አባወራውን መታደግ(በመኝታ ቤቱ….ካለፈው የቀጠለ)

ከታች የተዘረዘረው እየጠፋ ለመጣው አባወራነት መታደጊያ ይኾን ዘንድ ነው። አንተ የቱ ጋር ነህ?

የዛሬው ጽሑፍ ስለ ግልጽነት ሲባል በቋንቋ አጠቃቀሙ በመጠኑ ለቀቅ ያለ(explicit) ነውና ቅር ሊያሰኛችሁ የምትችሉ የራሳችሁን ጥንቃቄ ውሰዱ።

ለአባወራ ከሚስቱ ጋር የሚፈጽመው የወሲብ ፍልሚያ (የሚስቱን ወሲባዊ ፍላጎት መፈጸም) ከመስክ(ከቢሮ) ሥራው እና ከእልፍኙ ኃላፊነት ቢበልጥ እንጂ አያንስም። እናስ? እናማ በሩን ከዘጋበት ደቂቃ አንስቶ መሪው እርሱ ነው። የአባወራው የተራክቦ ስኬት በዋነኛነት ከዚሁ በልዕልና ካለው መሪነቱ ነው። በእርግጥ የተዋጣለት መሪ ለመኾን ታዛዥ አስፈላጊ ነውና (ወደር የለሿን)የአባቷን ልጅ ምርጫው ያደርጋል።

አባወራው እና ሚስቱን በተለይ በመኝታ ቤት ጨዋታቸው ተጠቃሚ ለመኾን ለየቅል የኾነ ሚናቸውን እናያለን።ነገር በምሳሌ ጠጅ በብርሌ እንዲል ብሂለ አበው፤ ምሳሌም እናንሳ፦ አባወራውን በሹፌር ሚስቱን በመኪና ልመስልና ንጽጽራዊ ሀተታን ልጠቀም።

1 ዐላማ አለው
ሾፌር ዐላማ አለው አንድ ቦታ መኪናውን ማድረስ፤ በዚህ የእርሱም መድረስ ይረጋግጣል። አባወራም ዐላማ አለው፤ ሚስቱን የድንቅ እርካታ ባለቤት ማድረግ በዚህም ውስጥ የእርሱ እርካታ እውን ይኾናል። ልብ አድርግ! ለአባወራ ሚስቱን በወሲባዊ እርካታ ከአልጋ ላይ ነጥቆ ዐለሟን ማሳየት ምትክ የሌለው ደስታው ነው። ይኽም በእርሱ መሪነት ብቻ እውን ይኾናል።

2 በወሲባዊው ልፊያ አንተ መሪ እንጂ ተከታይ አይደለህም
መኪና ምን ምርጥ ብቃት ቢኖራት አንድ ቦታ ለመድረስ ሾፌር ያስፈልጋታል። ሾፌሩም ማስነሳት እና መንዳት ይጠበቅበታል። የሹፌር ቦታ መቀመጥ ብቻውን፣ አልያም ሳያስነሱ አትሄድልኝም ማለት በዛሬ ጊዜ አትስመኝም፣አትወደኝም ብሎ እንደሚያላዝን ምስኪን ነው። ሚስትህም ምንም እንኳ ተፈጥሮኣዊ የኾነ የተራክቦ ፍላጎት ቢኖራት አነሳሹ፣ ቀስቃሹ፣ ጀማሪው፣ መሪው እና አድራሹም አንተ ነህ። በውጭ(በኣፍኣ) ምን ተጫዋች እና ግልጽ ብትኾን መኝታ ቤት ግን መጥታ እስክትስምህ፣ ልብሷን እስክታወልቅ፣ አልያም መውደዷን እስክትነግርህ አትጠብቅ ጾታዊ ጭምትነቷ፣ ባህላዊ አይናፋርነቷ፣ መንፈሳዊ ትሕትናዋ እንዲህ እንዳትኾን ይከለክሏታልና። ስለዚህም እነዚህን ኹሉ ባንተ መሪነት አድርጋቸው።

3 ቅድመ ምርመራ
ጎበዝ ሾፌር መኪናውን ከመንዳቱ በፊት አኹን ያለችበትን አቋም ይፈትሻል። ካሰበው ቦታ ለመድረስ አጉል ቦታም እንዳይቀሩ አስቀድሞ ይጎበኛታል። ጎማ ይቀይራል፣ የራዲያተር ውሃ ይሞላል፣ ዘይት ይጨምራል…. እንደ አስፈላጊነቱ፤ እንጂ እንከን በገጠመው ጊዜ ኹሉ ትቷት አይሄድም።

አባወራም ወደ ወሲባዊ ልፊያ ከመግባቱ በፊት ያለችበትን ስሜታዊ ኹኔታ ይፈትሻል። ስሜቷ ጥሩ እና ግልጽ ከኾነ እሰየው ይቀጥላል። አልያ ግን ስሜቷን አድሶ እና ወደሚፈለገው አምጥቶ ይወስዳታል እንጂ እንደ ምስኪን ሰኞ “ራሴን” ስትለው “እሺ ውዴ ተኚ”፣ ማክሰኞ “ወገቤን” “እሺ ተኚ”፣ ረቡዕ “ደብሮኛል”…… “እሺ”፣ ሐሙስ “ሥራ አናዶኛል”…… “እሺ”፣ ዐርብ “ደክሞኛል”…”እሺ”፣ ቅዳሜ “ሰንበት እኮ ነው”…፣ እኹድ “ዛሬን እንኳ እስቲ ልረፍ” ሲባል “እሺ” እያለ አይተዋትም። ከነገረችው ሰበብ በእጅጉ የራቀ ሌላ ምክንያት እንዳለ ይገባዋል፣ ይህ ሰበብ ድርደራ በዚህ ከቀጠለ ለትዳር አስጊ ነውና፣ መፍትሔ ያበጅለታል።

አሞኛል ብትለው እኔ መድኃኒትሽ የት ሄጄ፣ ወገቤን ስትለው ጣቶቼ ምን ሥራ አላቸው አሽቼ እያለ ስሜቷን ወደ ተፈላጊው ሁኔታ ማምጣት የእርሱ ሥራ ነው። ይህን ባትቀበል ግን….. የላቀውን (advanced course) በጊዜው እንደርስበታለን።ትልቁ የአባወራው ጥበብ ሚስቱን የአፏን ሳይኾን የሠራ አካላቷን ግብረ-መልስ መከተሉ ነው በዚህም ይሳካለታል፤ እርሷም ደስተኛ ነች፣ እንደኾነችም አይጠይቅም፣ ያውቃላ።

ምስኪኑ ግን ሙሉ በሙሉ የአፏን ይሰማል፣ያምናልም ፣ “እንዴት ነበረ?” ብሎ ይጠይቃል ፤ ውጤቱ ግን ኹለቱንም ያስከፋል።

4 ቅድመ ጨዋታ
ሾፌር መኪናው ብትነሳም በእርሷ ውስጥ ያለውን ከፍተኛውንና እምቁን ኃይሏን ለመጠቀም እንዲያሞቃት አባወራም በሚስቱ ውስጥ ያለውን ከፍተኛውን የእርካታ ጣሪያ ለመድረስ …… ይቆየን

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *