አባወራው በልዕልና ሚስቱ በትሕትና፤ ወደር የለሽ ትዳር

ለድስት ግጣሙ ልከኛ የኾነ ክዳን እንደኾነና ክዳን ደግሞ ከድስት በላይ ስለዋለ ክብሩ ከድስት እንዳይበልጥ። ለሚስትም ትሕትና ግጣሙ ልከኛ የኾነ የባል ልዕልና ሲኾን ባል ደግሞ በሚስቱ(በቤቱ) ያለው ልዕልና በሰብዓዊ ክብር ከሚስት አያስበልጠውም(እኩል ነው)።

ድስት ክዳኑን ሲያገኝ ምሉዕ እንዲኾን አባወራም ሚስቱን ሲያገኝ ሚስትም ባሏን ስታገኝ የሚሟሉ ልከኛ ግጣሞች ይኾናሉ። የሚስት ጠባዮችም ከአባወራው ጠባዮች ጋር እንዲሁ የሚሟሉ ናቸው እንጂ ተፎካካሪ አይደሉም። ስለኾነም የአባወራው ልዕልና ለሚስት ትሕትና ልክክ የሚል ልከኛ ግጣም ነው።

ሚስትህ ላንተ ትሑት መኾኗ አግባብ ነው። የአንተ ለእርሷ ያለህ ትሕትና ግን ያለቦታው የገባ ትርፉም ኪሳራ ነው። አንተ ትሕትናን ለወላጆችህ፣ ለመምህራንህ፣ ለሥራ ኃላፊዎችህ፣ ለመንፈሳዊ አባቶችህ፣ ለሃገርህ መሪ(ለባለስልጣኑ)፣ አሳይ በቤትህ ግን አንተ ንጉስ፣ልዑል፣ራስ ነህ።
****
ይሄን ከሴቶቹ ትሰማላችሁ ነገሩም እንዲህ ነው፦ በተጋባችሁ በመጀመሪያዎቹ ወራት ሚስታችሁ የምትሰጣችሁን ስም ማስተዋል በቂ ነው። ጌታዬ፣ ንጉሴ፣ አባዬ ተብላችሁ አታውቁም?(በተለይ ከወደጓዳ)? ይህን ሴቷ ስትናገር በስሜቶቿ ተጽዕኖ ሥር ከሚወድቀው አካሏንም ከሚያስተዳድረው ልቦናዋ አንቅታ ነው። ዋሽታለች ወይ? በጭራሽ! ልክ ነበረች።

ለምን አልቀጠለችበትም እርሱ የእኔ እና ያንተ ችግር ነው። ተወደድኩኝ ፣ወደድኩኝ ብለህ እርሷ በትሕና ዝቅ ስትል አንተም ካልተነጠፍኩ ማለትህ ስህተት ነው። አንተ በልዕልና ኾነህ እርሷን በእቅፍህ ከፍታ ወደ እርካታ ማማ ልትሰቅላት፣በቤትህ ልትሾማትና በመኝታህም ልትሸልማት የተገባህ ነህ፤ ይህም የውዴታ ግዴታህ ነው።

አንተ ወንድሜ ስወድህ! ከደረትህ ነፋ ከአንገትህም ቀና በል ትሕትና ዋጋ የምታገኝበትም እንኳ ቢኾን በተገቢው ቦታ ለተገቢው ሰው ሲኾን እንጂ ልዕልናህ ሲፈለግ ትሕትና አሳያለሁ ብትል “የአህያ ስጋ አልጋ ሲሉት አመድ” የሚለው ተረት ደርሶብህ ተንቀህ ፈተና ውስጥ ትገባለህ። በዚህም ደግሞ ሰማዕትነትን እያተረፍኩ ነው በለኝና ምን ያክል ከድጡ ወደ ማጡ እንደምትሄድ ልነግርህ እችላለሁ። ደግሞስ ሚስትህ ተፈጥሮዋ የፈለገውን ለትህትናዋ ተስማሚ የኾነውን ልዕልና ሳትሰጣት፣በስሜት ማዕበል ለሚናጠው ልቧስ ወደብ ሳትኾናት? እንዴት? ፈተናን በራስህ አለማወቅ ወይም ስንፍና ጠርተኸው ማጣፊያው ሲያጥርህ ሰማዕት እኾናለሁ ትለኛለህ?
ፈጣሪ የጣለብህንስ የራስነት አደራ የት አሽቀንጥረህ ወይም ቀብረህ ነው? ራስነትህ እኮ አንድም ልታገለግልበት የተሰጠህ መክሊትህ ነው። የራስክን ቀብረህ በሌላ ሰው መክሊት መመጻደቅስ ምን ይሉት ነው?

አስተውለህ አንብብ! “ትዕቢተኛ ኹን፣ ክብር አትስጣት፣ ልትንቃትም ይገባል” አላልኩህም ይህ ካንተ ይራቅ።
በመንፈሳዊ ሕይወት በትሕትና እንመላለሳለን ለሚሉ ጥንዶች ትልቁ ፈተናቸው ይህ ነው። የእርሱን የአደባባይ ትሕትና ጎረቤት፣ ዘመድ አዝማድ፣ ጓደኛ፣ ሚስትም ራሷ የመሰከሩለት ነው። ስህተቱ የቱ ላይ ነው ይኼን ትሕትናውን ይዞ ወደ እልፍኙ እና ወደ መኝታቤቱ መግባቱ ነው። የተፈጥሮውን ፍላጎት እንደመፈጸም አስሬ ይጠይቃልና፤ ትሑት ነዋ!

በዚህን ጊዜ ሚስት ምን እንደኾነ የማታውቀው፣ ነገር ግን ትክክል ያልኾነ ነገር እንዳለ ይሰማታል (አንተ እና እኔ አናውቅም እመነኝ)። ላንተ የፍቅር ጨዋታ የሰውነቷ ግብረ-መልስ እየቀነሰ ይመጣል፣ ፍላጎቷም እንዲሁ፣ ሰበብም እያመጣች ከአልጋው ወግ ትርቃለች(ይኼን ጊዜ ነው እኔ እና አንተ ችግር እንዳለ የምንጠረጥረው)። እርሷን ግን ውስጧን እረፍት የነሳ ይኼነው የማትለው ነገር ገጥሟታል። ለማንስ ይወራል? እርሱ ባሏ ዐለም ያጨበጨበለት ትሑት? ስታገባው “ዝኾን ሎተሪ ወጣልሽ” ተብላ? ምኑ ጎረበጠኝ ትበል?

ትወደዋለች እኮ፣ የልጆቿ አባት ነውና፣ ትወደዋለች እኮ ምናልባትም የመጀመሪያዋ ነውና፣ ትወደዋለች እኮ በተቻላት መጠን ራሷን የገለጸችው ለእርሱ ነውና። ግን አንድ ነገር ጎድሏል እርሱም የእርሷን ትሕና ልክክ አድርጎ የሚገጥም ልዕልና ከባሏ ዘንድ የለም። ይህ ባለመኖሩም ምን አብረው ቢተኙ፣ ምን ተራክቦ ቢፈጽሙ እርሷን ግን እርፍ የሚያደርግ አይኾንም፤ እርሷ እንጂ አድራሽ እርሱማ ኹሌ ይገላገላል።

አኹን ልዕልናህን የምትታዘብበት ቀላል የቤት ሥራ ልስጥህ ከእልፍኝህም እንጀምር
1 በእልፍኝህ የTV remote control በማን እጅ ነው? በአንተ፣ በሚስትህ፣ በልጅህ፣ በሌላ
2 TV የሚታይበትን ፣የጥናት፣ የቤተሰብ ጨዋታ፣የጸሎት ጊዜ ማን የወስናል?
3 በእልፍኝህ የመተዳደሪያ ስርዓት አውጪው ማን ነው?
4 ስርዓቱ እንዳይጣስ ማን ያስከብራል? ቢጣስስ ማን እርምጃ ይወስዳል?
5 የእረፍት ቀናችሁን መርሃ-ግብር ማን ያወጣል?….
የኹሉም ልስ፦ አንተ አባወራው መኾን አለበህ።
በመኝታ ቤትህስ ትሑት ነህ ወይስ ልዑል?
1……. ይቆየን

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *