አባወራውን መታደግ(በመኝታ ቤቱ….ካለፈው የቀጠለ)

ወንድሜ ከዚህ በታች የተጻፈው የሚስቱ ደስታ፣ የትዳራቸው ስኬት፣ ለሚያሳስበው ወሲብን(ተራክቦን) የፈጣሪ ስጦታ ነው ብሎ በአንድ ሚስቱ ተወስኖ ለሚኖረው፣ በዚህም ኃላፊነት ለሚሰማው አባወራ ነው። አንተ “ያስከፋኛል” “ያናድደኛል” የምትለኝ ወዳጄ አታንብበው። አንብበኸው ከስድብ ኃጥያት ከምትወድቅብኝ።

አንድ ነገር ግን ቃል ግባልኝ “pornography” እንደማትመለከት ሁልጊዜ አስጠነቅቅሃለሁ እርሱ አጥፊህ ነውና።

4 ቅድመ ጨዋታ
ሾፌር መኪናው ብትነሳም በእርሷ ውስጥ ያለውን ከፍተኛውንና እምቁን ኃይሏን ለመጠቀም እንዲያሞቃት አባወራም በሚስቱ ውስጥ ያለውን ከፍተኛውን የእርካታ ጣሪያ ለመድረስ ያሞቃታል(በፀሐይ ወይም በእሳት ያልኾነ ሙቀት ነው)።

ልብ በሉ! የብዙዎቻችን ወንዶች ችግር ይህ ነው የትም(በሥራ፣ በትምህርት፣በማሕበራዊ ጉዳዮች) ስንባዝን ውለን አልጋ ላይ እንደወጣን ቀጥታ ወደ ጉዳያችን መሄድ እንሻለን። ተራክቦ ምንም እንኳ በዓይናችን በሚታየው በሴቷና እና በወንዱ መካከል በሚፈጸመው ስጋዊ ፍትጋጊያ እውን ቢኾንም በተለይ ለሴት ልጅ ግን ፍጹም ልቦናዊ ነው፤ “ምን?” አዎን ልቦናዊ ነው። ይህም ማለት በልቧ ውስጥ አንተን ማሰብ፣ ስላንተ ማሰብ፣ አለባት። ምንያክል ቆንጆ እንደኾነች አንተም የእርሷ፣ እርሷም የአንተ፣ አንተ እና እርሷ ምሉዕ እንደኾናችሁ የመሳሰሉትን ልትነግራት ……. የተገባህ ነው።

ይህ ሲኾን ዐይኗ ይከደናል የሚያመዛዝነው፣ የጭንቅላቷ ክፍል እረፍት ይወስዳል፣ ልቦናዋ ይሰማሃል፣ ልቦናዋ ደግሞ ከአእምሮ ይልቅ ሰውነትን የመግዛት ኃይል አለውና ሰውነቷን ይሰጥሃል። በዚህ ጊዜ ብቻ ሚስትህን ማስደሰት፣ ተወዳዳሪ የማይገኝለትንም እርካታን መስጠት ይቻልሃል።

ልብ አድርግ! ዝም ብለህ እንዳዋዋልህ ዘው የምትልበት እልፍኝ አይደለም። ብትል ግን የእርሷን ፍላጎት ዘንግተህ፣ የራስህን ፍላጎት ፈጽመህ፣ እርሷንም አስቀይመህ ለሌላው ቀንም ፍላጎቷን ዘግተህ ትሄዳለህ።

5መንደርደሪያ

ሾፌር መኪናው ምን ብትሞቅ እርሱም ምን ቢቸኩል ወዲያው በአምስተኛው ጥርስ(ማርሽ) እንደማይነዳት አባወራም ሚስቱ ምን ብትሞቅ ችኮላ የለበትም። ልብ በል! ችኮላ የምስኪን ነው።ምስኪን ተለማምጦ፣ ደጅ ጠንቶ፣ ወይንም አይኑን አጉረጥርጦ፣ ተበሰጫጭቶ የፈለገውን ያገኛል ወይም ይወስዳልም። ለድርጊቱም የተራበን እንሰሳ ይመስላል፤ ቸኩሎ ይገባል ቸኩሎም ይወጣል። ለአባራው ግን እንዲህ አይደለም
* ሲጀምር አይለማመጥም፣ ደጅም አይጠናም
** ሲቀጥል ፍቅርን እርካታን ይሰጣል እንጂ አይወስድም፤ ወሰደ ቢባልም በመስጠቱ የሚያገኘው፣
የሚኾንለት ነው።
*** አይቸኩልም ያሰበው የሚከናወንለት፣ ድርጊቱን በመዳፉ ሥር የጨበጠ፣ ምን
መስጠት እንደሚችል ምን ማግኘትም እንዳለበት ጠንቅቆ የሚያውቅ ነው።

**** ወንድሜ አንተና ሚስትህ በየትኛውም የእድሜ ክልል ብትኾኑ ለተራክቦአችሁ መቀጣጠል አስፈላጊው ሙቀት ላይ ለመድረስ ከአንተ እርሷ ትዘገያለችና ድርጊትህ በማስተዋል ይኹን።

**** አንተ እንደ ብረት ምጣድ ነህ የሚንቀለቀል ጭራሮ ላይ ቢጥዱህ ባንዴ ትሰማለህ። እርሷ ገበር ምጣድ(ከሸክላ የተሠራ የዳቦ ምጣድ) ነች ጊዜ ሰጥተህ ልታሰማት የተገባህ ግ..ዴ..ታ..ህ..ም ነው።!!!!*****

6 መነሻ
ሾፌር መኪናው ስትሞቅ አንደኛ ጥርስ(ማርሽ) አስገብቶ ይነሳል፤ የሞተሯንም ድምጽ እየሰማም በደረጃ እያሳደገው ይሄዳል። አባወራም ከቀላል ውዝዋዜ ተነስቶ የትንፋሿን ክብደት የልብ ምቷን ፍጥነት በማዳመጥ የሚጨምረው ፍጥነት በደስታ መንኮራኩር ሾር ያደርጋታና ….ይቆየን

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *