሴጋንስ ውስጥህ እየተሟገተብህ መልሰህ ግን ራስህን እዛው ታገኘዋለህ?

እንግዲያውስ ከሙያም አንጻር ኾነ ትውልዳችን ብሎም ሀገራችን የተጋረጠባትን ይኼንና መሰል ክፉና ጎጂ ልማዶች ለመፍታት #Bete Saida ማዕከል ይጠብቁሃልና እርዳታን ማግኘት ትችላለህ።

ብንኖር ሴጋን ስንተው ምንና ምን እናተርፋለን?….. ይቆየን

https://www.facebook.com/2096961580575530/posts/2241894866082200/

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *