አባወራነት፦ ራስን አውቆ፣ ይዞና ተማምኖም ለቤቱ መትረፍ

ሳተናው!
የሰው ልጅ አብዛኛውን ጊዜ ራሱን ለማወቅ ከሚጥረው ጥረት ይልቅ ሌሎች ፍጥረታትን እና አካባቢውን ለማወቅ የሚያጠፋው ጊዜ በጣም ብዙ ነው።

ራስህን አለማወቅህ ተፈጥሮኣዊ ስጦታህን (ጸጋህን) በግልጽ አለመረዳትህ ምን እንደተሰጠህ እና ለማንስ መስጠት እንዳለብህ ከእነርሱስ ምን መጠበቅ እንዳለብህ ለማወቅ ይሳንሃል።

ሲጀመር ከባለጸጋው ፈጣሪህ ዘንድ ምን እንደተሰጠህ ካላወቅህ በራስመተማመንህ አሽቆልቁሎ ፈሪ፣ ስጉ፣ አልጫም ኾነህ በእነዚህ ድምር ውጤትም ኾነ ስብጥር
የወጣለት ምስኪን ትኾናለህ።

ሳተናው!
በራስመተማመንህ ደካማ ከኾነ ለሚስትህ፣ ለልጆችህ(ለትውልድ)፣ ለሀገርም አትበጅም። ይኹንና ብዙዎቻችን ስጦታችንን(ጸጋችንን) ካለማወቃችን የተነሳ ያጣነውን በራስመተማመን የ”ፍቅር”፣ የ”ስልጣኔ” እና የ”መንፈሳዊነት” ካባ እያለበስን ለስንፍናችን ማምለጫ ለፍርሃታችንም መተንፈሻ የስርቆሽ በር እንከፍታለን።

ነገር ግን ራስህን ስታውቅ የተሰጠህ ጸጋ ምን እንደኾነ ታውቀዋለህ። እርሱን ስታገኘው፣ ወደህ ስትይዘው እና ስታበለጽገውም በራስመተማመንህ ይጨምራል። በዚኽም ለሌሎች ስለምትሰጣቸው ስጦታና በምትኩ ስለምታገኘው ነገር ግልጽ አቋም ይኖርሃል።

በተለይም ደግሞ ከሴቶች ሁሉ አስበልጠህ ለወደድካትና ለልጆችህ እናት ለኾነችው ሚስትህ ይኽ በተፈጥሮ የተቸርከውን ጸጋህን የሚስተካከል ስጦታ ከግዑዙ ዓለም ፈጽሞ አይገኝም።

ለሚስትህም ኾነ ለልጆች የምትሰጠው ስጦታ ፈጣሪ አንተ ውስጥ በዓላማ ካስቀመጠው ለቤትህ፣ ለትዳርህ፣ ለልጆችህ እንድትኾን ግድ ከሚልህ እና በእርሱም ከምታርፍበት (ከምትረካበት) የፍቅሩ ስጦታ የመነጨ ነው። አንተ አክብረህ ተቀብለህ እንደምታቀብለው ሁሉ እነርሱም አክብረው ሊቀበሉህ ይገባል።

ስጦታ በቁሙ ፍቅር ሳይኾን የፍቅር መገለጫ ነው። አንተ ከመውደድህ ብዛት ደምና ላብህን ገብረህ በሸመትከው ስትሰጥ፤ ሚስትህም ኾነች  ልጆችህ ላንተ ያላቸውን ፍቅር ስለስጦታህ ላንተ አክብሮትን ያሳያሉ።

ይኽ ካልኾነ ግን የውለታህ ብዛት የስጦታህም መትረፍረፍ በሚስትህም ኾነ በልጆችህ ዘንድ ያስወድደኛል ብለህ አታስብ። ይልቁንስ የባለዕዳነት ስሜት አንዳንዴም “ግዴታው እኮ ነው!” ወደሚል የንቀት አቋም ያደርሳቸዋል እንጂ።

================

ሳተናው!
በሚስትህም ኾነ በልጆችህ ዘንድ የምታያቸውን የቤትህን ስርዓት እና ስነምግባር የተከተሉትን ጠባዮች ብቻ አበረታታ፤ በስጦታም ደግፍ። በጭራሽ ስርዓተቢስነትንም ኾነ ኢ-ስነምግባራዊ ድርጊትን ለመሸፋፈን፣ ለማረሳሳት፣ ለማስተባበልም ኾነ ለማባበል ብለህ በስጦታ(በማበረታቻ) አታበላሻቸው።

ልብ አድርግ!
ራስህንና ያለህን ጠንቅቀህ ስታውቅ እናም ከእርሱ ጨልፈህ ስትሰጥ በሚስትህም በልጆችህ ዘንድ ስለስጦታህ አንተ አክብሮትን ማግኘት አለብህ። ሚስትህ ስጦታዎችህን የማታከብር የምትሳለቅባቸው ከኾነ ልጆችህም እንዲሁያደርጋሉ። አንተ ደግሞ ይኼንን ንቀት በ”ፍቅቅ”፣ “ስልጣኔ” እና “በመንፈሳዊነት” ካባ ከተቀበልክ ራስህን፣ ስጦታህን የማታውቅ፣ ያቀለልከው ኋላ ላይም አመድ አፋሽ የሚያደርግህ ምስኪን ትኾናለህ።

ይኽ እየኾነ ግን እንወድሃለን ቢሉህ በአፋቸው እየደለሉህ እንደኾነ እወቅ። ስለኾነም ትዳርም፣ ትውልድም የማይወጣልህ ብኩን ኾነህ ታርፈዋለህ።
===============
? “እኔ አላገባሁም በጓደኝነት ከያዝኳት ሴት ጋርስ ….?” ያልከኝ እንደኾነ፤ እርሷን ከመውደድህ የተነሳ ከችግሯ ስትታደጋት ከፍጹም ርህራሄህ ከኾነ ጥሩ፤ ነገር ግን በኾድህ “ባደርግላት ትወደኛለች” ብለህ ከኾነ በከንቱ ከሰርክ።

ምክንያቱም እንዲህ አስበህ ብታስተምራት፣ እናቷን ብትጦርላት፣ አባቷን ብታስታምምላት፣ በስሟ ቤትም ኾነ መኪና ብትገዛላት ውለታ ታበዛባታለህ እንጂ ልቧን በፍቅር አታሸንፍበትም። በዚኽም ደግሞ ከውለታህ ብዛት የተነሳ በማትፈልገው ትዳር ውስጥ ታስራና ልጅ ወልዳ እንድትኖር ታደርጋታለህ እንጂ።

? “ስለዚህ?” ስለዚህማ ከተዋወቅካት ሴት ጋር በትዳር ተሳስረህ የመኖር ሀሳብ ካለህ እና ለእርሷም ይኼን ካሳወቅክ ስለስጦታህ(ስለጊዜህ፣ ስለገንዘብህ፣ ስለጥበቃህ፣ ስለቃልህ ….) መከበርህን አረጋግጥ። ይኽ ካልኾነ የራስህንም ኾነ በእጅህ ያለውን ስጦታ ዋጋውን ስታውቅ አታባክን።

? “ነገር ግን ለጓደኝነት የመረጥኳትን ሴት ስለስጦታዬ(ዛሬም ኾነ ወደፊት) እንደምታከብረኝ ማወቅ እኮ ከባድ ነው?”

እኔ ግን እልሃለሁ በጣም ቀላል ነው።

ሳተናው!
አንድነገር ላስታውስህ መጀመሪያ አንተ በወንድነትህ የተሰጠህንና ለሚስትህ ልትሰጣት ልታደርግላት ስለሚገባህ ስጦታ ጠንቅቀህ እወቅ። ያወቅከውን ያዘው፣ አበልጽገው እና ኑረውም።

ይኽ ራስህን በመኾን የራስመተማመንህን ሲጨምረው ለማን፣ ምን፣ እንዴት፣ ምንያክል፣ በምን ፈንታ መስጠት እንዳለብህ ያስገነዝብሃልም።

ይኽ ከኾነ የመረጥካት ሴት ስጦታህን የምታከብር ትኹን አትኹን እንዴት እንደምትለይ እነግርሃለሁ።
“መቼ?”      ቅዳሜ ጥቅምት 9 2012 ዓ.ም.
“የት?”        ፒያሳ ኤልያና ሆቴል
ዝርዝሩን ከታች ባለው አስተያየት መስጫ(comment) ሳጥን ውስጥ ተመልከት…. ይቆየን

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *