ባጣቆየኝ፣ ባጣቆይ፣ ባጤ

ባጣቆይነት፦ባጣቆያዊ ኹኔታ

ባጣቆየኝ፣ ባጣቆይ፣ ባጤ፦
(1) ሂያጅ(አመንዝራ)ፍቅረኛ (ሚስት) ያለችው።

(2) የትም ስትሄድ(ስታመነዝር) የሚያውቅ፣ “ካላንቺ መኖር አልችልም፣ ደስታሽ ደስታዬ ነው….” እያለ የሚቀበላት፣ አልፎ ተርፎም የሚደሰት አልጫ ወንድ።

(3) ለራሱ፣ ለትውልድ፣ ለሀገር የማይኖር ሴት አምላኪ የኾነ፣ ፈጣሪ እርሱን የፈጠረበትን ዓላማ የዘነጋና
ሕልሙና ርዕዩ ሴት የኾነችበት፣ የነገሰችበትም ከሌላ መዳራቷ “ደስታዋ” ደስታው የኾነ ወንድ።

ባጣቆይ ወይም ባጤ በዘመናችን እየተለመደ ነው። ትውልድ ለወግ፣ ለባሕል፣ ለኃይማኖት፣ ለማሕበራዊ እሴት እና ስርዓት ያለው አመለካከት፣ ቁርኝት እና ቁርጠኝነት በላላ ቁጥር፤ እንዲሁም አቋም የለሽ፣ ፈሪ እና ሴት አምላኪ የኾነ ትውልድ በመጣ ቁጥር ባጣቆይነት አይቀሬ ነው።

ባጣቆይ እና ሴታውል ሁለት ጽንፍ የያዙ ሴት አምላኪዎች ሲኾኑ የአምልኮት አፈጻጸማቸውም ይለያያል።

የቀደመው(ባጤው) የትም የማይሄድ ነገር ግን አንዲት የወደዳት ሴት የትም እንድትሄድ የሚፈቅድ አልያም “ከእኔ በላይ አምናታለሁ” ብሎ ዝም የሚል፣ ወስልታ ስትመጣም የሚቀበላት ነው።

ስለውስልትናዋም ሲያውቅ ነገር ግን “ይወዳታልና” (ያመልካታልና)፣ ይፈራታልና፣ “ትዳሩ” እንዳይፈርስ ልጆቹ እንዳይበተኑ “ይጨነቃል”ና አይቶ እንዳላየ ሰምቶ እንዳልሰማ ያልፋታል።

ይህን የሚያደርግበት ምክንያትም “ካለእርሷ መኖር አልችልም፣ አሷኮ ነፍሴ ናት፣ የእርሷ ደስታ ደስታዬ ነው፣ ከእርሷ ውጪ ሕይወቴ ባዶ ነው…..” በሚለው አመለካከቱ ነው።

ሴታውሉ ግን ከብዙ ሴቶች ጋር በመተኛት ይለያል። አፍቃሬ ሴትነቱን ከብዙ ሴቶች ጋር በመዋሰብ ይገልጻል። ከአንዷ ጋር የመጽናት ፍላጎት የለውምና መሄዷም አያሳስበውም፤ ቆሞም አይጠብቃት።

ሳተናው!
ባጣቆይነት(ባጤነት) ዛሬ ዛሬ በ”ፍቅር” እና በ”ስልጣኔ” እየተሳበበ በዘፈኖቻችን፣ በግጥሞቻችን ሲሞካሽ በተግባርም በማሕበራዊ ሕይወታችን እየተለመደ እያየን ነው።

ድሮ ድሮ በትዳር ላይ ማመንዘርን ይጠየፍ የነበረው ማሕበረሰብ ዛሬ ዛሬ ግን ቀለል አድርጎ ማየት ይስተዋልበታል። አልፎ ተርፎ እንኳ በትዳር ውስጥ የሚፈጠሩ ግጭቶች ሲዳኙ ባልና ሚስትም ሲሸመገሉ አመንዝራነት ወይም የምንዝር ጌጡም ኾነ ጋባዥ ድርጊቱ ይወገዙ ነበር።

አሁን አሁን ግን “ተው እንጂ ጃል አሁን እኮ ዘመኑ ተቀይሯል ዛሬ ዛሬ እኮ ለትዳርህ፣ ለልጆችህ ስትል አንገትህን ሰበር አድርገህ ተቻችለህ ነው እንጂ….” ይባላል (ራሴ ተገኝቼ ከታዘብኳቸው አሳፋሪ ሽምግልናዎች)።

እነዚህ ዘመን የወለዳቸው “ሴት አምላኪ” አስተሳሰቦች ታዲያ በርካታ ባጣቆይ ወንዶችን እያፈሩ፣ መጪውን ትውልድም ኾነ ሀገር እየበደሉ ነው። ብዙ ወንዶች ፈሪ ከመኾናቸው የተነሳ ስንፍናና ፍርሃታቸውን በ”ስልጣኔ” እና “በፍቅር” አልያም “በመንፈሳዊነት” እያሳበቡ ባጣቆይ ይኾናሉ።

ብዙዎቹም መናገር ከሚችሉት በላይ ይፈራሉ፦
የወደዷትን “ማጣት” ይፈራሉ፣ ትዳራቸው “እንዳይፈርስ” ይፈራሉ፣ ልጆቻቸው “እንዳይበተኑ” ይፈራሉ፣ የደከሙበት ሁሉ “መና” እንዳይቀር ይፈራሉ….. ። ይኹንና ያዩትን “እንዳላየ” አልፈው ባጣቆይ ኾነው መኖርን ይመርጣሉ።

ነገር ግን የዚህ ሁሉ በ”ሳይንስ” አስደግፈው የሚያቀርቡት ፍርሃታቸው ምንጭ ምንድነው ብላችሁ ስትጠይቁ ይበልጡን ቤተሰብኣዊ አስተዳደጋቸው ከዚያ ሲያልፍ ግን የሚኖሩበት ከባቢ(መገናኛ ብዙኃን) ተጽዕኖ ኾኖ ታገኙታላችሁ።

ፍርሃትና አልጫነት……ይቆየን

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *