ታመሰግንህ ዘንድ ቀዳሚው ሥራህ የቱ ነው

በእግር በፈረስ ፈልገህና አስፈልገህ ስለተሰጣት ነገር ማመስገንን የተማረች ልጅ ብታገኝ ወላጆቿ ባሳዩዋት መንገድም ሄዳ ስለሥራህ ታመሰግንህ ዘንድ የትኛውን ሚናህን ብታስቀድም ይበጅሃል?

ጀግናው ወንድሜ!

ሚስትህ ሳታገባህ ቀድሞ አንተ ላይ ዐይኗ እንዲያርፍ ያደረገ ወንድነትህ ሲኾን ይኼም ወንድነትህ የተለየ ስሜት በውስጧ ፈንጥቆባት ነበር።

ያኔ አንተ ሴት ኾነህ ቢኾን ኖሮ ይኽቺ የዛሬዋ ሚስትህ የተለየ ስሜት ባልተሰማት በተለየ አስተያየትም ባላየችህ ነበር።

ይኽ ስሜትም አንተን ባሏ እንድትኾን፣ የልጆቿ አባት እንድትኾን፣ በቤቷም ላይ ራስ እንድትኾን አስባ ስትጨርስ የተፈጠረ ሳይኾን እንዲሁ ወንድ በመኾንህ ብቻ በመላ ሰውነቷ የተሰራጨ መልስ የሚያሻው ተፈጥሮአዊ ጥያቄን ያነገበ እንጂ።

ይኽ ስሜትም ወሲብን ማዕከል ያደረገ ተፈጥሮኣዊ ና ቅጽበታዊ ጥያቄ ነው።

ወንድነትህ ለአባወራነትህ ምንጩ፣ መንስዔው፣ ምክንያቱ መገኛውም ነው። ወንድነትህ ሌሎቹን የአባወራነት ሚናዎች ይገልጻቸዋል ወይም እነርሱ በወንድነትህ መጠን ይገለጻሉ፣ ይተረጎማሉ።

ወንድነትህ ሲቀዘቅዝ(ሲያሽቆለቁል) አባትነትህ፣ ባልነትህና ራስነትህም አብረው ይቀዘቅዛሉ። ወንድነትህ ሲያይል ደግሞ አባትነትህ፣ ባልነትህ፣ ራስነትህም አብሮ ያይላል ይጎመራል።

ስለዚህም ይኼን ወንድነትህን መኮትኮት፣ ማሳደግና ማጠናከር በተዘዋዋሪ አባወራነትህን ማበልጸግ መኾኑን አስተውል።

ወደቀደመው ነገራችን ስንመለስ አንተን ለሚስትህ ዐይን ማረፊያነት ያስመረጠህ ወንድነትህ ነው። ይኽ በጾታዎች የዋልታ ልዩነት የሚመጣው መሳሳብ ደግሞ ጠንሳሹም ኾነ መሥራቹ ወሲብ ነው። የስበቱን ማዕከል ምክንያትም ወሲብ ኾኖ እናገኘዋለን።

ስለዚህም ተፈጥሮኣዊና ቅጽበታዊ ለኾነው ስበት ወንድነትህ ቅድምና እንዳለው ኹሉ፤ አንተም ከተሰጡህ ተፈጥሮኣዊ ሚናዎችህ አስድመህ፣ ለይተህና አጽንዖት ሰጥተህ ልትፈጽምላትና ልትሰጣትም ይገባሃል።

ጀግናው ወንድሜ!

“ሚስቴ ይኼን ስሰጣት፣ ይኼን ስገዛላት ታመሰግነኛለች ትወደኛለችም” አትበል። ወንድነትህ ስቦት ለመጣ ሴትነቷ ግብዣህ ያው ተፈጥሮኣዊ ወንድነትህ እንጂ ብርና ወርቅ አይኹን የጥያቄዋን ክፍተት አይሞሉምና። እርሱንም አጉድለህ በሌላ ልትክሳት አትሞክር። እርሱን ዘንግተህም ሌላውን ለመሙላት አትቸኩል።

አንተና ሚስትህ ከሁለት ወደ አንድ የምትመጡበት ተፈጥሮኣዊና ተዓምራዊ ሕብረት ወሲብ ነው።(፩ኛ ቆር ም፮፥፲፮)

፩ኛ ተፈጥሮኣዊ አልኩኝ፦ የሰው ልጅ ተምሮና ተመራምሮ ያመጣው ሳይኾን በፈጣሪ የተሰጠን ስለኾነ።

፪ኛ ተዓምራዊ አልኩኝ፦ የሚታይ የአካል ሁለትነት ባለበት የማይታይ ነገር ግን በስሜት የምንሰማው፣ በዐይነ ህሊና የምናየው፣ በድርጊት(በሩካቤ) ብቻ የምናገኘው አንድነት ስለኾነ ነው።

ስለዚህ ወንድሜ አንተ በወንድነትህ ከሚስትህ ጋር የምትፈጽመው ወሲብ የመጀመሪያውና ዋነኛው፣ ወደህና ፈቅደህም የገባህበት፣ የውዴታ ግዴታህም ነው።

ይኹን እንጂ ምንም እንኳ እንደሚያስወድድህ እንደሚያስመሰግንህም ብታውቅ ሕብረታችሁንም እንደሚያጠነክር ብታረጋግጥ ኹሉ በሥርዓት እንዲኾን ታዟልና እንዲሁ ፈጽም።

በልክ፣ በአግባብና በኃላፊነት ሲኾን ድርጊትህ ተልኮውን ይፈጽማል።

በልክ
ከሚስትህ ጋር የምትፈጽመው ወሲብ ልክ ሊኖረው እርሱንም ልታውቀው ይገባሃል፤ አንተ! በሴታቆርቋዡ (Feminism) አእምሮህ ከተበከለ ይኼንን ማስተዋል ይቸግርህ ይኾናል።

እንዴት … ይቆየን

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *