“ትኅትና” የምርጫህ መለያ

ሳተናው!

የሃያዎቹ እድሜዎች የወንድ ልጅ ከእውቀት፣ ከእድሜ እና ከልምድ ከዚህም የተነሳ ከሚገኘው ጥበብ አነስተኛ ክምችት እያለው ነገር ግን ከዚህ በተቃራኒ ብዙ እንዳወቀ፣ እንዳስተዋለ እና እንደኖረም ሰው “ነኝ” የሚልበትና የሰውን ምክርም ከመስማት አሻፈረኝ የሚልበት እድሜ ነው።

ይህን እድሜ አልፌበታለሁና ስለማውቀው እንዲህ አልኩህ። በዚህ እድሜ ላይ ኾነህ ከምትጠቀምባቸው ወይም ከምትጎዳባቸው የሕይወት ዘመንህ ምርጫ እና ውሳኔዎችህ መካከል ታዲያ አንዱ እና ዋነኛው የወደፊት ሚስትህ እንድትኾን በምትመርጣት ሴት ላይ ያለህ የተዛባ አመለካከት ነው።

ይኽ እድሜ ከላይ በጠቀስኩልህ ምክንያቶች የተነሳ ከምክንያታዊነት፣ ከጥበበኛነት ይልቅ ስሜታዊነት የሚያደላበት ነው። ስለዚህም አብዛኛዎቹ ከተፈጥሮኣዊ ሐቅ እና መሬት ላይ ካለው ተጨባጭ እውነታ የራቁ ነገር ግን ስሜት ላይ ያተኮሩ፣ በስሜት ዙሪያ የሚያጠነጥኑ፣ “ሰዎች ምን ይላሉ” ተበለው የሚጠነሰሱ ኃሳቦች የሚዘወተሩበት እድሜ ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በዚህ እድሜ ውስጥ ኾነህ ሴትን ልጅ በሚታየው መረጃ የተደገፈ የኖረችበትንና እየኖረችበት ያለውንም ጠባይ ካለማየት የተነሳ ትዳር፣ ቤተሰብና ጤናማ ትውልድንም የምናፈራባትን ሚስት ለማጨት እንቸገራለን።

ከዚህ ይልቅ “ደስ ትለኛለች፣ ካለእርሷ መኖር የምችል አይመስለኝም፣ የእናቴ ምትክ ናት፣ እኔ ከወደድኳት(እኛ ከተዋደድን) የኋላ ታሪኳ የቤተሰብ አስተዳደጓ ወሳኝ ሊኾኑ አይገቡም….” በማለት በስሜት በተነዳ ምርጫ ብሎም ውሳኔ ውስጥ እንገባለን።

ሳተናው!
አንተ ግን በሴት ምርጫህ ላይ በስሜት ከመነዳት ተቆጥበህ ምክንያታዊ እና አስተማማኝ መመዘኛዎችን ተጠቅመህ ወደ ትዳር መግባት ይጠበቅብሃል። ይህን በማድረግህ ደግሞ ራስህን፣ ሚስትህን፣ ልጆችህንና ሀገርህንም ትጠቅማለህ።

ከእነዚህም መመዘኛዎችህ ውስጥ ታዲያ ታላቁ እና ሌሎች መመዘኛዎች እንኳ የሚመዘኑበት “ትኅትና” ነው። ትኅትና ለሴት ልጅ ተፈጥሮኣዊ ጸጋ ብቻ ሳይኾን ሌሎቹን ተፈጥሮኣዊ ስጦታዎቿን እውን የምታደርግበት ልምምዷም እንጂ ነው።

አንተ ምርጫህ ውስጥ የምታስገባት ሴት ይህን ፈጣሪ የሰጣትን ጸጋ የተቀበለች፣ በአባቷ አሰልጣኝነት፣ በእናቷም አርኣያነት የተለማመደችው ልትኾን ይገባል። ይህንንም ምርጫህን “ቸርነት፣ ደግነት፣ ስጦታ፣ ውለታ፣… በሚባሉ አለቦታቸው በሚገቡ ትሩፋቶች ልታዛባው አይገባም።

ማለትም አንተ ልትረዳት፣ ልታግዛት፣ ልትለግሳት፣ ልትራራላት…… የምትፈልጋት ሴት ካለች በሰውነቷ በእህትነቷ እርዳት እንጂ ስለቸገራት፣ ስላሳዘነችህና ስለረዳሃት ብቻ ሚስትህ እንድትኾን ከማሰብም ኾነ ከማድረግ ልትቆጠብ ይገባል።

ከዚህ ይልቅ ግን ከብዙ ከምትወዳቸውና ከምትቀርባቸው ሴቶች መካከል ይህቺ ያሰብካት ሴት “በአባቷ ተመክራ፣ ተገስጻ ና አስፈላጊም ኾኖ ተቀጥታ አድጋለች ወይ? እንዲሁም ደግሞ እናቷስ የትኅትና አርኣያ ኾናታለች ወይ?” ብለህ መጠይቅ ለጥያቄህም ተገቢውን መልስ ማግኘት አለብህ።

“እናቷን አይተህ ልጅቷን አግባ” እንዲሉ

ሳተናው!
? አንዲት ሴት ትኅትና ከሌላት ምኗን ዐይተህ ታገባታለህ? ላንተ ጥያቄ የምንዴት(ምን?…እንዴት?..አይገርምህም..?) መልስ የምትመልስ ከኾነ ምኗን ወደህ የቀሪ ሕይወትህ አካል ታደርጋታለህ?

? አንዲት ሴት “ከእኩልነት” በተነሳ ስሌት ብታንባርቅብህና “ልቆጣህ” የምትልህ ከኾነ ቀሪ ዘመንህን ከእርሷ ጋር እንድትኖር የሚያደርግህና ሚዛን የደፋልህ ጠባይዋ የቱ ነው?….. ይቆየን

“እናቷን አይተህ ልጅቷን አግባ”….

ቴሌግራም
https://t.me/abawera

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *