ታዳጊው ምስኪን ፪

ሳተናው!
ጽሑፎቹ መረርና ጠንከር ብለው ሲመጡ ታግሰህ አንብባቸው፤ ራስህንም ፈትሽባቸው። 

ልብ አድርግ! አንብብልኝ አላልኩህም ለራስህ ስትል አንብብ እንጂ።
ታዳጊ ስል የቃሉ ትርጉም፡ ከችግር፣ ከውድቀት፣ ከተጋረጠ አደጋ የሚታደግ የሚያድን።

ማስታወሻ፡ ታዳጊ-ምስኪኖች በዋናነት ዋጋ ያስገኝልናል(ያስወድደናል) ብለው የሚፈጽሙትን ትድግናቸውን ይመኩበታል፣ ይጠብቁታል፣ ያሳድጉታል በእርሱ የመጣባቸውንም ያጠቁታል።

ታዳጊ-ምስኪን ትድግናውን ፦

፩ኛ ይመካበታል፦ 
ይኽን ምግባሩን ሌሎች ከ”ኩራታቸው” እና ከ”ትዕቢታቸው” የተነሳ ይርቁታል ሲል አይገቡ ገብቶ አይኾኑ ኾኖ ይፈጽመዋልና እንደጀብድ ቆጥሮት ይመካበታል። ይኹን እንጂ በሕቡዕ በልቡ ያስቀመጣትን እና በ”ትድግናዬ ማግስት አገኛታለሁ” የሚላትን መወደድና መከበር ከሰዎች ልብ ከልብ አያገኛትም። ይኽ ደግሞ በጾታዊ ግንኙነቱ ጎልቶ ይታያል።

፪ኛ ይጠብቀዋል፦ ይመካበታልና “ያለኝ ምርጡ ኃብቴ ነው” ሲልም ይጠብቀዋል። የትኛውም መካሪ ታዳጊ-ምስኪንን አሳምኖ ትድግናውን እንዲተው ለማድረግ ከባድ ነው። “ለምን?” ቢሉ ቆራጥነት፣ እውነትን መመስከር፣ ስለእውነት መከራከር፣ እርሱንም መጋፈጥ በሚመለከተውና በተጠራበት ጉዳይ ብቻ መሳተፍና በመሳሰሉት የመገኘት አቅም የለውምና።

፫ኛ ያሳድገዋል፦ በጣም የሚያሳዝነውና የሚያስቆጨው ደግሞ ታዳጊ-ምስኪን በቀደመ ትድግናው የጠበቀውን መወደድ፣ መከበር፣ ምስጋና ካላገኘ ከበፊቱ እጥፍ ድርብ አድርጎ ትድግናውን መፈጸሙ ነው።

በተለይም ደግሞ ባለትዳር ከኾነ ይኽ ጎልቶና ሰፍቶ መታየቱ እርግጥ ነው። ይኹን እንጂ የሚጠብቀውን ስለማያገኝ ብስጭቱና ንዴቱ እጥፍ ድርብ ይኾንበታል።

፬ኛ ትድግናውን የሚቃወሙትን ይጠላል ያሳድዳልም፦ ታዳጊ-ምስኪኖች በየትኛውም የሥራ መስክ(በፖለቲካውም ቢኾን)፣ በየትኛውም የማሕበራዊ ሕይወት ልምምድም ቢገኙ እንደእነርሱ ዓይነት መልካም ሰው ያለ፣ ተነስቶ የሚያውቅና ወደፊትም የሚነሳ አይመስላቸውም፤ አይነሳም ብለውም ያስወራሉ። ከእነርሱ የሚጠቀሙት ተከታዮቻቸውም ከጥቅማቸው እንዳይጎልባቸው ሲሉ ብቻ “አቦ”፣ “አቦ” እያሉ እየካቡ ይከተሏቸዋል።

ታዳጊ-ምስኪኖች ተቃዋሚዎቻቸውን ማሳደዳቸው ስለሁለት ነገር ነው፦
፬፥፩ ራሳቸውን ኾነው(የግድ ከሰው ስለሚያገኙት ሳይጨነቁ) ዓላማን ሰቅለው፣ ርዕይንም ሰንቀው፣ ስለሌላውም ጭብጫቦና ሽብሻቦ ግድ ሳይሰጡ በሚኖሩት፤ ይኹንና አክብሮት፣ ፍቅርና ውዳሴው ባልተጓደለባቸው ሰዎች ይቀናሉ ይበሳጫሉምና። የእነርሱንም ፈለግ መከተል አንድም አልቻሉም አልያም አይፈልጉምና ነው።

፬፥፪ ይልቁንም በጾታዊ ግንኙነት በጠቅላላው በሴቶች በተለይም በሚስቶቻቸው ዘንድ በአፍኣ 
በአደባባይ በየመገናኛ ብዙኃኑና በየመድረኩ ሲለፍፉ ደርሰው “የሴቶች ተቆርቋሪ” መስለው በመታየት ቢቻል ከኹሉም ሴቶች ባይቻል ግን ከሚስቶቻቸው ማትረፍ ይፈልጋሉና ነው።

የሚኾነውና እየኾነ ያለው እውነታ ግን ከዚኽ የራቀ ነው። እርሱም ሴቶች ዘወትር እነረሱ ዓላማው፣ ሕይወቱ፣ ጥረቱ፣ ኑሮው የኾኑለት ታዳጊ-ምስኪን ወንድ ይልቅ የሚኖርበት ዓላማ የገባውና በተጠራበት ጉዳይ፣ በተጠራበት ልክና መጠን የሚገኝ ለጊዜውም ዋጋ የሚሰጥ፣ ላመነበት ጉዳይና ፍላጎቱ የእነርሱን ይኹንታ የማይፈልግ ቆራጥና ጀግና አባወራ መማረካቸው ነው(ከዚኽ በፊት የለጠፍኩትን የምስኪንና የዱርዬ ንጽጽር ከልስ)። 

ምስኪን ተሸናፊ ሲኾን ለሽንፈቱ ግን የራሱን ስንፍና እና ፍርሃት ከመውቀሰ ይልቅ አፍቃሬ ሰብዕ(ሰው ወዳጅ) እንደኾነ ራሱ ስለራሱ ምስክርነት ይሰጣል፤ ይከራከራልም…. ….ይቆየን

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *