ንጉስ ለመንግስቱ አባወራ ለቤቱ

የአንድ ሀገር ንጉሥ ሀገሩን የሚያስተዳድርበት ሕዝቡንም የሚመራበት ሕግ ያወጣል አዋጅም ያውጃል። ይኽ ሕግ ሀገሪቷ ሰላማዊ እንድትኾን ሕዝቡም በሰላም ወጥቶ ይገባ ዘንድ ሌሎች ሰብዓዊ መብቶቹ ይከበሩለት ዘንድ መሠረታዊ ነውና ተፈጻሚነቱ ግድ ይላል።

ይኹን እንጂ ሠርተው መለወጥ መሻሻል የማይፈልጉ ድክመታቸውን ስንፍናቸውን እና ዝርውነታቸውን(መረንነታቸውን) በሌሎች በማሳበብ ያለድካምም መጠቀም የሚፈልጉ ጥቂቶች ግን ይኼን አይፈልጉም።

እንደ እነርሱ ከኾነ ሁሉም ራሱን መምራት የሚችል ብቁ ስለኾነ የሚጠብቀው፣ የሚመራው ብሎም የሚቀጣው ሕግ በዝቶበታል አልያም አያስፈልገውም ብለው ይከራከራሉ። ንጉሱንም ያውካሉ፣ ይሞግታሉ ለመጣልም ይታገላሉ።

ንጉሱን የሚታገሉት እነዚህ በሕግና በስርዓት መተዳደር የማይፈልጉ እርሱ የሚያስተዳድራቸው ወገኖቹ ብቻ ሳይኾኑ ትላንት ሲነግስ ያጨበጨቡ፣ ንጉስ ኾይ ሺህ ዓመት ንገስ ብለው ላንቃቸው እስኪሰነጠቅ የጮኹ፣ የዘንባባ ዝንጣፊም እግሩ ሥር የጣሉ ነገር ግን በንግስናውም ኾነ በሕዝቡ ስርዓት ቅንዓት የተቃጠሉ የጎረቤት ሀገራትም ጭምር እንጂ።

እነርሱ ደግሞ የንጉሱ መውደቅ፣ የመንግስቱም መፍረስ፣ የሕዝቡም መቅበዝበዝ በሀገሪቷ ውስጥ ያለውን አንጡረ ሀብት ለመቀራመት፣ ሕዝቡንም እንደነእርሱ ስርዓት አልባ መደዴ ለማድረግ ይጠቅማቸዋልና እምቢተኞቹን ይደግፋሉ።

የንጉሱ እምቢተኞች ንጉሱን ከጣሉት ኹሉ ወደ ዘረፋ፣ ኹሉ ወደ ጥፋት እንደሚገባ ለእነርሱም አመቺ መንገድን እንዲጠርግ እርግጠኛ ናቸው።

ይኼም ባይኾን ግን ንጉሱ በሕግና በስርዓት የያዛት ሀገር ስትበጠበጥ፣ ሕዝቧም ተፈጥሮውን ረስቶ መደዴ፣ መረን እንዲኾን በነጻነት ስምም ከእንሰሳት በማይገኝ ግብር እንዲጠመድ በዚህም ግብሩ ከፈጣሪው እንዲጣላ እንዲረሳውም ይፈልጋሉ፤ ፈልገውም አይቀር ንጉሱን ንቀው፣ ድንበሩን ገፍተው ይገባሉ ይሠራሉ።

ንጉስ ደግሞ በመንግስቱ ጎልማሳ በሚስቱ ሲመጡበት አይወድምና ይተዳደሩበት ዘንድ የሰጣቸውን ሕግ ባይጠብቁ የሚቀጣበት ተመጣጣኝ ቅጣት አብሮት አለና ይተገብረዋል። ንጉስ ምን ግዛቱ ቢያምር፣ የሚገዛበትም እንከን የለሽ ደንብና ስርዓት ቢኖረው እረሱን የሚያስፈጽምበት ኃይል ካጣ ግን አንድ ቀን አያድርም።

ታዲያ የከይሲዎች ሴራ ያልገባቸው የንጉሱ እምቢተኞች ለጊዜው ለስርዓቱ ቢታመኑ፣ ተስፋቸው ነገ ለሚኖራቸውና ለሚናፍቁት ሰላም ሕይወት እስትንፋስም በኾነላቸው ነበር።

ይኹን እንጂ ለንጉሱ ሥርዓት የታመኑት (ንጉሱ ያወጣው ሕግ ስለራሳቸው ጥቅም መኾኑን በልባቸው አምነው የተከተሉት) ዓላማውም የገባቸው፣ የነገን ተድላ ደስታ ዛሬ በድንግዝግዝ ያያሉና የድግሱም ጢስ ይሸታቸዋልና(ተሰፋ ያደርጋሉና) እምነታቸው በተስፋ ተስፋቸውም ከንጉሱ ጋር በሚኖራቸው አንድነት ፍቅር ፍጻሜውን ያገኛል።

የሚያሳዝነው ግን የንጉሱ እምቢተኞች ዛሬ በእምነት ሥርዓት ይመላለሱበት ዘንድ የፍቅርን ጣዕም፣ ማንነቷ፣ አሠራሯና አፈጻጸሟ እስኪገባቸው ድረስ የተሰጣቸውን “ሸክም”፣ “ጭቆና”፣ “ባርነት” ብለው ማመጻቸው ነው።
ይኼም አልበቃ ብሏቸው የራሳቸው ወገን፣ የአብራካቸው ክፋይ የኾነን ንጉስ ለመጣል አንድነታቸውን ከማይፈልግ ጠላታቸው ጋር ማበራቸው ነው።

ንጉሱ ቢወድቅ
ንጉሱ ቢወድቅ፣ መንግስቱ ይፈርሳል፣ ሀገሩም ይፈታል፣ ሕዝቡም መረን ይወጣል።ሕዝቡ በቅርብ ያለውን ንጉስ የሚያስተዳድርበትንም ስርዓት ንቀዋልና ይኼም ንቀት የሚያቋትንና የረገጧትን ሀገር ያሳጣቸዋል በሀብቷም ጠላት ሲፈነጭበት እነርሱን ባይተዋር ያደርጋቸዋል።

ይኽ ድርጊታቸው ካልጸጸታቸውም ለማያዩት ንጉስ ማደር፣ ለሕጉም መገዛት የማይመስል ነገር የማያቋትን ሀገር(መንግስት) መውረስም ተረት ተረት ይኾንባቸዋል።
=============================================================

አባወራ ለቤቱ
አንተ ወንድሜ አባወራ ነህ። ይኼ ደግሞ በፈጣሪ የተሰጠህ፣ ፈቃዱንም የምትፈጽምበት ስልጣን፤ ቤተሰብህን በስርዓት፣ በፈሪሃ እግዚአብሄር ወደ ፍቅር አምላክ እየመራህ የምታደርስበት ባትወጣው የሚያስጠይቅህ ኃላፈነት ነው።

ራስህን በቃሉ አንጽ የዓለምንም የእኩልነት እንቶፈንቶ አትስማ፤ አባወራነትህ ከሚስትህ የሚያበላልጥህ ሳይኾን በሚናህ እንደሚስትህ ኹሉ ልዩ ስለኾንክ እንጂ። ቤተሰብ አንተ በመሪነት የምትሰየምበት፣ ራስህንም ቢኾን መስዋዕት አድርገህ ልትታደገው የሚገባ ትንሹ ቤተመንግስት ነው።

አባወራ ለቤቱ መሪ፣ አስተዳዳሪ ነው። ሚስቱንና ልጆቹን የሚያኖርበት፣ የሚያስተዳድርበት ሕግን የሚያወጣም እርሱ ነው። አባወራው በሚያወጣው ሕግ ቤቱ ስርዓት ሲይዝ የቤተሰቡም አባላት ከአባወራው የሚያገኟቸው ተፈጥሮአዊ መብቶች ኹሉ ስርዓቱን በመጠበቅ ተፈጻሚ ይኾንላቸዋል።

ይኹን እንጂ በስርዓት ቀርጾና አንጾ ላስተዳድር በሚል አባወራ ቤት ውስጥ ለሕጉና ለስርዓቱ የማትገዛ፣ ከልጅነቷም አባቷ በስርዓት ያላሳደጋት፣ እናቷ የእምቢተኝነት አርአያ የኾነቻት ሴት(ሚስተ) ትኖራለች።(ከቅድመ ጋብቻ የምርጫ ስሕተት የተነሳ)

እናም…..
ይቆየን

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *