አባወራ መሪ ነው!

(ምሪት እና ስምሪትን ከሚስቱ ከሚጠብቀው ምስኪን በተቃራኒ)

መሪ መጀመሪያ መሪነቱን ኃላፊነቱን አምኖ፣አውቆ፣ተቀብሎ ይፈጽማል።አምኖ ላልነው የእምነት ሰው ነውና ኃላፊነቱን ከሰጠው አካል ሲቀበል እርሱ ሰውየው ያላመጣው ከፈጣሪ የተሰጠው ስለሆነ በሙላት በኩራት በደስታ ሊፈጽመው ህጸጽና ግድፈት የሌለበት ስለመሆኑ ነው።በንጉሥ መላክ ክብር ደስታ እንደሆነ ተላኪውንም ማንም እንዲራዳው መልእክቱም እንዲፈጸም።

አባወራውም ፈጣሪውን በሰጠው ኃላፊነት አይጠራጠረውም።አውቆ ላልነው የሰጠውን ኅላፊነት ግዴታውን ከመብቱ ጋጣወጥነትን ከቅጡ ለይቶና ተረድቶ ሚስቱ ደስ የምትሰኝበትን ልጆቹም ስነ ሥርዓት የሚይዙበትን አባታዊ ሚና ይጫወታል። ይህንንም ከአባቶቹ ይማራል ነገር ግን ያየው ሁሉ ትክክል አይሆንምና (ሚስቶቻቸውን የሚያሳዝኑ ልጆቻቸውን የሚበድሉ አባቶች አሉና)እውነቷን ይሻል ያገኝማታል(ቀደም ሲል ያመነው አምላክ ይገልጥለታል)።

አምኖ የተረዳውን ወደ ህይወቱ አምጥቶ ይኖረዋል ይፈጽመዋል። በዚህም ሚስቱን ልጆቹን በአጠቃላይ ቤተሰቡን ይመራል ይህን ልምድ ይዞም እድር ዕቁብ ይመራል ይሰበስባል። መንፈሳዊ ሰው ቢሆን ቤተክርስቲያኑ እርሱን በምትፈልግበት ቦታ ሆኖ ይመራል ወረዳው፣ክፍለ ከተማው፣ከተማው፣ሀገሩ እርሱን የሚፈልጉ ቢሆን ኃላፊነቱን ተቀብሎ ይመራል። እንግዲህ ልብ አድርጉ ሀገር መምራት ድረስ የሚያደርሰው በቤቱ የተለማመደው የመሪነት ሚና ነው።

ምስኪኑ ወንድ ግን ከፈጣሪ የተሰጠውን የመሪነት ስልጣን ፍቅር እና እኩልነት ገብቶኛል ብሎ ሚስቱን ያጋራል አንዳንዴም ሙሉ ለሙሉ ለእርሷ ይተወዋል። ልብ አድርጉልኝ ፈጣሪ አንተ(ወንዱን) ራስ፣አፍቃሪ፣ወዳጅ፣አዛዥ፣ናዛዥ አንቺ(ሴቷን)ቀሪ አካሉ፣ ተፈቃሪ፣ ተወዳጅ፣ ታዛዥ፣ተናዛዥ ሆናችሁ ቤታችሁን ሥሩት ሲል ከምን እና ከምን እንዴትም እንደሠራን ስለሚያውቅ ነው።

በእኩልነት ምሩት አዛዥ ታዛዥ መሪ ተመሪ የለባችሁም ማለት ጠፍቶት አይደለም። እኛ ዛሬ በጠባቧ ጭንቅላታችን ገባን የምንለው ዕውቀት(የፍቅርም ሆነ የእኩልነት) ለእርሱ ባዕድ ሆኖበት አይደለም እውቀት ያልነው ልክ ስላልሆነ እንጂ።
ከምን እና እንዴት እንደተሠራን የሚያውቀን እንዲህ ኑሩ ሲለን እኛ ገብቶናል ብለን እንዲያ ስንኖር ትዳርም አይሰምርም ትውልድም ትውልድ ሀገርም ሀገር አይሆኑም።

ወደቀደመ ነገራችን ስንመለስ አባወራ ወንድ መሪነቱን ሲለማመድ ከእልፍኙ ውጪ በጉርብትናው፣ በመንፈሳዊ ቦታ፣ በሥራ ገበታው፣ በአለማዊ አስተዳደሩ(በሕዝባዊ አስተዳደሩ) በጠቅላላው ለወገኑ፣ ለሀገሩ፣ለዓለም የሚሰጠው ፋይዳ ከፍተኛ ነው። ከእልፍኙ ወደ ውስጥ ስንገባ ደግሞ ሚስቱን በእርካታመንኮራኩር ጭኖ ሰማየ ሰማያት የሚያደርሳት የስሜቷ ጥግ፣የእርካታዋ ምንጭ፣የጥያቄዋ መልስ፣የማዕበሏ ወደብ፣የረሀቧ ጥጋብ፣የጥማቷ እርካታ……ይሄው አባወራ ነው…ሴት ልጅ ይህን ወንድ የምትገልጽበት ቃላት ያጥራታል ከእቅፉ ገብታ የደስታን እንባ ከማንባት በቀር።

አዳሜ ልብ በል! የተጋቡ ሰሞን ብቻ ወይንም አብረው ለመጀመሪያ ጊዜ አንሶላ የተጋፈፉ ቀን ብቻ አይደለም አባወራው በህይወት እስካለ እንጂ።የአባወራውን ሚስት እድሜም ሆነ ልጅ መውለድ ከአባወራው ባሏ ይህን እንዳታጣጥም አይከለክሏትም። ምናባዊ ልብ ወለድ አይደለም አምነው ለተቀበሉት እና ለሚፈጽሙት የሚኖር እውነት እንጂ።ሁሌም ለዚህ ንጉሥ ምርኮኛ፣ሁሌም የእርሱ ውብ፣ሁሌም የውበት ድንግል፣ሁሌም አዲስ እና የማይጠግባት ናት (እድሜ እና ወሊድ የማይገድቡት ሁሌ!!!!!!ነው)።

ምስኪኖቹ ግን ብዙ ጊዜ ሴት ልጅ ስትወልድ ወደ ልጆቿ ነች፣ለባሏ ያላትም ፍላጎት ይቀንሳል፣ለተራክቦ ብዙ ጊዜ ፈቃደኛ አይደለችም ይላሉ። ይህን ገጽ አንብቡ በሏቸው። አባወራ አይደሉም።
በመኝታ ቤታቸው ውስጥ በአልጋቸውም ላይ ንጉሡ እርሱ(አባወራው)ነው እርሷማ ንግሥቲቱ እንጂ ጌታዋን የምትከተል በፍጹም እምነት የምታምነው፣ የሚሰጣትንም የምታጣጥመው። እርሱ በንግሥናው አልጋ የአምላኩን የፍቅር ህግጋት ከፊት አድርጎ አደራ ውደዳት እንደተባለው በየቀኑ የፍቅርን ሀሁ ያስጠናታል በየቀኑም ይወዳታል በየቀኑም ውብ ንግስቱ እንደሆነች ይነግራታል በየቀኑም……።

አዎን አንተ አባወራ ነህ?ትዳርህን ሚስትህን ትመራለህ? ወይስ ዘመነኛ ነን እንደሚሉት እልፍኙንም መኝታ ቤቱንም በጠረጴዛ ዙሪያ ነው የምታስተናግደው? ልንገርህ በተለይ በተራክቦ ለሚኖራችሁ ስምረት ያንተ መሪነት ግድ ነው። ታዲያ በእልፍኝና በውጪው ያልተለማመድከው መሪነት መኝታቤት ከየት ይመጣል?

መሪ መፈክር አለው። አባወራ መሪ ነው።መፈክሩም፦ ፍጹም የሆነ የህይወት ደስታ እና እርካታ ለእነዛ ውብ እና ጣፈጭ ሚስቶቻችን ለልጆቻችን እናቶች ከነግህ እስከ ሰርክ እስከ ሌሊት ይገባል! ሚስቶቻችሁን የምትወዱ አብራችሁኝ በሉ ድገሙትም።….ይቆየን

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *