“ንግስቴ ነሽ?”

ሳተናው!
ዛሬ ዛሬ መረን የለቀቀው የኪነጥበብ ውጤት ትውልዱን ከተፈጥሮኣዊው ሐቅ አርቆታል። በተለይም ወንዶችና ሴቶች ተፈጥሮኣዊው ጸጋቸውን (ስጦታቸውን)፣ ሚናቸውንና ዓላማቸውን ስተው እንደ እንሰሶች ስሜታቸውን ብቻ የሚሰሙ በእርሱም የሚነዱ እንዲኾኑ ዳርጓቸዋል።

ይኼንንም እስከዛሬ በነበሩት ጦማሮቼ በጥቂቱም ቢኾን ዘፈኑ፣ ፊልሙ፣ ቲያትሩ ይኼንን የሊበራል ምዕራባውያንን ክፉ ተልዕኮ እንደተወጣ አይተናል። ምዕራባውያን (ሰሜን አሜሪካ፣ ካናዳ፣ እንግሊዝ፣ አውስትራሊያ፣ ጀርመን፣ የስካንዲኔቪያን ሌሎችም) ሀገሮች እዚህ ከላይ የጠቀስኳቸውን የኪነጥበብ ውጤቶች በመጠቀም ትውልዳቸውን መረን አውጥተውበታል፣ ተፈጥሮኣቸውን አስተውበታል፣ ዓላማ ቢስ አድርገውታል በፈቃዱ(ለኾዱ፣ ለገንዘብ፣ ለዝና፣ ለወሲብ) የሚገዛ ባርያም  ኾኖላቸዋል።

በእኛም በሀገራችን ከዚህ በፊት ባልተለመደ ሁኔታ ዛሬ ዛሬ በሚወጡት የኪነጥበብ ውጤቶች ይኽ የምዕራባውያን ተጽዕኖ ይንፀባረቃል። ይኸውም ወንዶች በቤታቸው በትዳራቸው ውስጥ ሊይዙት የሚገባቸውን ተፈጥሮኣዊ ቦታ እያሳተቸው እያሳሳታቸውም እየመጣ ነው።

ሳተናው!

አንተ በቤትህ ንጉስ ነህ፤ በሚስትህም ልብ እንዲሁ። አንተ የቤትህ ራስ ነህ፤ ለሚስትህም እንዲሁ። ሚስትህ ደግሞ በቤትህ ንግስት ብትኾን ንግስትነቷ (መሪነቷ) ከእርሷ ስር ላሉት ቢኾን እንጂ ላንተ አይደለም።

አንተ ራስህን (አካባቢህንም እንዲሁ) የምትገዛ፣ የምትመራ ነህ(መኾንም አለብህ)። ሴቷ ደግሞ ተፈጥሮኣዊ በኾነው ዝንባሌዋ እንዲህ የኾነውን ወንድ ትፈልጋለች።

ዐለም በኪነጥበብ ውጤቶቿ የተፈጥሮኣችንን ተቃራኒ እየነገረች ብታሳድገንም እኔ ግን የተረዳሁትን እውነቱን፣ የነበረውን፣ የቀደመውን ተፈጥሮኣችንን ልንገርህ፦ ሴት ልጅ ራሱን የሚያቅ፣ በራሱ የሚተማመን፣ ራሱን የሚገዛና ከራሱ አልፎ ቤቱን ቤተሰቡን የሚቆጣጠር የሚመራም ወንድ ይገዛታል(ይማርካታል)።

በእርግጥ ከአስተዳደግ በደል፣ ከዘመኑም መጣመም የተነሳ ተምሬያለሁ፣ ንብረት ሰብስቤያለሁ፣ ሰልጥኛለሁ፣ እንዳንተው ትዳር ካልመራሁ ብላ የአባወራነት ሙግት የምትገጥምህ ባትጠፋም።

የሚያሳዝነው ነገር ታዲያ በወንዱ ዘንድ አሁን አሁን እንደምናየው፣ እንደምንሰማውና እንደምናነበውም
? “ንግስቴ ነሽ፣
? እታዘዝሻለሁ
? ካንቺ በቀር ወዴት እሄዳለሁ፣
? የልብ ምቴ ነሽ፣
? እስትንፋሴ ነሽ
? አቴጌ …… “

የመሳሰሉ አባባሎች በዚኽ ዘመን ከሚወጡት የኪነጥበብ ውጤቶች የተነሳ የሚዘወተሩ ኃይለ ቃሎች መኾናቸውን መታዘብ ትችላላችሁ።

ይኽም ታዲያ ትውልዱን ተፈጥሮውን ስቶ፣ የተፈጠረለትን ዓላማ ዘንግቶ፣ ከሚናውም ርቆ፣ ስሜቱን ብቻ በመስማት እንዲነጉድ አድርጎታል። ዓለምም ምንዝር ዓላማዋን በማር ለውሳ በአፈ ቅቤ አሟሽታ ስትጥድ ለእርሱ ያሰበችለት የተቆረቆረችለትም እየመሰለው ያለምንም ግዳጅ ወዶና ፈቅዶ የሚማገድ ኾኗል።

ሳተናው!

ተፈጥሮህን እወቅ ፍጥረትህን ተረዳ። ያንተ ልዕልና እና የሚስትህ ትሕትና እርስ በርስ ተመጋጋቢ ናቸው እንጂ ጌታና ሎሌ(ገረድ) የሚያደርጋችሁ አይደለም። አንተ ግን ሰለጠንኩ ብለህ፣ ወዲህም ዘመንኩ ብለህ ይኽን ተፈጥሮኣዊ ስርዓት ብትገለብጠው አንተም ኾንክ ሚስትህ ሲቀጥልም ትውድም ኾነ ሀገር ተጎጂ ናቸው።

ሚስትህን “ንግስቴ.. ” ብለህ ከእርሷ የምታተርፈው ፍቅር ያለ ከመሰለህ ተ ሳ ስ ተ ሃ ል! በጭራሽ እልሃለሁ፤ አንተ ስለ ሚስትህ በሕልምሕም ይኹን በእውንህ፣ በአንደበትህ ገልጸህም ይኹን በኃሳብህ ይኼን ኃይለቃል የምትደጋግመው ከኾነ ለመታዘዝ ዝግጁ ኹን።

ስትጠራ አቤት ስትላክ ወዴት፣ ስትሰጥ እጅ ነስተህ ስትነሳ ተለማምጠህ …. የምትኖር ከልጆቻችሁ እንደአንዱ አልያም ታማኝ ጃንደርባ ለመኾን ወስን።

ነገር ግን በፍጹም የአባትነት ክብር፣ የባልነት ሞገስ፣ በወንድነትህ የልቧን ምርኮ፣ የራስነትም ስፍራ (የአባወራነት ማዕረግ) በእርሷ ዘንድ እንደማይኖርህ ተረዳ።……

የዛሬ ወንድ አልጋ ሲሉት(ንገስ ሲሉት ይቆየን

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *