አልጫ አትኹን፤ ከአልጫም አትወዳጅ!

ሳተናው!
ከዚኽ ቀደም በአእምሮ፣ በሥነ-ልቦና እና በአካል ብቃት ሊኖርህ ስለሚገባ አቋም በተለያየ ጊዜ ጽፌልሃለሁ።

እርሱም ደግሞ ለራስህ ለጤናህ የሚጠቅምህ ብቻ ሳይኾን ይልቁንስ የተፈጠርክለትንና የምትኖርለትን ዓላማ ከዳር ለማድረስ፤ በእርሱም ውስጥ የተሰጠኽን ሚና በአግባቡ ለመወጣት የሚረዳህ፤ ይኽንንም ትፈጽምበት ዘንድ የተሰጠኽን ተፈጥሮኣዊ ጸጋ ሙሉ ለሙሉ መጠቀም የሚያስችልህ ነው።

ይኹን እንጂ ዛሬ ዛሬ ይኼንን የአእምሮ፣ የስነልቦና እና የአካል ብቃት መያዝ፣ በእነርሱም ልቆ መገኘት እንደ ከዚህ ቀደሙ ዘመናት የሚያስወድስህ አይለም። ይልቁንስ በእርሱ ፈንታ ትውልዱ በኪነጥበባዊ ድርሰት ተፈጥሮኣዊ ጥጉን ለሳቱ፣ በፖለቲካዊ ልከኝነት ለጸደቁ “ፍቅር” እና “እኩልነት” ለሚባሉት ሰላቢዎች ተላልፎ ተሰጥቷል።

ሕብረተሰባችን በኖረባቸው ዘመናት ውስጥ በተፈጥሮኣዊው ስጦታው፣ በኃይማኖታዊው ቀኖናው፣ በባሕላዊው እሴቱ ውስጥ የሌሉ ዐዲስም የተገኙ የሰው ልጅ “የስልጣኔ እውቀቶች” ይመስል “ዴሞክራሴያዊዋ” እና “ሊበራሏ” ዐለም ትውልዱ ላይ ቀድሜ በጠቀስኳቸው ሁለት ቃላት አማካኝነት አልጫነትን ትዘራለች።

በመኾኑም አኹን ያለው ትውልዳችን በተለይም ወንዱን ዐለም ምን ያክል ፈሪ እንዳደረገችው እና ከዚኽም የተነሳ ከየትኛውም የሰው ዘር ከኖረባቸው ዘመናት ይልቅ ስሜታዊ እንደኾነ ሩቅ ሳትኼድ ራስህን በማየት መገንዘብ ይቻላል።

ድሮ ድሮ ፈሪ በማሕበረሰባችን ውስጥ የተናቀ፣ የተወገዘ፣ የተፌዘበትም ነበር። ይኼ ንቀትም ደግሞ በአቻዎቹ ወንዶች ብቻ ሳይኾን በሴቶቹም ዘንድ አስንቆት እርሱን ማግባት የምትፈቅድ ሴትን እስከማጣት ያደርሰዋል።

ዛሬ ላይ ግን ትውልዳችን በስልጣኔ ስም በዘመናዊው ትምሕርት እየላቀ ሲመጣ ለኾዱ ሲል፣ በሰው ዘንድ “መጠላትም ኾነ መጣላት ጥሩ አይደለም” ተብሎ ለመወደድ ሲል፣ ላለመክሰር ሲል፣ ለእርሱ “የተፈጠረችውን አንዲት” ሴት ላለማጣት ሲል፣ ቤቱን በሚመራበት አቋም ቢጸናም ትዳሩ እንዳይፈረስ ሲል ይፈራል።

የተፈጥሮን ሐቅ፣ ገንዘብ ያደረገውንም እውቀት፣ ትምክሕት የሚኾነውንም እውነት(ፈጣሪን) ይዞ ዐለምን አይጋፈጥም። ይልቁንስ ፍርኃቱን የሚደብቁለትን ውሃ የማያነሱ ምክንያቶች እየደረደረ በፈሪነቱ ይሰለጥናል ከትልቅ የአልጫነት ማዕረግም ይደርሳል።

ጀግንነት ከአባት ወደ ልጅ ከጓደኛ ወደ ጓደኛ እንዲተላለፍ አልጫነትም እንዲኹ ነው። የምትውልበት ቦታ፣ የያዝከው የሥራ መስክ፣ ጓደኞችህ እናም እውቀትን የምትቀስምበት መንገድ “እውቀቱም” ጭምር ያንተን ወኔ በመስለብም ኾነ በመካብ ትልቁን ሚና ይጫወታሉ።

በተለይም ደግሞ በአካዳሚክ ጥናትህ እየገፋህ ስትኼድ በኑሮ መንገድህ ላይ በምትወስዳቸው ውሳኔዎች ላይ መጠነኛ ጥናት አድርገህ አንዱን አንስተህ ወደተግባር ከመቀየር ይልቅ ብዙ ግራና ቀኝ ስታማትር ፈሪ ትኾናለህ። “ተምሬያለሁ” “አውቃለሁ” ብለህ ታስባለህና መሳሳትን ትፈራለህ።

ቁምነገሩ ግን መሳሳትን በፈራህ ቁጥር አልጫነትክን፤ ደፍረህ ወስነህ በሞከርክ ብሎም በተሳሳትክና እራስህንም አርመህ በተመለስክ ቁጥር ጀግንነትክን እየገነባህ መኼድህን አስተውል።

ዛሬ ላይ እኛ ወላጆች ፈሪ ኾነን ልጆቻችንን ዘለው በመውደቅ፣ ሞክረው በመክሰር፣ ተፈትነው በማለፍ፣ አደጋን ተጋፍጠውና ተጋግጠው የሚያገኙትን ወኔ እኛ በ”ሰላማዊ” ክበብ ውስጥ በማኖር እናሳጣቸዋለን የወጣላቸው ፈሪ እናም ስሜታዊ እያደረግናቸው እንገኛለን።

ሴቶችና የወንድ አልጫ…..

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *