አባወራውን መታደግ

ወንድሜ ምንም እንኳ በተፈጥሮአዊ ጾታህ ወንድ ለመባል ከነቃጭልህ መወለድህ በቂ ቢኾንም ወንድነትን ግን የወለዱህ(ያሳደጉህ) ቤተሰቦች፣ የምትኖርበት ሕብረተሰብ፣ የተገኘህበት ዘመን እና የምትውልበት ቦታ ይሰሩታል። እኔ እና አንተም የእነዚህ ድምር ውጤት ነን።

አኹን ላለንበት የወንዳወንድነት መጥፋት፣ ኃላፊነት የሚሰማው፣ መምራት፣ መወሰን ማድረግ ለተቸገረው፣ ሚስቱን ማስደሰት ግራ ለተጋባው ወንድ መገኘት እነዚህ የጠቀስናቸው ቀጥተኛ አስተዋጽዖ አላቸው።

እንዲሁም ሴቶችን እና ሕጻናትን ለሚበድለው፣ ከየት እንደመጣ ወዴትም እንዲሄድ ለማያውቀው፣ የማንነት ጥያቄ ላለበት ትውልድ መፈጠርም እነዚሁ ከላይ የዘረዘርናቸው ነጥቦች ዐይነተኛ ሚና ይጫወታሉ።

ዛሬ ዛሬ ወንዶች ልጆች የሚያድጉበት መንገድ፣ በተለይ ከማሕበረሰባቸው የሚደርስባቸው ኢ-ተፈጥሮአዊ ጫና፣ ዘመን አመጣሽ የኾኑ ስልጣኔ ተብዬ የኑሮ ዘዬዎች፣ አንዳንዴም የሚሠሯቸው ሥራዎች ወንድነታቸውን ከማጠናከር ይልቅ ሲሸረሽረው ይታያል።

ይኽም በመኾኑ በትዳራቸው ማረፍም ኾነ ሚስቶቻቸውን ማሳረፍ አልተቻላቸውም። አመንም አላመንም ይኼ አኹን ላይ በሃገራችን ብሎም በዓለማችን ያሉትን ትዳሮች እየፈተነ ያለ ክፉ በሽታ ነው።

አዎን! አብዛኞቹ ወንዶች ተፈጥሮ ካስቀመጠቻቸው ቦታ የሉም። ዐላማቸው ጠፍቶአቸዋል፣ የሕይወት አቅጣጫቸውን ስተዋል፣ የተፈጠሩበትን ምክንያት አጥተውታል፣ ርዕይ አልባም ኾነዋል። ለዚህ ደግሞ አኹኑኑ መፍትሄ ካልሰጠነው እንደ ምዕራብያውያኑ መረን መኾናችን አይቀርም።

ይህን ለውጥ ለማምጣት ደግሞ ሴቶች ላይ ጣትን መቀሰር አያስፈልግም። አንተ እና እኔ ብቻ ስንለወጥ፣ አንተ እና እኔ ብቻ ወደ ቦታችን ስንመለስ፣ አንተ እና እኔ ብቻ አባወራ ስንኾንይህን ችግር እንቀርፈዋለን። ለመለወጥ ጊዜው ረፍዷል እድሜዬም ገፍቷል አትበል ነገ ልትሞት ዛሬን ወንድ ኾነህ ማደርህ ራሱ ከራስህ አልፎ ትውልድን በመቅረጽ ሂደቱ ላይ ዐይነተኛ ሚናይጫወታልና።

አባወራን ወደ ሕይወታችን ስንመልሰው ምስኪንነታችንን ሸኝተን ነው። አባወራ በሙሉ ክብሩ ሲመለስ ታዲያ አይደለም ድርጊቱ ግርማ ሞገሱ፣ ትከሻው በቂ ነው፣ በራስ መተማመኑማ አይጣል ነው፣ መሽቶ ድምጹ እስኪሰማ፣ ኮቴው እስኪለይ ይናፈቃል፣ የቤቱ ሞገስ፣ያለመደፈርራቸው አርማ እርሱ ነውና። ይህ ግን የአባትነት ፍቅሩ፣ የባልነት ክብሩ፣ የወንድነት ግብሩ፣ የራስነት ማዕረጉ (አባወራነቱ) ለገባቸው ነው።
አባወራ በመስክ ላይ
አባወራ ከምስኪኑ የሚለየው አንድ መሠረታዊ ጠባይ አለው። እርሱም አብዛኛውን ጊዜ ሚስቱም ኾነች ልጆቹ የሚያስፈልጋቸውን እንጂ የፈለጉትን አለማድረጉ ነው። ይኼን ሲያደርግም ለጉልበቱ መሳሳት፣ ለጤናው መጠንቀቅ፣ ለሕይወቱም መጨነቅ ሳያስፈልገው የእጁን የድካሙን ፍሬ ይዞ ይመጣል።
አባወራ በእልፍኙ
እርሱ በቤቱ ቤተሰቡ የታነጸበት መሠረት፣ ለስነ ስርዓታቸውም ልክ የማዕዘንም ድንጋይ ነው። ማንኛውንም የቤተሰቡ አባል(ሚስቱንም ጨምሮ) ከስርዓቱ ወጥቶ ቢያይ በመምከር ጀምሮ በመገሰጽ ደግሞ በቅጣት አሠልሶ ይመልሰዋል እንጂ አይቶ እንዳላየ አያልፍም። ይህ ትልቁ የሚያስጠይቀው ኃላፊነቱ ነውና።

በመኝታ ቤቱስ ቢኾን? አጅሬ አባወራ?
እውን እንደምስኪን አባወራ ከአልጋው ላይ ወጥቶ ያቺ በጉጉት እና በናፍቆት የምትጠብቀውን ሚስቱን ይዘነጋልን? በጭራሽ! ወይስ የራሱን ስሜት ብቻ ተከትሎ በሶስት ደቂቃ ውዝዋዜ አይሉት ንጥሻ ጢቅ ብሎ ይተኛል? በጭራሽ! የመኝታ ቤቱማ ከቀደሙት ከመስክና ከእልፍኝ ግዴታዎቹ ቢበልጥ እንጂ አያንስም። እ..ና..ስ..? እናማ አጅሬ በሩን ከዘጋበት የምሽቱ ቅጽበት አንስቶ ሰማይ አመድ የአህያ ኾድ እስኪመስል …..ይቆየን።

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *