አባወራ በራሱ ይተማመናል፤ ሚስቱንም ይጠብቃል

አባወራ ሚስቱ የሚያስፈልጋትን በማድረግ፣ ስሜታዊ(sensitive) መኾኗን ተረድቶ ይጠብቃታል። የዱርዬው ጥበቃ ተፈጥሮአዊ ነጻነቷን የገፈፈ እና ከፍተኛ ቅናትም የተቀላቀለበት ነው። ሴት-አውል ግን የኔ የሚላት አንዲት ሴት ስለሌለችው ይኽ አይመለከተውም። ስለዚም ምስኪኑ ውስጥ ፍርሃት እና ስጋት፣ ዱርየው ውስጥ ከፍተኛ ቅናት፣ ሴት-አውሉ ጋር ደግሞ ግድ የለሽነት ይገኛሉ።

ምስኪኑ ፍርሃቱና ስጋቱ እየተማቱበት በራስ መተማመኑ ከጊዜ ወደ ጊዜ ሲያሽቆለቁል በተቃራኒው ደግሞ ዱርየው ከልክ ላለፈ ቅናቱና፣ ተቆጣጣሪነቱ ማስፈጸሚያ ጉልበቱን በመተማመን ጥበቃው ይጨምራል።

ከዚህም (ከፍርሃቱ እና ስጋቱ) የተነሳ ምስኪኑ “ትክክለኛውን” ነገር በማድረግ ወይም በነገሮች ኹሌ “ትክክል” ሲኾን ሚስቱ የምትወደው የምትጠበቅለትም ይመስለዋል። ይኼን ኹሉ አድርጎላት አይኗ ግን ወደ ሌላ(ወደ ዱርየው) ሲያማትር “ሴቶች ኹሉ አንድ ናቸው የሚንቃቸውን እንጂ የሚንከባከባቸውን ወንድ አይሹም” ይላል።

አንተ ለሚስትህ የሚያስፈልጋትን በማድረግ (ልብ አድርግ! እንደምስኪኑ የምትፈልገውን ሳይኾን) ስሜታዊ መኾኗንም ተረድተህ ሌሎች ተፈጥሮዋንም ግምት ውስጥ የከተቱ አመክንዮችን ተጠቅመህ ልትጠብቃት ግድ ይልሃል። ጥበቃህ ደግሞ የእርሷን ሙሉ ሰውነት(አእምሮዋን፣ መንፈሷን እና አካሏን) ይጨምራል።

ነገር ግን አንተ ወድጃታለሁ አገባታለሁ (አግብቻታለሁ) ለምትላት ሴት ይኼን ጥበቃ እና ከለላ ለማድረግ ምን ያክል ዝግጁ ነህ? አንተ ራስህ በራስ መተማመንህ(በአእምሮህ፣ በመንፈስህ እና በአካልህ) ምን ያክል ልቀሃል፣ ጸንተሃል፣ ጠንክረሃል?

በአእምሮህ መበልጸግ አለብህ ስልህ በዓለማዊው ጥናት ተጨልጠህ ዲግሪ፣ ማስተርስ ….ይኑርህ ማለቴ አይደለም። መንፈሳዊ ጥበብንም ታጠቅ ስልህ ከጉባኤ ቤት ገብተህ እንድታስመሰክር አይደለም። የአካልህን ጥንካሬ ሳወሳህ ከስፖርት ቤት ተመዝግበህ ጡንቻህንም እንድታፈረጥም አይደለም።
ነገር ግን በዓለም ላይ ሕጋዊ ኾነህ ስትኖር ታተርፍበት ዘንድ የተመጣጠነ እና ልከኛ አልያም ማዕከላዊ ስብዕና እንዲኖርህ እንጂ።

ሴቶች ከምንም በላይ በራሱ የሚተማመን ወንድ ይስባቸዋል መሳባቸው ግን በስሜት እንጂ በአመክንዮ አይደለም። ለዚህ አስረጅ ደግሞ ምስኪን ወንዶች ከአፋቸው የማትጠፋ የምሬት ቃል አለቻቸው። እርሷም “ሴቶች የሚንቃቸውን(ዱርዬ ወንድ) ይሻሉ” የምትል ናት። ልብ አድርጉ ዱርየው የራሴ ነው ለሚለው ነገር ጥበቃ ለማድረግ ሲል ጉልበቱን(የራስ መተማመኛ ኾኖት) ይጠቀማል።

ምስኪኖች ግን ከዚህ ተነስተው ሴቶችን ከቻሉ በምክር አልያም በቁጣ ከዚህ ተግባር ሊመልሷቸው ይሞክራሉ። ሴቶችም ራሳቸው እንኳ ሳይቀሩ ይህ ለዱርየው ወንድ የመሳባቸውን ነገር ክፉ መንፈስ እንዳሳሰባቸው ቆጥረው በጸበልም ኾነ በጸሎት(“መንፈሳዊ በመኾን”) ሊያርቁት ይሞክራሉ። ይህ ኹሉ ድካም ግን ተፈጥሮአችንን ካለመረዳት የመነጨ በመኾኑ ውጤት አልባ ከንቱ ድካም ነው።

ይህ ኹለት መሠረታዊ ስህተት አለበት። አንደኛው ሲጀመር ዱርየውን ወንድ ያስወደደው ዱርዬነቱ ሳይኾን በዱርዬነቱ የተሸፈነው በራስ መተማመን ነው። ኹለተኛው ደግሞ መንፈሳዊነት ምስጢር በመመርመር እና በመግለጥ ተፈጥሮንም ኾነ ፈጣሪን እንረዳበታለን እንጂ እኛ ስለወደድን አልያም ስላልወደድን ተፈጥሮአችንን የምንጠመዝዝበት አይደለም።

ስለዚህም ሴቶች በራሱ የሚተማመንን ወንድ ከስሜታዊው ምስኪን ይልቅ ይመርጣሉ። ነገር ግን በአኹኑ ሰዓት በራሱ የሚተማመን ወንድ ማግኘት አስቸጋሪ ነው (ዱርየውን በማውገዝ ሂደት በጠቅላላው ወንዶች ውስጥ ያለው በራስመተማመን በአንድነት ተፈርጆ ይወገዛልና)። ሴቶቹ ትዳርን፣ ኃላፊነትን፣ ክብካቤ፣ ምቾትን፣ ገንዘብን፣ ዝናን”ፍቅር”ን፣ ሲያስቡ ምስኪኑን ይመርጣሉ፣ ያገባሉም። ነገር ግን ተፈጥሮአዊ ስሜታቸውን የዱርየው በራስመተማመን ያሸንፈዋል። አንተ ወደድክም ጠላህም እውነቱ ይኽ ነው።

ስለዚህም ለምትወዳት ሴት ጥበቃ የምታደርግበት፣ በዚህም ተወዳጅነት የምታተርፍበት ከዱርየው የተለየና የራቀ፣ ሴት-አውሉ እና ምስኪኑ የሌላቸው የራስመተማመን ሊኖርህ ይገባል። በአእምሮ፣ በመንፈስ፣ በአካል ስትበለጽግ የራስመተማመንህ ይጨምራል። ለእነዚህ ደግሞ የማይታበል ምንጫቸው፦
1ኛ. አባት
2ኛ. የራስ ጥረት ናቸው …. ..
ሳምንት ብንኖር
1ኛ. ተፈጥሮአዊውን እና ምትክ የለሹን የራስመተማመን አሰልጣኝ…. አባትን እናያለን…ይቆየን

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *