በመሪነት ሚናህ የሚስትህ ተግዳሮት፣ ምንጩ….

ያንተን የመሪነት ሚና እንደራስህ ስብዕና የሚፈትነው የለም(ያለፈውን ጦማር አንብብ)። በኹለተኛነት ግን ሚስትህ ናት። በተለይም ደግሞ አባቷ መክሮ ገስጾ ተቆጥቶ እና ቆንጥጦ ያላሳደጋት ልጅ ከኾነች። በተጨማሪም በሴታቆርቋዡ አመለካከት(Feminism) የተወሰደች(የተነጠቀች) ከኾነች ጭርሱን ውጤታማ አትኾንም።

ይኹንና እነዚህ ፈተናዎች የማታ የማታ ትዳርህን ዋጋ እንዳያስከፍሉት ከፈለግህ በሚስት ምርጫህ ላይ የአባቷን ልጅ አስቀድም። ናፖሊዮን ሂል የተባለው ጸሐፊ በThink and Grow Rich መጽሐፉ ላይ “The most important decision you will ever make is the selection of a wife.” ይላል። ለትዳርህ ስኬት መሠረት የምትጥለው ኹነኛ ሚስት የመረጥክ ዕለት ነው።

የቤትህ አባወራ(መሪ) መኾንህን አምና ደስም ብሏት የምትቀበለው ኹነኛ ሚስት ደግሞ የአባቷ ልጅ ናት። የአባቷ ልጅ የኾነችዋ በሴቷቆርቋዡ(Feminism) ከተወሰደችው በተለየ መልኩ ጤናማ የኾነ በራስ መተማመን እንዲሁም አክብሮት ለወንዶች አላት። እርሷ ስኬታማና ደስተኛ መኾንን አጥብቃ ትሻለች። “ማን የማይፈልግ አለ?” ብትለኝ ብዙዎች በአፍኣ(ውጭ ውጪውን) “መወደድን እሻለሁ” ቢሉም በውስጣቸው ግን ይኼን የሚሰጣቸውን አጋጣሚም ኾነ ሰው የሚያጨናግፍ ሥራ ይሠራሉ ምክንያቱንም አይረዱትም።

ይኽ እንግዲህ ካላቸው ደካማ የራስመተማመን(በመላ ማንነታቸው) ይመነጫል እርሱም ከአስተዳደግ። ለአንዲት ሴት ልጅ ታዲያ ከአባቷ ጋር ያላት ጤናማ ግንኙነት ወንድን እንድታምንና በጠቅላላው ከወንዶችም ጋር ጤናማ ግንኙነት እንድትመሠርት ያስችላታል።

ስታድግ(ስትልቅ) በርቺ፣ ስትወድቅ አይዞሽ፣ስታጠፋ ለምን ብሎ(መክሮ ቀጥቶ) በሚያሳድግ አባት እጅ ያለፈችን(ያለችን) ልጅ ነው እንግዲህ የአባቷ ልጅ የምንላት።

ምርጫህን አስተካክለህ ያገባሀትን ሚስት ታዲያ በዐለማዊ አቋሟ ሳትታለል ልትመራት ግድ ይልሃል። የሚስትህ ቁንጅና፣ የሚስትህ የትምህርት ደረጃ፣ የሚስትህ የቤት ውስጥ ባለሙያነት በቤትህ ካስቀመጥከው ሥርዓት(ሕግ)ለማፈንገጥ ሰበብ ሊኾናት አይገባም።

ሚስትህ ዶክትሬት፣ ማስትሬት አላት? እሰየው፤ ሚስትህ የድርጅት የአንድም መምሪያ ኃላፊ ናት?
እሰየው፤ ሚስትህ መንፈሳዊ(በተለመደው አባባል) ናት? እሰየው፤ ሚስትህ የጦር አለቃ የኢታማዦር ሹም ናት? እሰየው፤ ወይንም አንድ ሚንስቴር መሥሪያቤት ሚንስትር ናት? እሰየው….ወዘተርፈ። ይኽ ኹሉ ግን አንተን ለሚስትህና ለልጆችህ ይሄዱበትም ኾነ ይከተሉት ዘንድ የሚኾን ልከኛ ሕግ ከማውጣት እርሱንም ከማስጠበቅ ሊያግድህ አይገባም።

ልብ አድርግ! በቤት መሪነትህ ሚስትህ ልታከብርህ የተገባህ ነህ። ይኽ አምላካዊ ትዕዛዝ ተፈጥሮኣዊም ሥርዓት ነው። ሚስቴ አታፈቅረኝም ብለህ ኾድ አይባስህ እወድሃለሁ ብትልህም እስክትወልድ ነው ልክም ነች። ሴት ልጅ ባሏን ታከብራለች(ታደንቃለች) ልጆቿን ትወዳለችና።

ይኼን አውቀህ አግባ አግብተህም ፈጽም።

ልጆች
ልጆች የሚያሳዝኑ የሚያሳሱ ቢኾኑም እንኳ በፈሪሃ እግዚአብሄር፣ በሰው መውደድ፣ በሀገር ፍቅር ያድጉ ዘንድ በሥርዓት ልታሳድጋቸው ይገባል።

ዛሬ በፍቅር ሰበብ በሥርዓት ባያድጉ ምን ጭምት ምን ምኹር ቢኾኑ አንተን ከማስወቀስ፣ ሕዝብን፣ መንግስትን፣ ሀገርንም ከመበደል አይመለሱም። ያልዘራኸውን፣ ያላረምከውን አታጭድምና።

ቤተሰብ
ወንድሜ የቤትህ መሪ አንተ ነህ። ያንተ በርነልቦናም ኾነ በዓለማዊ ኑሮ አለመበርታት በቤትህ ላይ ማንም እየመጣ እንዲፈነጭ እድል መስጠት ነው። በተለይ ደግሞ ምስኪን ከኾንክ አበቃልህ። በቤትህ ኾነው ቤትህን ያፈርሳሉና።

ማጠቃለያ፦ ራስህን ከማሸነፍ በስንፍና፣ ሚስትህንም ለመምራት በፍርኃት፣ ልጆችህንም ለመቅጣት ስስት፣ ቤተቦቻችሁንም ለመሞገት በይሉኝታ ታሥረህ ከቀረህ ትዳርህ እያደር መናዱ አይቀሬ ነው።

እንዲህም ተብሏል “marriage is an adventure, like going to war” Gilbert K. Chesterton
…. ይቆየን

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *