ቅርፊቱን በእውነት መዶሻ

አንተ ራስህን ስትቀበል ብቻ ነው አንተነትህን ወደተሻለ ማንነት የምታሳድገው። ወንድነትህን ዱርዬነት፣ አሸባሪነት፣ አደገኛ ቦዘኔነት፣ ትዕቢተኝነት፣ ጋጠወጥነት፣ አምባገነንነት፣ ግትርነት፣ ጨቋኝነትና የመሳሰሉትን የሚሉህን እየሰማህ ካደግክ ማንም ሳይጨመር ቀንደኛ የወንድነትህ(የራስህ) ጠላት አንተው ራስህ ትኾናለህ።

አንተ የተጠየፍከውን “ከመዝናናትና ከማዝናናት” ውጪ ሚና የሌለው ወንድነትህ ደግሞ ከፈጣሪህ የተሰጠውን የመምራትና ትውልድንም ወደ እርሱ ዐላማ የማድረስ ሚና መወጣት አይችልም።

ይኹንና ይህ ሚና እራሱ ዛሬ ዛሬ ከሊቅ እስከ ደቂቅ ከጌታ እስከ ሎሌ ባለው ዐለማዊ ሥርዓት ውስጥ ራሱ አጠያያቂ እየኾነ መጥቷል። እኛ ራሳችንን ወደ ፈጣሪ ቃል ከማምጣት ይልቅ “ጥበብ” ላልንነው የዓለም ሞኝነት ተላልፈን ተሰጥተን የእግዚአብሄርን ቃል ጊዜው ያለፈበት አድርገን እንሞግታለን። ይኽንንም እንደ ዐዲስ አስተሳሰብ በየተቋማቱ እንሰማዋለን መሪዎቻችንም ደጋግመው ይነግሩናል።

ወንድሜ በሰው ዘር ላይ አምባገነን የኾኑ ብዙ ጉስቁልናም በዓለም ላይ ያደረሱ ሰዎች(ወንዶች) በተለያየ የታሪክ አጋጣሚ ዐለም አስተናግዳለች።ይህ የታሪክ ስህተት ግን የወንድነት ችግር፣ የስልጣን ሰጪውም ስህተት አይደለም። ስልጣኑማ አግባብነት ካለው የማስፈጸሚያ ጸጋ ጋር ተሰጥቷቸው ነበር። ነገርግን የሰዎቹ በተሰጣቸው ስልጣን አላግባብ መጠቀም እንጂ።

የዚኽ መፍትሄ ደግሞ ወንዶችን ከቤተሰብ ጀምሮ ካለው አመራርነትማንሳት ሳይኾን ሥልጣናቸውን በጉልበታቸው ያላገኙት በስጦታም ከፈጣሪ በምክንያት የተቸራቸው መኾኑን ማስተማር ነው። አልያ ግን በእርሱ ሥራ ገብቶ ያላዋቂ ሳሚ ሥራ መሥራት ይኾናል።

ወንዶች ቤታቸውን መምራት ካልቻሉ ወደ መምራቱ ብቃት ማምጣት እንጂ የፈጣሪን ዐላማ ማስፈጸሚያ የኾነውን ቤተሰብ መመሪያ(manual) (ወንድ የቤቱ ራስ መኾኑን)አሽቀንጥሮ ዐዲስም አስተሳሰብ ብሎ ከዐለም እብደት ጋር አሸሼ ገዳሜ አያዋጣንም።
፩ ወንድሜ! በተሰጠህ የተፈጥሮ ጸጋ መጠን እንዳትዘረጋና እንዳትሞትም እንዳታድግም የሚያደርግህ ቅርፊት አጥር እንዳለ አስተውል።

፪ በሙሉ አቅምህም፣ ወደ ተፈጠርክበት ዐላማም እንደፈጣሪህ ኃሳብና ፈቃድ የምትኖረውይኽንን የዐለም “ጥበብ” ነገር ግን ሞኝነት የኾነ ቅርፊት ስታፈርስ ነው።
፫ አንዴ ከቅርፊቱ ወጥተህ የነጻነት ዐየር መተንፈስ ከጀመርክ በኋላ ግን ወደ ኋላ መመለስ የለብህም።
👌 በወንድነትህ በተለይ የተሰጠህን ጸጋ አስረግጠህ እወቅ
👌 የተሰጠህ ኹሉ መልካም እንደኾነና ለመልካምም እንደኾነ አንዳችም ሕጸጽ እንደሌለበት እወቅ
👌 በዓላማ በምክንያት የተሰጠህን ጸጋ ለበጎ ምግባር፣ በአግባብም እንድትጠቀምበትና በከንቱ እንዳይባክንም ተጠንቀቅ

ማጠቃለያ
ወንድነትህ ራስህን፣ ቤትህን፣ ዐለምን የምትመራበት ስልጣን ነው።ለአፈጻጸሙም በተፈጥሮኣዊ ጸጋ የታገዘ፣ አምላካዊም ትዕዛዝ ነው።

የትኛውም የዐለም አሠረራር ከዚህ ተቃርኖ ከቆመና እንድትቀበለው ግድ ቢልህ የአንተን እድገት የሚገታ፣ ወደ ተፈጠርክበትም ዐላማ እንዳትደርስ የሚያግድህ የጠላት ቅርፊት ወይም አጥር ነው።

ይኽን ቅርፊት መስበር አጥሩንም ማፍረስ አንተን ብቻ ነጻ የሚያወጣ ሳይኾን ትውልድንም የሚታደግ ነው።

ብዙኃኑ በጠላትነት እንደሚነሱብህ ሳትርሳ።
….ይቆየን

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *