በሥነ-ስርዓት ያላሳደግነው ትውልድ በሕግ ብዛት አይቃናም

ክፍል፪

አስገድዶ ደፋሪዎች ምንም እንኳ ፊት ለፊት የሚታይ እና ይኼነው ተብሎ የሚነገር የአእምሮ ችግር ባይታይባቸውም ነገር ግን ከአስተዳደግ ጉደለት/ በደል የተነሳ ይኽንን አስነዋሪ ተግባር ይፈጽማሉ።

ስሜታቸውን መግራት፣ መግዛትና በእርሱም ላይ መሰልጠንን አልተማሩምና።

ይኽ የአስተዳደግ ጉድለትም ኾነ በደል ታዲያ በእነርሱ ላይ የሚያሳድረውን የጠባይ ተጽዕኖ እነርሱ ራሳቸው ሳያውቁት የሚኖሩ፣ ሲከሰትም ከድርጊቱ በኋላ ክፉኛ የሚጸጸቱ፣ ነገር ግን ጊዜ፣ ቦታና ሁኔታን ጠብቆ ሲመጣ ካደረጉት በኋላ የሚቆጫቸው አብሮ-ኣደግ ነው።

ይኽ የአስተዳደግ ጉድለት/በደል ከላይ እንደጠቀስኩት በግልጽ ስለማይታወቅ ፈጽሞ ያደርጉታል ብለን በማንጠብቂያቸው እና በማንጠረጥሪያቸው ሰዎች ይኽ ከፉ ድርጊት ይፈጸማል።

ይኽም ችግሩን ሲከሰት ለማወቅ፣ ከታወቀም በኋላ መፍትሔ ለመስጠት እና ከዚያም በኋላ ዳግም እንዳይከሰት የማድረግ ሂደቱን ውስብስብ ያደርገዋል።

ይኽ ክፉ ድርጊት የአስተዳደግ ጉድለትና በደል ነው ብዬሃለሁ፤
፩ኛ የአስተዳደግ ጉድለት ስል

፩ኛ ሀ አንድም ልጆች በሥነ-ስርዓትና ሥነ ምግባር ታንጸው ያለማደጋቸው ውጤት

፩ኛ ለ አንድም በሥነ-ስርዓት እና ምግባር የሚያሳድግ ወላጅ በተለይም አባት ያለመኖር ውጤት

፩ኛ ሐ ጤናማ ጾታዊ አስተዳደግ ላይ ከፍተኛ ሚና የሚጫወተውን የወንዳወንድ አባት (በአካል ቢኖርም ወንዳወንድ ሳይኾን) የማጣት ውጤት

፪ኛ የአስተዳደግ በደል ስል

፪ኛ ሀ በልጅነት የተፈጸሙ ጾታዊ ጥቃቶች
፪ኛ ለ በልጅነት የሚታዩና በአእምሮ የሚቀረጹ ጾታዊ ግንኙነቶች(pornography) በተለይ በከተሞች ላይ መስፋፋት

መፍትሔ
፩ኛ ልጆችን በሥነ-ስርዓት እና ሥነ-ምግባር ለማሳደግ ቁርጠኛ ፍላጎትና ውሳኔ ይኑረን

፪ኛ ልጆችን በሥነ-ስርዓትና ሥነ-ምግባር የማሳደጉን ሚና በዋነኛነት እንዲሁ ላደገ አባት መተው(በዋነኛነት)

፫ኛ ወንዶችን ጤናማ የወንዳወንድ ጠባይ እንዲኖራቸው ማገዝ፤ …….

https://t.me/abawera

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *