አባወራው 

ከዱርየው ስንሸሽ፣ ከሴት አውሉም ስንርቅ፣ ምስኪኑንም ታዝበን ስንጨርስ አባወራውን ብቻ በትክክለኛው ቦታው እናገኘዋለን።

ሦስቱ ከላይ የጠቀስናቸው እንደፀባያቸው ልዩነት ብዙውን የተፈጥሮ ጠባዕይ ጥለው ጥቂቷን ብቻ አንጠልጥለው ጉዞኣቸውን በራስወዳድነት የተሞላ የግል ጥቅም ያጠናቅቃሉ። አባወራው ግን ስጋዊ ባሕሪውን ሳይዘነጋ፣ በአርአያ ሥላሴ የተፈጠረ ሰብዓዊነቱን ግምት ውስጥ ከቶ ለተፈጠረበት ሕያው(ዘልዓለማዊ) ዓላማ ሲል ሚናውን ይለያል ጥቅሙንም ያጋራል።

አባወራው ተፈጥሮአዊ የሥጋ ጠባይን በተረዳ መንገድ ሚስቱን ያስደስታታል፣ ይወዳታል፣ ይጠብቃታል።

አባወራው ሚስቱን ያስደስታታል አልን፦
ይኼን ሲያደርግ እንደ ሴት አውሉ ከዛሬ ነገ እተኛታለሁ፣ የወሲብ ፍላጎቴንም አሳካለሁ ከዛ በኋላ የራሷ ጉዳይ ብሎ አይደለም። የጀመረውን የፍቅር ግንኙነት ዘለቄታ እንዲኖረው በዚህ ውስጥም ትዳር በማሰብ ነው። ከትዳሩም ልጆችን ማፍራት ፣ ትውልድም እንዲደረጅ፣ ሀገርም ተረካቢ እንድታገኝ ያስባል። ርዕዩ ከጠባቧ ቤቱ በብዙ ይሰፋልና፤ የቅርብ ስሜታቸውን ከተከተሉትም በብዙ ይርቃልና ነው።

አባወራ ሚስቱን ሲያስደስታት ወሲብን ማዕከል አድርጎ ሳይኾን ትዳርን፣ በትዳርም ውስጥ የሚገኝን ፍሬ፣ የነገ ትውልድን ብሎም ከአባቶቹ የተረከባትን ሀገር በመገንባቱ ሂደት ታግዘኛለች ብሎ ነው። ይኼንን ሲያስብ ግን ወሲብ በትዳር ውስጥ የሚጫወተውን ሚና በፍጹም አይዘነጋውም። ተፈጥሮአዊ ፍላጎቷን ያውቃል፣ ለእርሱም እውቅና ይሰጣል እርሱንም ከአንደበቷ ሳይኾን ከስሜቷ ይረዳል እንደአመጣጡም ይመልስላታል ያሳርፋታልም።

ለምስኪኑ ግን እንዲህ አይደለም። ለእርሱ ሚስቱን ማስደሰት ብቸኛው ዓላማው ነው። ይኽንንም ለመፈጸም ከአንደበቷ የሚሰማው “ፍላጎት” መነሻው ነው። ተፈጥሮአዊ የኾነውን እንሰሳዊ ጠባዕይ ሰውነቷ ሳይዋሽ በግልጥ ከሚነግረው እውነት ይልቅ በሴትነቷ አይናፋርነት፣ በመንፈሳዊነቷ ትሕትና፣ በባሕላዊ ጭምትነቷ ቀባብታ የነገረችውን”እውነት” ያምናል።

አባወራ ሚስቱን ሲያስደስታት እንደምስኪኑ ራሱን ጥሎ አይደለም። እንደሴት አውሉ ራስ ወዳድ ባይኾንም እንደምስኪኑ ደግሞ ራሱን አይጥልም። ይኼ ዛሬ ዛሬ አፍቃሪ፣ አሳቢ፣ ተቆርቋሪ፣ መንፈሳዊ፣ትሑት ነን የምንል ወንዶች የምንገኝበት ጠባይ ከትርፉ ጉዳቱ ያመዝናል። ተፈጥሮን ያላገናዘበ አጉል ዘመንኛ አጉልም መንፈሳዊነት ነው። ልብ አድርግ! አንተ ሰው ኾነህ ሕሊና ቢኖርህ እንሰሳዊ ባሕሪህን ትገዛበት፣ ትጠብቅበት፣ ትመራበት ዘንድ ነው። ስጋህን ብትለቀው በአርአያ ሥላሴ መፈጠርህን ዘንግተህ ስድ እንዳትኾን አልያም ልጓሙን አብዝተህበት ሰብዓዊነትህም ተዘንግቶህ ፍጹም መልአክነትን ሽተህ እንዳትሰናከል ነው።

አባወራ ሚስቱን ይወዳታል
አባወራ ሚስቱን ሲወዳት በእርሱ ያለ መውደድ ለምስኪኑ እንዳለው ያለ አይደለም። ምስኪኑ ሲወድ ካላንቺ መኖር አልችልም፣ ካላንቺ ሕይወቴ ባዶ ነው፣ እታዘዝሻለሁ፣ እከተልሻለሁ….. የሚሉ ቃላት ከአፉ አይጠፉም በዚህም መውደዱን ይገልጻል።ልብ አድርጉ! ሠላሳ ዓመት ብቻውን የኖረው ምስኪን ሠላሳ አንደኛው ላይ ቢወድ ካላንቺ መኖር አልችልም ይላል ይህ ታዲያ ስሜታዊነቱን አጉልቶ ያሳያል። ይህ ንግግሩም የሴቷን ልብ በእርሱ ላይ ያለውን የጥንካሬ እምነት እንዲጠራጠር ሲያደርገው ከምስኪኑ ልብም ከመተሳሰር ይርቃል። ምስኪኑ ኹልጊዜ በስጋት ይኖራል “ታኮርፈኝ ይኾን፣ ትፈታኝ ይኾን፣ ትከለክለኝ ይኾን አንዱ ይነጥቀኝ ይኾን?” እያለ።

አባወራው ቢኾንስ ከሴቶች መካከል ምርጫው እንደኾነች፣ ቆንጆ እንደኾነች ይነግራታል (ሳያላዝን) ይበልጡን በተግባር ያሳያታል። እርሷን መውደዱ በእርሱ እንድትተማመን፣ ኃሳቧ እንዲያርፍ ለስሜቷም ወደብ እንዲኾናት የሚሰጣት ዋስትና እንጂ ከሄድሽ እሞታለሁ… እያለ የሚሰጋ፣ እንኳን ልትደገፍበት ለራሱም ያልጸና አይኾንም። አባወራው ምንግዜም መውደዱ ውስጥ ልበ ሙሉነት አለ። ከዚህ ልበሙሉነቱ የሚመነጭ ፍቅርን ስታገኝ ልቧ የእርሱ ብቻ ይኾናል፤ ያርፋልም።
ሴት አውል ምን ቢወዳት እንደምስኪን አይንሰፈሰፍም አልያም እንደዱርዬው በንቀት ኾነ በጉልበት አይወስዳትም። ውበቷን ቢያደንቅ ጠባይዋን ቢወድ ይኽንንም ቢነግራት እስኪተኛት ነው። ዱርዬው ደግሞ ፈለጋት አይደል መጎተት ብቻ።

አባወራ ሚስቱን ይጠብቃታል…..ይቆየን

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *