አባወራ እና ምስኪን በንጽጽር 

ለዛሬ እስቲ አባወራን ከምስኪኑ (ዘመኑ ከሰለበው ወንድ) ጋር እናነጻጽረው። በቅንነት እናንብበውና እኛ የቱ ጋር ነን ብለን ራሳችንን እንፈትሽ። ያልተስማማንበትን ኃሳብ ብንወያይበት ደስ ይለኛል። አባወራው ወይም ምስኪኑ መገለጫቸውን እናነሳለን እንጂ በወቅቱ ላያገቡም ይችላሉ።
አባወራ ////// ምስኪኑ ዘመነኛ
የቃሉ ሰው ነው/// ሰዎችን አስደስታለሁ ሲል ቃሉን አይጠብቅም
የሚናገረውን የሚያደርገውን ያውቃል ///መረጃዎቹ በመሰለኝና በአሉታ የታጀቡ ናቸው
ስለማያውቀው አያወራም///እወዳታለሁ ለሚላት መቀባጠር ይወዳል
የማይችለውን አይሰራም/// ለሚወዳትማ ሁሉን ይችላል
ለተናገረው ለሠራው እኔ ነኝ ሲል ኃላፊነት ይወስዳል//መጋጨትን ጭቅጭቅን ሊሸሽ ስህተቱን ይደብቃል
በተቻለው መጠን ከራሱ ቃል የሚጣረስ ድርጊት አይሠራም///ልወደድ ብሉ የራሱን ቃል በተደጋጋሚ ይጥሳል
ያመነበትን እንጂ የሰው ፊት እያየ አይሠራም///የሰዎችን በተለይም የሚስቱን ፊት አይቶ ዓላማውን ይስታል
ስለራሱ በራሱ ማንነት ላይ የቆመ ስብዕና አለው///ማንነቱ በሰው አስተያየት ላይ የቆመ ነው፤ስለራሱስለድርጊቱ ማረጋገጫ ይፈልጋል በተለይ ከሚስቱ
የፈለገውን የወደደውን በግልጽ ይናገራል///የፈለገው ሌላ የሚጠይቀው ሌላ የሚያገኘው ሌላ
ሚስቱን ማዘዙ ተፈጥሮአዊ መኾኑን ያውቃል///ሚስቱን ማዘዝ (ትዳርን ማፍረስ) የማይታሰብ
ክብሩን የምትጠብቅ ያገባል/// እለውጣታለሁ ብሎ የማታከብረውን ያገባል
እርሱ ቅጠኛ ነው///ፍቅርን ምክንያት አድርጎ መላቅጥ የለውም
ቤቱን ቅጥ የማስያዝ ኃላፊነቱን አይዘነጋም ///ለእርሱ ሚስቱን ቅጥ ማስያዝ ጭቆና ነው
ልጆቹን መቅጣት ከጥፋት መታደግ ነው////ልጆቹን ለመቅጣት ሆዱ ቡቡ ነው
በቤቱ የመጨረሻው ወሳኝ ነው /////ውሳኔ ዳገቱ
ከሚስቱ ለመተኛት ማግባቱ በቂው ነው////ሚስቱን ለመተኛት ተለማምጦ ያውም ከተሳካለት
ሚስቱን ሲተኛ እርካታዋን ያስቀድማል////እርሱ ሲደሰት ትልቅ ችሎታው ነው
ሚስቱ መደሰቷን ያውቃል ////ሚስቱ መደሰቷን ይጠይቃል
የሽርሽር ጊዜያቸውን ያቅዳል /////ለሽርሽር ሚስቱን ልጆቹን ይጠይቃል
በአቋሙ ጽኑ ነው ////በአቋሙ (ካለው) ሚስቱን ጨምሮ ልጆቹ ይሳለቁበታል
ገዢ ነው ባለግርማ ሞገስ ////ፍቅርን ተገን አድርጎ ምንም ሞገስ የለውም
እንኳን ድርጊቱ ትከሻው አይኑ በቂ ነው /// ልምጥምጥ እና ስልምልም ነው
ስለእውነት ከማንም ግጭትን አይፈራም ///በተለይ ከሚስቱ መጋጨትን የሞት ያህል ይፈራል
ድምጹ መሣሪያው ነው ቅጣቱም ልከኛ ወቅታዊ እና ቤቱን ታዳጊ ነው//// ዝምታ ትልቁ መሣሪያው ሲኾን ሲበዛበት ግን አጥፍቶ ጠፊ ነው
ወድጃለሁ ብሎ የወደደውን ለማገኘት ይነሳል/////ፍቅር ይዞኛል ብሎ ያለቅሳል
የሚወዳትን እንደ ሀገሩ ባህል ይጠይቃል ////ይወዳል ለጥያቄው ግን ይቀደማል ይቀማል
አስቦ አቅዶ ቀን ወስኖ የወደዳትን ያገባል///ሲለማመጥ ይኖራል ወይ ማግባት ለመወሰን ይቸገራል
ባለው የሚኮራ ለሰውም የሚተርፍ ነው///ባለው የሚሸማቀቅ ሚስቱንም የሚያሳቅቅ ነው
ሚስቱ የምትነግረውን ሳይኾን የሚሰማትን(የስሜቷን) የምትፈልገውን ጥግ ያደርሳል///ሚስቱን ያስደሰተ መስሎት ከእልፍኝ እስከ መኝታ ቤት ፍላጎቷን ይጠይቃል
በተፈጥሮአዊ እውነት ላይ ይመረኮዛል/// ሰዎች በምክርቤት ያጸደቁትን(የለፈፉትን)ይቀበላል
ከእልፍኝ መኝታቤት፣ከመኝታቤትም አልጋ ላይ ወንድነቱ ያይላል ////ከእልፍኝ መኝታቤት፣ ከመኝታቤትም አልጋ ላይ ምስኪንነቱ ይበረታል
ጀግንነቱ ደጅም ቤትም ነው//የደጅ ጀግና፤በቤቱ ካገኘ ተደስቶ ፊት ከተነሳ ተጠቅልሎ ይተኛል
ግርማ ሞገሱ ስብዕናው እንጂ ከመልኩ ወይም ከሰውነቱ አይደለም///አለመከበሩን አጭር፣ ቀጭን ስለኾንኩ ብሎ ያሳብባል …….

አባወራም ኾነ ምስኪኑ በሥራቸው የተዘረዘሩትን ሁሉ ይኾናሉ ማለት ሳይኾን አንዱ አብዛኞቹ ይገልጿቸዋልና ነው። እስቲ ሰውን ሳይኾን ራሳችንን እንይባቸው።…..ይቆየን

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *