ባልሽ በቤት ውስጥ የሚያስፈልገውን …

በጭራሽ በጭራሽ ባልሽ የሚፈልጋቸውን ነገሮች ሌላ ሰው(ለምሳሌ የቤት ሠራተኛ፣እህትሽ) እንዲያደርግለት አትተዪው። ውሃ ለጣቱ፣ ጠላ ለጉሮሮው፣ ቡና ለአምሮቱ፣ ምግብ ለረሃቡ፣ ጋቢ ለትከሻው ቢፈልግ አንቺን ይጠይቅ። አንቺ ሁሉንም ማድረግ ባትችይ እንኳ ሠራተኛሽ ትዕዛዙን ካንቺ ትውሰድ ትዕዛዙንም ላንቺው ትመልስ አንቺም ለባልሽ። ብታምኚም ባታምኚም ወንድ ልጅ ሶፋ ላይ ተቀምጣ ከምታዝ ቆንጆ የምትታዘዘው ፉንጋ ልቡን በፍቅር ትማርከዋለችና ነው። ባልሽ የሚፈልገውን ሁሉ ማዘጋጀትና ማቅረብ የምትችል ሠራተኛ ብትኖርሽ እንኳ ሁሉንም ለእርሷ አትተይላት። ምክንያቱም ፍቅርሽን የምትገልጪበት አንዱ እና ዋነኛው መንገድ ባልሽን በቤት ውስጥ ፍላጎቱ ማገልገል ነው። ይህ አንቺ ሴትነት ውስጥ አለ። “የወንድ የበላይነት የሰፈነበት ማህበረሰብ እላዬ ላይ የጫነው ነው” ካላልሽ በስተቀር በከተማም ኑሪ በገጠር፣ በምዕራቡ ዓለም ኑሪም በምስራቁ ይህ የተፈጥሮ እውነት ነው።
እህቴ የዓለምን የክስረት መፈክር በምንም አይነት አታስተጋቢ። ውስጥሽ፣ ልብሽ ፍቅር ሲይዘው፣ ባልሽ ከእቅፉ የፍቅር እንጎቻ እየቆረጠ ሲያጎርስሽ፣ በፍቅር ጨዋታ ሲነጥቅሽ፣ ከእርካታ ማማም ሲሰቅልሽ፣ ልብሽ ጥፍት ብላ ደግሞ ስትመለስልሽ ያን ጊዜ አዳምጪያት የሚሰማሽ እርሱ ልክ ነው፤ተፈጥሮሽ እርሱ ነው።
አሁንም በድጋሚ እልሻለሁ ከአእምሮሽ ውስጥ ባልሽ “እኔን አያዘኝም ከፈለገ ሠራተኛዋን ማዘዝ ይችላል” የሚለውን ሃሳብ አውጪው። አስቲ አስቢው ባልሽ ከሥራ ሲገባ እጁን ያስታጠበችው፣ ነጠላ ጫማ የሰጠችው፣ ጋቢ ያቀበለችው፣ ለገላው ሙቅ ውሃ ያስገባችለት፣እራት ሠርታ ያቀረበችለት፣ እጁን ያስታጠበችው፣ ቡና አፍልታ ያጠጣችው፣ልብሱን ያጠበችለት፣የዓመት በዓል ዶሮ የምትሠራለት፣ ከውጭ ሆኖ ለማዘዝ ቀላል የሆነችለት……… ሠራተኛዋ ከሆነች አንቺ በህይወቱ ውስጥ የቱ ጋር ነሽ? ይህን ሰው ሠራተኛችሁ እንዲህ ባለመልኩ ለወራት እና ዓመታት ብታገለግለው ምን ሊፈጠር እንደሚችል መቼም ይገባሻል። መፍትሄው በቅናት መንፈስ መንጫጫት ወይም አንቺም ላትታዘዢው ሠራተኛሽን ማባረር አይደለም ለሠራተኛሽ አሳልፈሽ የሰጠሻትን ያንቺን ግዴታ መልሰሽ መውሰድ፣ባልሽን በደስታ መታዘዝ እንጂ።

አንድ ጥያቄ እስቲ ልጠይቅሽ፦ ይሄ ብዙ ጊዜ የማወራለትን የእርካታ ማማ፣ የልብ መሠወር፣ የደስታ ጫፍ፣ በእርሱም ጋር ያለ ሲቃ እና ለቅሶ ደርሰሽባቸው ታውቂ ከሆነ ነፍስሽ መለስ ሰትል፣ እራስሽንም ስታውቂ፣ ነግቶም ከአልጋሽ ስትወርጂ፣መቆምም ስትችዪ ለባልሽ ምን ልታደርጊለት ትቸኩያለሽ?(ያንን የደስታ ጣሪያ ካላወቅሽ ጥያቄዬ ተረትተረት ይሆናልና ለመመለስ አታስቢ)
ከልብሽ ውስጥ ያገኘሽው መልስ(በከዓለም የአውቀናል ድንቁርና በተቃራኒ) እርሱ ተፈጥሮሽ ነው!!! እልሻለሁ።…….ይቆየን

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *