ታዳጊው ምስኪን

የቃል ትርጉም፡ ታዳጊ ስል የሚታደግ ከችግር፣ ከውድቀት፣ ከተጋረጠብን አደጋ እና ከመሳሰሉት።

ሳተናው!
ምስኪን  “መልካም ብሠራ ሰዎች ይወዱኛል” በሚለው አስተሳሰቡ በምስኪንነቱም ለመቀጠል የሰዎችን የድክመት፣ የስንፍና እና የግዴለሽነት ሥራ መታደግ ያዘወትራል።

ይኼን ውለታ ሊውልላቸው የሚችላቸውን ሰዎች፣ ትድግናን የሚፈልጉ ሰዎችን በመቅረብና በመታደግም ከእነርሱ አክብሮትን፣ መወደድንና፣ ምስጋናን አገኛለሁ ብሎ ያስባል፤ ይጠብቃልም። ከዚኽ የተነሳም ምስኪን በዙሪያው በጥረት፣ በጥንካሬ፣ በጽናት ድልን ያገኙ ሰዎችን ሳይኾን ደካሞችን፣ ሰነፎችን፣ ሰበበኞችን፣ የኾነ “ጥቃት ሰለባ ነን” ባዮችን ይሰበስባል፤ ይስባቸዋልም።

ይኽ የምስኪኑ ጠባይ የሳባቸው ሰዎችም ታዲያ ለገጠማቸው የራሳቸው ችግር ኃላፊነት መውስድ፣ መጋፈጥና አስፈላጊ ከኾነም እርዳታ መጠየቅን አይሹም፤ አልያም ደግሞ ራሳቸውን ከችግር ለማራቅ አይጥሩም።

እንዳውም ከምስኪኑ ጋር ያጣብቀናል ፍቅሩንም ይጨምርልናል የሚሉትን የእነረሱን ችግር( ስንፍናና ኃላፊነት ያለመውሰድ አባዜ) እየፈተፈቱ ትኩስ ትኩሱን ያቀርቡለታል። ለእነርሱ “መልካም ሰው” ማለት ለትንሽ ትልቁ ጉድለታቸው ወይም ስንፍናቸው “ኃላፊነት ውሰዱ፣ ግዴታችሁንም ተወጡ፣ ተጠያቂነትም አለባችሁ” የሚለው አባወራ ሳይኾን ያለምንም ማንገራገር በደካማ ጎናቸው የሚቆምላቸው ምስኪን ነውና።

እነዚህ ሰዎች ለራሳቸው ሥራ ኃላፊነት መውሰድ አይፈልጉም ሰበበኛ ናቸውና፣ ግዴታቸውን መወጣት አይችሉም ስንፍና አስሯቸዋልና፣ በቃላቸው አይገኙም ጽናት ይጎላቸዋልና። ስለዚህም በጥገኝነት የሚያኖሯቸውን ምስኪኖች ይፈልጋሉ። 

በዚኽ ኹኔታ ከሌላው አካል በሚጠበቅም ውለታ ነው እንግዲህ ይኼ የጥገኝነት ጥምረት የሚፈጠረው። ይኽ የፍቅር ጥምረት መጠባበቅ ያለበት በብስጭትና በምሬት የተሞላ፣ ፍሬው የማያምር መጨረሻውም የመፍረስ ዕጣ ፋንታን የሚስተናግድ፣ ባይፈርስም እንኳ ለአርኣያነት የማይጠቀስ ይኾናል።

አንዱ አካል ለችግሩ ኃላፊነት ወስዶ ለመፍታት ከመጣር ይልቅ ምስኪኑን ይጠብቃል፤ ሳይጠራው እንኳ ቢደርስለት ይወዳል፤ ቢቀርበት ደግሞ ያማርራል። ምስኪኑ ደግሞ ተጠርቶ መታደጉ እንኳ ይኹን ብንል አብዛኛውን ጊዜ ግን ያንኛውን ወገን በራሱ ለችግሮቹ መፍትሔ እንዲሰጥ አይተወውም። 

ይልቁንስ ሳይጠራ ይመጣል፣ ሳይጠየቅ ይሠራል “ለምን?” ቢሉ ይኼ “የሚያስከብር፣ የሚያስወድድ፣ የሚያስመሰግን” ሥራ ነው ብሎ ያስባልና እናም “እከበራለሁ፣ እወደዳለሁ፣ እመሰገናለሁም” ብሎ ይጠብቃልና።

ወቅታዊ ትዝብት
======================

አኹን ያለንበትን ዘመን ግምት ውስጥ ከትቼ ወንዶችን(ራሴንም ጨምሮ) ስታዘብ አብዛኛው ወንድ ከሴቶች አክብሮትን፣ ፍቅርን፣ ምስጋናንም አገኝበታለሁ ሲል ታዳጊ(ከላይ የሰጠሁትን ትርጉም አታውስ) ነው።

እነዚህ ታዳጊ ወንዶች በምስኪን ጥላ ሥር ያሉ ናቸው። ታዳጊነታቸው ከምስኪንነታቸው ይመነጫል (የታዳጊነታቸው ምንጩ ነቁ  ምስኪንነታቸው ነው)። ሚስታቸው በምትከታተለው ትምሕርት፣ በተሠማራችበት የሥራ መስክ፣ በምትሳተፍበት ማሕበራዊ ሕይወት፣ በተቀበለችው ኃላፊነትና በሚጠበቅባትም ግዴታ ውስጥ አቅሟን አጎልብቶ ብቃቷን እንድታሻሽል አያደርጉም። 

ይልቁንስ ችግሮች በገጠሟት ቁጥር እየተገኙ ያንን ጊዜያዊ ችግር መፍትሔ መስጠት አክብሮትን፣ ፍቅርንና ምስጋናን ይጨምርልናል ብለው ያስባሉ። ነገር ግን አብዛኛውን ጊዜ(ለኹል ጊዜ የቀረበ) የጠበቁት ሳይኾን ተቃራኒው ይኾናል።

ይኽ ከሴቶቹ ጋር ያላቸው ግንኙነት በተለይ በፍቅር ላይ የተመሠረተ በትዳር የታጠረ ከኾነ ይኼን ሥራቸውን አብዝተውና አጉልተው ይፈጽሙታል። ይኹን እንጂ…. ይቆየን

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *