ታመሰግንህ ዘንድ …. (ላገቡት)

በልክ

ወንድሜ ከሚስትህ ጋር የምትፈጽመው ወሲብ ልክ ሊኖረው ልኩንም ልታውቀው ይገባሃል። ምናልባት በሴታቆርቋዡ(Feminism) የተመረዘ አመለካከት ካለህ እኔ የምልህ አይዋጥልህም።

ዛሬ ዛሬ የመገናኛ በዙኃኑ የሚያወሩትን ሰምተህ መጀመሪያ ያስወደደህንም ወንድነትህን ዘንግተህ የሚስትህን የወሲብ ፍላጎት መጠን የእርካታውንም ጥግ ችላ አትበል። ብዙ ነገር ኾነህ ብዙ ነገርም ሰጥተህ ይኼን ልክ የማታውቅ ከኾነ፤ ወደእርሱም እስካልወሰድካት (እስካላደረስካት) ድረስ ድካምህ ቢላሽ ስጦታህም ምስጋና የለሽ ነው የሚኾነው።

ወንድነትህ ከውጭ ገዝተህ፣ ለምነህ ሰርቀህ የምታመጣው ሳይኾን በተፈጥሮ የተቸርከው ነው። አምጣ አምጣ የሚልህን ስሜት የምታሳርፈው ልከኛና ጥም ቆራጭ ሥራን ስትሠራለት ብቻ ነው። ይኼን ለማድረግ ደግሞ የእርሷን (የአንደበቷን ሳይኾን) የሰውነቷን ግብረ መልስ መከተል በቂ ነው። ልኩንም ከእርሱ ታገኛለህና።

ከዘመኑ የጠረጴዛ ላይድርድር በተቃራኒ ልኩን ከሰሜታዊነት ወጥተህ በአመክንዮ ተመርኩዘህ ልትወስን ግድ ነው። እመነኝ ዝቅተኛውም ወለል ኾነ ከፍተኛው ጣራ ባንተ መወሰን አለበት።

በአግባብ

ወንድሜ አንተ ልኩን አውቀህ በአግባቡ በምትፈጽምላት ወሲብ ደስተኛ ትኾናለች። ሴትነቷ ከለመደው፣ በባሕል ከተቀበለችው፣ በኃይማኖት ከተረዳችው ውጪ ወጥተህ ላንተ ያላትን እምነት እንዳታጣ በወሲብም ላይ ያላት አመለካከት እንዳይጠለሽ አግባቡን እወቅ።

እነዚህን ተረድተህ ግን አግባብ ባለው መንገድ ልኳን የምታሳይበት(የምትሰጥበት) ኺደት በፍላጎትና በስምምነት የሚኾን ሳይኾን በውዴታ ግዴታ ውል በኃላፊነት የምታደርገው ነው።

ኃላፊነት

ለአባወራ አባትነት፣ ባልነትና ራስነት ወንድነቱ ቅድምና አለው። ይኽም ማለት አባትም ባልም ኾነ የቤቱ ራስ ለመኾን ወንድ መኾን ግድ ይላል።

ለተራክቦአችሁ ልኩንና አግባቡን የተሰጠህ ኃላፊነት ይወስናቸዋል። በእያንዳንዱም ድርጊትህ ኃላፊነት ሲሰማህና ስትወስድ ልክና አግባብ ድንበር አይኖራቸውም። ልኩ ዘወትር የሚያድግ ሲኾን አግባቡም ኢምንት እየኾነ ይኼዳል።

ጀግናው ወንድሜ! እንደትዳራችሁ ኹሉ ወሲባዊ ተራክቦአችሁ ያንተና ያንተ ኃላፊነት ነው። ሰለጠንኩ ብለህ ይኽን ኃላፊነትህን ከራስህ ላይ አውርደህ ጠረጴዛ ላይ ለውይይት(ለድርድር) አታስቀምጥ። እንዲህ ያደረግህ ዕለት ግን ላንተም ኾነ ለስጦታዎችህ ያላት ቦታ እየቀነሰ የሚኼድበት፣ አነስተኛና መለስተኛ ጭቅጭቆችም የሚጀመሩበት ዕለት ይኾናል።

ይኼን ኃላፊነት መቼ፣ የት፣ እንዴት እንደምትወጣው መርሐ ግብር ማውጣት ምስኪንነት ነው። እርሷ ካወጣችልህማ አባወራነትህን ተነጠቅህ ክብርህንም አጣህ ማለት ነው።

አንተን ከፍ የሚያስደርግህ ቅጽበታዊ፣ እንደ ድንገቴ ደራሽ በኾነ፣ ልኳን ጠብቀህ አግባቡን ሳትለቅ ሙሉ ለሙሉ የክዋኔው ባለቤት ኾነህ በኃላፊነት ስትፈጽመው ነው።

ይኽ ሲኾን ሌሎቹ ስጦታዎችህ (ገንዘብ፣ ጌጣጌጥ፣ አልባሳት፣ ጊዜ..) እርሷ ጋር በዐለም ገበያ ካላቸው ዋጋ በላይ ዋጋ ትሰጣቸዋለች። ሌሎቹን ስጦታዎችህን የሚያቀለውም ኾነ የሚያዋድደው ይኸው አንተን መጀመሪያ ያስፈቀደ(ያስከጀለ) ወሲባዊ ስሜት ነው።

ይኼን ሳታደርግ “ሚስቴ ምንም ባደርግላት አታመሰግነኝም” ትለኝ ከኾነ ግን “ባትንቅህ ነው የሚገርመኝ” እልሃለሁ።

ይቆየን

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *