በራስ መተማመንን ከአባት(ተፈጥሮኣዊ ስጦታ)

 

አንተ ለሚስትህም ኾነ ለትዳርህ፣ ለልጆችህም ኾነ ለቤተሰብህ፣ በምታደርገው ጥበቃ (ይኽም አእምሮአዊ፣ መንፈሳዊም ኾነ አካላዊ) ብቁ ኾነህ መገኘት አለብህ። ይኽ ብቃትህ ነው የራስመተማመንን የሚሰጥህ። በራስመተማመንህ ደግሞ ባታገባ በዙሪያህ ባሉ ሴቶች በአብዛኛው ብታገባ በሚስትህ ዘንድ ተፈላጊነትንና ተወዳጅነትን ያስገኝልሃል።

ወንድሜ ይህ ተፈጥሮአዊ እውነት ነው። ከምስኪንነትህ የተነሳ ይኼን እውቀት መገንዘብ ቸግሮህ “ሴቶች የሚንከባከባቸውን ሳይኾን የሚንቃቸውን ይፈልጋሉ” እያልክ አትማቸው።
ትዳርህን ማትረፍ በዚህም ሚስትህን ማስደሰት ትሻለህን? እንግዲያውስ ተፈጥርኣዊ እውነትን ጨብጠህ በራስ መተማመንህን አበልጽግ።

አንተ ይኽን ጽሑፍ በምታነብበት ወቅት ከአባትህ ሥር ኾነህ ለመማር ጊዜው ተላልፎሃል። ይኹንና ነገ አባት የምትኾንበት የቀጣይ ትውልድን ዕድል ፈንታ በአስተዳደግህ የምትወስንበት ነውና አስተውለህ ተከተለኝ።

አባት ለልጆቹ ስነልቦናዊም እና አእምሮኣዊ ደኅንነትም ኾነ እድገት የሚጫወተው ሚና ቀላል አይደለም። አባት በመጀመሪያዎቹ የልጆቹ እድሜ ላይ የሚኖረው ቅርርብ እስከ እለተ ሞታቸው ድረስ ለሚኖራቸው የጓደኛ እና የፍቅር ሕይወት እንዲኹም ለሚመሠርቱት ትዳር፣ ለሚያፈሯቸው ልጆች እና ለሚመሩት ቤተሰብ ጉልህ ሚና ይጫወታል።

በተለይ ወንዶች ልጆችን አስተውለህ ከኾነ በብዙ የእለት ተእለት ንግግራቸውና ድርጊታቸው የአባታቸውን ፈለግ ለመከተል ይጥራሉ። አቀማመጡን፣ አረማመዱን፣ አመጋገቡን፣ አነጋገሩን፣ አቆጣጡን፣ ድፍረቱን፣ የሥራ እልኹን እና ሌሎችንም አኳኋኖቹንም እንዲሁ ለእነርሱ አባታቸው አርአያቸው ነው። ከእርሱ የወሰዱትንም ኾነ የራሳቸውንም ድርጊት የሚያበረታታላቸውም ኾነ የሚደግፍላቸው ከኾነ በራስ መተማመናቸው ይጨምራል።

ስለዚህም ከአባታቸው ጋር ጥሩ ቅርርብ ያላቸው ልጆች ለራሳቸው ከሚሰጡት ቦታ አንጻር የሚኖራቸው አመለካከት ጤናማ እና ጠንካራ ይኾናል።

አንተ የልጅህን በራስ መተማመን በእነዚህ ትጨምራለህ
1. ውጤቱ ምንም ይኹን ምን በራሱ ተነሳሽነት የሚሠራውን ሥራ አበረታታው፤ አድንቅለትም።
ላንተ ፍጹም ተራ ነገር ቢመስልህም ለእርሱ ግን ካንተ ከሚወደው ትልቅም ቦታ ከሚሰጠው አባቱ ይኼን መስማት የአንድ ስቴድዬም ሙሉ ደጋፊን ጭብጨባ እንደማግኘት ነው። በዚህም “ጀግና ነህ፣ ትችላለህ፣ ድንቅ ነህ” የሚሉ ሙገሳን አዘውትረህ ለግሰው።

2. አዳዲስ ነገሮችን ለማወቅ እና ለመሞከር ያለውን ዝንባሌ አበረታታለት
ዛሬ አንተ የምትሰጠው ማበረታቻ ለነገ የሥራ ፈጠራዎቹ መሠረት ነው።አዲስ ነገር እንዲሠራ ሲሠራም እንዲኮራ “ጀግና በለው”።

3. ፈጣሪውን እንዲያውቅ አስተምረው
አንተ ኹልጊዜ ከልጅህ አጠገብ አትኾንምና አንተ በሌለህባቸው ጊዜያቶች ኹሉንቻይ የኾነው ፈጣሪ አብሮት እንዳለ በእርሱኹሉ እንዲቻለው አስተምረው። ተፈጥሮውን፣በተፈጥሮው ውስጥ ያለውን አቅም እንዲኹም ከእርሱ ውጭ ስላለው ተፈጥሮ አስተምረው።

4. ጀግናው አንተ ነህ
ጀግናው አንተ ነህና በሥራህ፣ በጨዋታህ፣ ጀግንነትን አሳየው። አንተ ራስህ ጠዋት በመነሳት በጠዋት እንዲነሳ ሥራን እንዲወድ፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እንዲያደርግ ራሱን እንዲጠብቅ አንተ እያደረግህ አስተምረው። ሙከራዎቹንም ኹሉ አድንቅለት።

5. ከስኬትህ ብቻ ሳይኾን ከውድቀትህም አስተምረው
ውድቀት/ስሕተት ትልቁ ትምህርት ቤት ነው። የሚሠራ ታታሪ ሰው እንደሚሳካለት ኹሉ ይወድቃልም። የማይወድቅ የማይሳሳት ተጎልቶ የሚያወራ ሰነፍ እንጂ። አንተ ስትሳሳት ስህተትህን ለመሸፋፈን ሳትሞክር ተቀብለው፣ ከስህተትሀም ተምረህ ስታርመው ልጅህ ያያል። መሳሳት ያለ የነበረ ወደፊትም ባላወቅነው ልክ የምንሳሳት እንደኾነና ጀግናው አባቱም እንደሚሳሳት እንደውም እንደተማረበት ይረዳል።

6. አላማህን አቋምህን ግልጽ በማድረግ ከጎኑ(ከአቋምህ) ቁም
ቤቴ ውስጥ ተደማጭነት የለኝም ብለህ ሚስቴም አትሰማኝም ብለህ አቋምህን የምትቀያይር አትኹን። አልያም ከጭቅጭቁ እያልክ ቤትህን ጥለህ አትውጣ።ችግሮችህን ፊት ለፊት ካልተጋፈጥ አብረውህ የሚኖሩ፣ እድገትህንም የሚጎትቱ በራስ መተማመንህንም የሚሰርቁ ይኾናሉ። ይህ ልጅህ ችግሮችን የሚረታበት አቅም እንኳ እያለው ፈተናዎች በመጡ ቁጥር እንዳይሸሽ በራሱም ተማምኖ እንዲወጣቸው ይረዳዋል።

በእንደዚህ መልክ በራስ መተማመንን አግኝተህ ካላደግህ የሚቀጥለው ራስህን በራስህ ማሰልጠን ነው…. ይቆየን

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *