ጤና ይስጥልኝ

ጤና ይስጥልኝ 1

ይኽ የአባወራ ድረ-ገጽ የእኔ የሄኖክ ኃይለገብርኤል የግል የጡምራ ገጽ ነው። ድረ-ገጹ ላለፉት አሥራ ስምንት ወራት በFacebook ስጽፍበት የነበረው ገጽ “አባወራ” ፍሬ ነው።

ይኼን ለማዘጋጀት ምክንያት የኾነኝደግሞ በዘመናችን የሚታየው የወንዶች (እኔን ጨምሮ) መልፈስፈስ (በአካል፣ በአእምሮ፣በመንፈስ) ነው።

ሲቀጥልም ዛሬ ዛሬ በእኩልነት ሰበብ ትዳርን በሁለት ሰው ለመምራት መሞከር፣ አልያም ከፉክክር የተነሳ መሪ አልባ መኾን፣ ወንዶችም የመሪነት ሚናቸውን መወጣት አለመቻል ምክንያቶቼ ናቸው።

በተለይም በወንዶች በተፈጥሮአዊው ወንድነታቸው ውስጥ ያለውን ኃይል(አቅም) ኾነ ዓላማው ተዘንግቷል። ይኽ ደግሞ በራሳቸው በወንዶቹምኾነ በቤተሰባቸው፣ በማሕበረሰቡ፣ በትውልድና በሀገር ሕልውና ላይ አደጋ ጋርጧል።

አነርሱም፦

በራሱ በወንዱ ላይ
ራሱን በስነምግባር፣ በእውቀት፣ በአካል ብቃት ብቁ ዜጋ ያለመኾን። ከዚህም የተነሳ ግለሰባዊ፣ ማሕበራዊና ሀገራዊ ግዴታዎች(ሚናዎች) ለመወጣት መሳን(ማቃት)ናአለመፈለግ።

በትዳር
በዓለም ላይ ያሉት የትኛዎቹም ተቋማት ምን ትልቅ ቢኾኑ በአንድ ግለሰብ በኃላፊነት ይመራሉ። ዛሬ ላይ የምናየው የትዳር ተቋም ግን በሁለቱ ሰዎች(በባልና በሚስት) እኔ ልምራ እኔ ልምራ ፉክክር ከመቆም ይልቅ መፍረስ ሲቀናውይታያል።

ሚናውን የተረዳ ወንድ ሲጠፋም ትዳሮች ወሲብ የለሽ ይኾናሉ።

በቤተሰብ
መሪ፣ መካሪ፣ ዘካሪ፣ ተቆጪ፣ ቀጪና ተፈሪም የሌለበት ይኾናል።

ትውልዱ
-ፍዝና ግድ የለሽ
-ግለኝነት፣ ራስ ወዳድነት፣ ሴታውልነት፣ ሴሰኝነት፣ ሱሰኝነት፣ ሌብነት የሚያደንቅ የሚያበረታታና የተዘፈቀበትም ይኾናል
-ኃይማኖት እንጂ እምነት አልባ(ፈሪሃ እግዚአብሄር የሌለው) መኾን
-ጾታው የተምታታበት አልያም ጾታ የለኝም(ዘመን አመጣሽ) የሚል አለባበሱም ኾነ አኳኋኑ እንዲሁ የኾነ
ሀገር
የሀገር ዕጣ ፋንታም ባለቤት አልባ መኾን ነው
ወንዶችና ሴቶች ከመራቢያ ክፍሎቻቸው ባሻገር የጾታ ልዩነቶቻቸው በምክንያት ለዓላማ የተሰጣቸው መኾኑን አምናለሁ። ይኽ ድረ-ገጽም ለየቅል የኾኑ ጸጋዎች ባለቤት መኾናቸውን በመመርመርና በማሳወቅ ገንቢ አስተዋጽዖ እንደሚኖረው ተስፋ አደርጋለሁ። በዚህም ጤናማ ትዳር፣ቤተሰብ፣ኃላፊነት የሚሰማው ትውልድ ብሎም ጠንካራ ሀገር እንገነባለን።
መልካም ቆይታ
ሄኖክ ኃይለገብርኤል ተስፋዬ